ማራናታ 🙏🤲


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7
👉 የቻናሉ አላማ
✔️💠 የአባቶች ምክር
✔️💠መንፈሳዊ መዝሙሮች
✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል
ለማንኛውም ሀሳብ @merii19✣✣

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: B̶r̶o̶k̶e̶n 💔❤️‍🔥
ልዩ የገና ፓኬጅ  በተመጣጣኝ ዋጋ

እንደምርጫዎ በትዕዛዞ መሰረት እናዘጋጃለን

      @merii19

             👉 @merii19


ልዩ የገና ፓኬጅ  በተመጣጣኝ ዋጋ

እንደምርጫዎ በትዕዛዞ መሰረት እናዘጋጃለን

      @merii19

             👉 @merii19




.....በየዕለቱ ምን ያህል ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ወደ እኛ ይመጣሉ? ትዕግሥትን ገንዘብ በማድረግ በአስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉን እየቻልን መከራዎች እንዳያጠቁን ለሚጠብቀን አምላካችን ምስጋናና ክብርን ለማቅረብ እንዴት ያለ ብርቱ ነፍስ ያስፈልገን ይሆን? ምን ያህልስ ያልተጠበቁ መከራዎች ሊነሱብን ይችሉ ይሆን? ጻድቁ ኢዮብ ብዛት ያላቸውና ከባድ ፈተናዎችን በተጋፈጠ ጊዜ ከአንደበቱ ምንም ዓይነት የስንፍና ንግግር ሳይወጣው ለአምላኩ ምስጋና ማቅረቡን እንዳላቋረጠ ሁሉ እኛም የሚመጣብንን ክፉ አሳብ በሙሉ መልሰን መዋጋት አለብን።

አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ሲሰናከሉ ወይም በሌሎች ስማቸው ሲጠፋ ወይም ከባድ በሆኑ በሽታዎች ሲያዙ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መንቀፍ ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለበሽታው ሕመም አሳልፈው ይስጡ እንጂ ከሚገኘው ጥቅም ወይም በረከት ራሳቸውን ያራቁ ናቸው፡፡

ሰው ሆይ! የመድኃኒትህን፣ የረዳትህንና የጠባቂህን ስም በከንቱ ስታጠፋ ምን እያደረግህ ነው? ወይስ ከታላቅ የገደል ጫፍ ላይ የመጨረሻ መውደቂያ ወደ ሆነው ጉድጓድ ራስህን እየወረወርክ መሆንህ አይታወቅህ ይሆንን? የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ብታጠፋ መከራህን ልትቀንስ አትችልም። ትችላለህን? ይልቁንም መከራህን በማባባስ ጭንቀትህን የበለጠ ከባድ ታደርጋለህ፡፡ ዲያብሎስም ለዚሁ ጉዳይ ብሎ የሚያዘጋጃቸው ብዛት ያላቸው መከራዎች አንተን ወደ ጉድጓዱ ይመሩሀል፡፡ እርሱ እግዚአብሔርን ማማረርህን እንደ ቀጠልህ ሲመለከት መከራዎቹን በመጨመር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደርሳቸዋል። እንዲህ በማድረግም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንድትገለው ያደርግሃል፡፡ ነገር ግን በጽናት ተቋቁመህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብህን ካላቋረጥክ የመከራው ብዛት እየከፋ ይሂድ እንጂ ከአንተ ጋር መዋጋቱ ጥቅም የሌለው መሆኑን ስለሚያውቅ አንተን መፈታተኑን ያቆማል፡፡ አንድ ውሻ በማዕዱ ፊት ለፊት ተቀምጦ በመመገብ ላይ ያለው ሰው ፍርፋሪ የሚሰጠው ከሆነ በጽናት ቁጭ ብሎ ይጠብቃል። ነገር ግን ምንም የሚበላ ነገር የማይወረውርለት መሆኑን ካወቀ መጠበቁ ዋጋ የሌለው መሆኑን ስለሚረዳ ከዚያ ቦታ ፈቀቅ ብሎ ይሄዳል፡፡ ልክ ውሻው የሚበላ ነገር ይወረወርልኛል ብሎ እንደሚጠብቀው ዲያብሎስም የእግዚአብሔርን ስም የሚያጠፋ ቃል ይወረወርልኛል ብሎ ይጠብቃል፡፡ ከወረወርክለት በድጋሚ ያጠቃሀል፡፡ ነገር ግን ምስጋና በማቅረብህ ከቀጠልህ በረሀብ አለንጋ ስለምትገርፈው ከጫንቃህ ላይ ትወረውረዋለህ፡፡

