"በርተሚዮስ ነኝ " Bertemios Negn
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
Liqe Mezemran Yilma Hailu
===================
በርተሚዮስ ነኝ የአይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል (2)
የልቦናዬ አይን ፈጽሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርተሚዮስ ይላል
አብዝቼ እጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ (2)
አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በሀጢያት ሰንሰለት ታስረሃል እቅተዎች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሃለሁ ሳልታክት (2)
የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለኔ የሞተው እየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል(2)
አብዝቼ እጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልጽ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች (2)
====================
Channel :
@yilma_hailu_mezmurs