እር'ቃን
በ ዕድል፡ አይደል ፡በ አጋጣሚ፡ ግን ፡በ ዕጣ ፈንታ ፡ ነው፥
ክቡር ፡ ንኡድ ፡ ስምሽን ፡ ከኮከቤ ፡ የፃፈው፥
በ እኔ ፡ ቀለም ፡ በ እኔ ፡ ብሩሽ ፡ በ እርሳሴ ፡ ስሎሽ፥
በእኔው ፡ ቃላት ፡ በእኔው ፡ ዓለም ፡ በእኔው ፡ ድርሰት ፡ ፈጥሮሽ፥
ከ ኮከቤ ፡ ፅፎሽ ፡ ቀርፆሽ ፡ ከ ሕይወቴ፥
ፀሐዬን ፡ ሰይሞሽ ፡ በርተሽ ፡ በ እኔነቴ፥
ሞቴ ፡ኑሮሽ ፡ ቢሆን ፡ ኑሮሽ ፡ ቢሆን ፡ ሞቴ፥
ፍቅሬ ፡ ከፍቅርሽ ፡ አይሎ ፡ ብትሆኝ ፡ ስስቴ፥
እንደው ፡ በ አንድዬ ፡ እናት ፡ ስሚኝ ፡ በ እመ ብርሃን፥
ምን ፡ በድዬ ፡ ምን ፡ አጥፍቼ ፡ ይሆን ፡ በህልሜ ፡ ማይሽ ፡ በር'ቃን።
ዘረ-ሠናይ
@Prince_Zeresenay