አንተ ግን በጭንቀት ስዋጥ ዝም ማለት አልችልም ብለሃል፡፡ እኔ ምንም ዓይነት ቃል እንዳይወጣህ አልከለክልህም። የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ከምታነሣ ይልቅ ምስጋናን አቅርብለት፡፡ ተስፋ ከመቁረጥም በእግዚአብሔር ታመን፡፡ ንስሓ በመግባት ድምፅህን ጮኽ አድርገህ በጸሎት ዕንባህን አንባ፡፡ አምላክህንም ከፍ ባለ ድምፅ አመስግን፡፡ እንዲህ ባለው መንገድ መከራዎችህን ታቀልላለህ፡፡ ምክንያቱም አንተ ለጌታህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስታቀርብ ተራዳኢነቱ በአጠገብህ ስለሚገኝ ዲያብሎስ ከአንተ ይሸሻል፡፡ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ብታነሣ ወይም ብታማርር ግን የእግዚአብሔርን እርዳታ ከአንተ ስለምታርቅ ዲያብሎስ በአንተ ላይ የበለጠ እንዲነሳሳ በማድረግ ራስህን የከፋ መከራ ውስጥ ትከታለህ፡፡ ምስጋና የምታቀርብ ከሆነም የዲያብሎስን ደባ ከአጠገብህ ስለምታጠፋ የጠባቂህ የእግዚአብሔርን እንክብካቤ ወደ አንተ ታቀርባለህ፡፡

እንዲያው ልማድ ሆኖበት ብዙ ጊዜ አንደበት ክፉ ቃላትን ማውጣት ይጀምራል፡፡ እንደዚህ ማድረግ በሚጀምርበት ሰዓት ያንን ክፉ ቃል ከመናገሩ በፊት መላስህን በጥርስህ ንከሰው፡፡ መላስህ አንዲት ጠብታ ውኃ አጥቶ ጥማቱን ማርካት ከሚሳነው ይልቅ አሁን በደም ቢታጠብ ይሻለዋል:: ልክ ባለጸጋው ሰው በነበልባሉ ሲቃጠል ምንም ማስታገሻ እንዳላገኘ ሁሉ ምላሳችን ማብቂያ የሌለውን ቅጣት ከምትቀበል ዛሬ ጊዜያዊ ሕመም ብትታመም ይሻላታል፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን እንድትወዱ አዝዟችኋል፡፡ እናንተስ ከሚወዳችሁ ከእግዚአብሔር ትርቃላችሁን? «ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፣ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ስለሚበድሏችሁም ጸልዩ፡፡» (ሉቃ 6፥27-28)። እናንተ ግን ክፉ ሲገጥማችሁ በረዳታችሁና በጠባቂያችሁ ላይ መጥፎ ልትናገሩ ትችላላችሁን? ከገጠማችሁ ፈተና ሊያወጣችሁ እንደማይችል አልተናገራችሁምን? እርሱ ግን ይህንን ጠባያችሁን እንድታሻሽሉ ፈቅዶላችኋል። በአንጻሩ እናንተ ወድቄያለሁ ጠፍቻለሁም ትሉታላችሁ፡፡ የጠፋችሁት ግን ከፈተናችሁ ክብደት ሳይሆን በራሳችሁ ስንፍና ነው፡፡

እስቲ ንገሩኝ! የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ማንሣት ይሻላል ወይስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ? በእርግጥ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ማንሳት አድማጮችህ እንዲጠሉህና ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዲገቡ ካደረጋቸው በኋላ በመጨረሻ ታላቅ ሥቃይን ያመጣባቸዋል፡፡ ምስጋናን ማቅረብ ግን ብዛት ያላቸው የጥበብ አክሊሎችን አግኝተህ በእያንዳንዱ ሰው እንድትደነቅ ያደርግሃል፡፡ ይህም በመጨረሻ ታላቅ ዋጋን ከእግዚአብሔር ዘንድ ያስገኝልሀል፡፡ ታዲያ እንዴት ቀላል፣ የሚረዳህንና ጣፋጭ የሆነውን ትተህ የሚጎዳህን የሚያሳምምህንና የማይረባህን ትከተላለህ?

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
    
@yleybgal19
@yleybgal19




🌿ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ 🌿

ቅድስት አርሴማ እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡ ይቺ ታላቅ ሰማዕት በነበረችበት ዘመን በአርመን የነገሠው አረማዊ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፡፡ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ “ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ” ብሎ የተናገረውን በመቃወም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም ያመልክ ነበር /ዘጸ.34፥17/፡፡ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖችን
“እኔ ለማመልከው “አምላክ” ወይም ጣዖት መስገድ አለባችሁ፤ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ትእዛዜን ጥሳችኋልና መከራ ይጸናባችኋል”
የሚል ዐዋጅ በማውጣት መከራ ያደርስባቸዋል፡፡
ጨካኙ ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ትእዛዙን ባለማክበራቸው መከራና ስቃይ ያደረሰባቸው ክርስቲያኖች ቁጥራቸው 27 ናቸው፡፡ “እኔን የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ያለውን የእግዚአብሔርን ሕግ የፈጸሙ ክርስቲያኖች እሱ ለሚያመልከው ለጣዖት አንሰግድም በማለታቸው ይደበድባቸውና ግፍና መከራ ያጸናባቸው ጀመር፡፡ ይህን ግፍና መከራ የተመለከተች እናታችን ቅድስት አርሴማ የተጋድሎ ሕይወትን እነሱን አብነት አድርጋ እንደ ጀመረች የሕይወት ታሪኳን የያዘው መጽሐፏ ይነግረናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ‘‘ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሳጧችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ! ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን ስለ እኔ ወደ ገዢዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ… አትጨነቁ! በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም” /ማቴ.10፥16-20/፡፡ ብሎ የተናገረውን በማሰብ ቅድስት አርሴማ በሃያ ዓመቷ የንጉሡን እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ሰማዕታት ወገኖቿ ጋር በመሆን ስለ እግዚአብሔር አምላክነት ትመሰክር ነበር፡፡
የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ሰማዕትነትን ልትቀበል በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ሚስት ትሆነው ዘንድ አብዝቶ ተማጸናት፡፡ እጅ መንሻና ማታለየ የዚህን ዓለም ወርቅና ብር አቀረበላት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን መልክ ረጋፊ፤ የዚህ ዓለም ሀብትም ከንቱ እንደሆነ ስለምታውቅ በዓላማዋ ጸናች! ንጉሡንም ‘‘እኔ የንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለት መለሰችለት፡፡
ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ እግዚአብሔር አምላኳን በማመኗ ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሠሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
በቅድስት አርሴማ የገድል መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ታሪክ በተመሳሳይ መልኩ በትንቢተ ዳንኤል ላይ ሲፈጸም እናያለን፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ያለ በደሉ በክፉ ሰዎች ምክር የተራቡ አንበሶች ወዳሉበት ጉድጓድ በተጣለ ጊዜ አንበሶቹ ፈጽሞ ጉዳት አላደረሱበትም፣ እንኳን ሊበሉት የእግሩን ጥፍር እየላሱ ተገዝተውለታል፡፡ “በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ ፈጥኖም ወደ አንበሶቹ ጉድጓድም ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኃዘን ቃል ጠራው፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፡- የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው፡፡ ዳንኤልም ንጉሡን ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና በአንተም ፊት ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም አለው” የዳንኤል ከሳሾች ግን “በአንበሶች ጉድጓድ ጣሏቸው፤ ወደ ጉድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዟቸው ዐጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ” /ዳን. 6፥19-25/፡፡
ንጉሡ የክርስቲያኖቹ በሰማዕትነት መጽናት ስለነደደው በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሠሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ከእሳት ያወጣቸው እግዚአብሔር አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ የክርስቲያኖቹ የእምነት ጽናት የሚደንቅ ስለነበር ንጉሡ አማካሪዎቹ ጠርቶ
“ምን ብናደርግ ይሻላል?” የሚል ምክር ጠይቆ ሁሉንም በሰይፍ ተሰይፈው እንዲሞቱ ስምምነት ላይ ይደርሳል፡፡
እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በሰማዕትነት አምላኳ እንዲያጸናት እየጸለየች “አይዟችሁ ጽኑ! የዚህ ዓለም መከራ አያሰቅቃችሁ! አትፍሩ” እያለች ታጽናናቸው ነበር፡፡
ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ “አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም! ስቃይ አጸናብሻለሁ” ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት ዓይኗን አስወጥቶ በእጇ እንድትይዝ አደረጋት፤ ጡቷን ቆረጣል፤ በኋላም አንገቷን በሰይፍ በመቅላት መስከረም 29 ቀን በሰማዕትነት እንድታልፍ አድረጋት፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ
‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ እንዲል /መዝ. 8፥3/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን ያዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡
የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይኑር፡፡ አሜን! ! !

"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ፡ ወከዓዉ ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ፡ ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።"

21 መዝሙር
ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ
@yleybgal19
@yleybgal19

                   


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ትዩብ
ንስሐ በገባኽ ጊዜ ሳይሆን፥ ኃጢአት በሠራህ ጊዜ እፈር።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ትዩብ
👉 ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተመቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመ ነበርኪ ፲ወ፪ተ ዓመተ እንተ ትትናዘዚ እምኀበ መላዕክት ስቴኪኒ ስቴኪኒ ስቴ ህይወት ውእቱ ወመብልዕከኒ ኀብስት ሰማያዊ 👉

      ትርጉሙም

👉 እንዲህ ኹነሽ በቤተመቅደስ ኖርሽ፤መላዕክትም ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤መላዕክት እየጎበኙሽ እንደዚህ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖርሽ 👉

       ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል (በዓታ ለማርያም ) ወደ ቤተመቅደስ የገባችበት ዓመታዊ በዓል አው ለታላቁ ኢትዮጵያዊ ፃድቅ ለአቡነ ዜና ማርቆስ ዓመታዊ በዓል አው ለሊቀ መላዕክት ለቅዱስ ፋኑኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በስላም አደረሳችሁ አደረስን 🙏

✤ ታኅሣሥ ፫(3) በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ቅድስት ሃና ወቅዱስ ኢያቄም ፋኑኤል ሊቀ መላዕክት ለዕረፍት ለቅዱስ ለአቡነ ዜና ማርቆስ አው ወክብራን ነገሥት ዕረፍቱ ለአፄ ሚኒሊክ ንጉሥ ነገሥት ዘኢትዮጵያ 👉

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እበውእ ቤተከ ምስለ መባዕየ
ወእሁብ ብፅአትየ ዘነበብኩ በአፉየ
ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ

✤ ትርጉም ✤

የሚቃጠል መባእ ጋራ ወደ ቤት እገባለሁ
መከራዬን ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን
ከንፈሮቼም ያሉት ስእለቴን

            መዝ ፷፭-፲፫
                   65  13

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፩ ቁ ፩-፲፯
           1     1  17

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ዕብ ም ፱ ቁ ፩-፲፩
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፭-፰
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪-፲፭

❖ ምስባክ ❖

ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ዘአጽምዒ እዝነኪ
ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ
እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ

🙏 ትርጉም 🙏

ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ
ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ
ንጉሥ ውበትሽን ወዶአል

             መዝ ፵፬-፲
                    44  10

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፩ ቁ ፴፱-፶፮
          1     39  56

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዝእትነ

" ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደ ሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና በቤተመቅደስ ኖርሽ እንጂ "
        ቅዳሴ ማርያም
           ም ፩ ቁ ፴፱
               1     39

✝ በዓሉ በዓል ምህረት በዓለ ፀጋ ያድርግልን ፆሙን ፆመ በረከት ያድርግልን ፆሙን ለማበርከት ያብቃን አምላካችን መድኃኒታችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሙን በአንደበታችን ታሳደርብን ከበዓሏ እግዝትነ ማርያም በዓታ በረከት ትክፈልን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ሊቀ መላዕክት ከቅዱስ ሩፋኤል በምልጃዋ አይለየን ከአባታችን ከአቡነ ዜና ማርቆስ በረከት ይክፈልነ ✝️


                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
  ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ
🌟
@orthodox_graphics_tub
ሪያክት ማድረግ አይርሱ 👇


 
📱 📱 📱        


በዓታ ለማርያም
---------------------------
ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም ከቅድስት ሐና እና ከቅዱስ ኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡

ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፤ ካህኑ ዘካርያስም ስለምግቧ በመጨነቁ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነስቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› ባላት ጊዜ ቅድስት ማርያም ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር ብለው አስገቧት፤ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡


ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላት ግን ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ ትውጣልን በማለት አይሁድ በጠላትነት ተነሱባት፡፡

ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን ጠየቃት «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም
«ከእግዚአብሐር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናት አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትራቸውን ሰብስበህ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይ አድረህ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጣው ብሎ ምልክትም እሳይህአለው ብሎ ነገረው፡፡

እርሱም እንዳለው አድርጎ በማግሥቱ በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት፤» የሚል ጽሑፍ አገኙ፤ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋለች፤ ስለሆነም ዮሴፍ እንዲጠብቃት ተወሰነ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ😍😍

21 መዝሙር
ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ
@yleybgal19
➪@


የበዓታ ማርያም መዝሙር ስብስብ 😍

21 መዝሙር
ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ
@yleybgal19
@yleybgal19






ከሚከተሉት ውስጥ''ፍሰሐ'' ለሚለው ቃል ተቃራኒ የቱ ነዉ?


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ትዩብ
“ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥
በመንፈሱም ላይ የሚገዛ  ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።”
  — ምሳሌ 16፥32








Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#ችግርን ያየ ሰው ይራራል

Показано 20 последних публикаций.