أبو عكرمة አቡ ዒክሪማ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


قال ابن مسعود رضي الله عنه: كفى بخشية الله علماً, وكفى بالاغترار بالله جهلاً.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በኦክስጅን የሚተነፍስ የልብ ህመምተኛ እባክህ ልጄ ቤቴን አታፍረስ እያለው ድብን በል ከሚል ማህበረሰብ ምን ትጠብቃለክ?


فَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَىْءٍۢ فَمَتَٰعُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا ۖ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

  {ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ህይወት መጠቀሚያ ነው። አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ለነዚያ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው}።

አብሽር ወንድሜ ብዙ የማፅናኛ ቃላቶች ቢኖሩኝና ብፅፋቸው ደስ ባለኝ ነገር ግን ከአላህ ቃል የበለጠ አስፅናኝ የለምና በሱ ተፅናና ❗️❗️❗️

ይህ ነው ዱንያ ዛሬ ማግኘት ነገ ማጣት አንዴ መደሰት አንዴ መከፋት
ሁሉንም ለአላህ ስጠው ስብራትክን ሊጠግነው ሚችለው አላህ ነውና ወደ እሱ ሽሽ❗️

https://t.me/AbuEkrima


ሁሌም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው⤵️⤵️
               👇👇
         ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
📮💥 ዕውቀትን በመፈለግ ላይ መበርታት💥📮
                  
🔖 በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሐደራ።

🎙️ በኡስታዝ አቡ ሱፍያን ሙኽታር አላህ ይጠብቀው።

🕌 መስጂድ ረሕማን ዳለቲ

🗓 21/05/2015E.C

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/12606


✍️የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ‼️
     ===============

    🔘ወደ ሰላት ከመገባቱ በፊት

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሙሉ የሆነ ውዱእ ይደረጋል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ወደ ቂብላ ይቀጣጫል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ሰፍ ይስተካከላል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ማእሙኖች ኢማሙን ተከትለው ይቆማሉ።


       🔘የሰላቱ አሰጋገድ

✍️የመጀመሪያው ተክቢራ ይባልና…
ሱረቱል ፋቲሃ ይቀራል።
          {بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ}
     {الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
                 الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
                   مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
           إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
               اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
              صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ
         غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ}

ይህንን ሲጨርስ ሁለተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከሁለተኛው ተክቢራ በኋላ……
በነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳል።
«اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد»
ይልና ሶስተኛው ተክቢራ ይላል

✍️ከሶስተኛው ተክቢራ በኋላ……
ለሟቹ ዱዓ ያደርግለታል። ለምሳሌ ከመጡ ዱዓዎች መሃል……
«اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه،
   وأكرم نزله، ووسع مدخله، واغ
سله بالماء والثلج والبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس،
  اللهم أبدله دارًا خيرًا من داره، وأهلًا خيرًا من أهله،
  اللهم أدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، ومن عذاب النار، ووسع له في قبره، ونور له فيه»
ከዚህም ውጪ ያሉ ዱዓዎች የ
ቻለውን ያደርግለታል። ይህንን ሲጨርስ አራተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ…
ቲንሽ ዝም ይልና እዛው በቆመበት ወደ ቀኝና ወደ ግራው ያሰላምታል።
«السلام عليكم ورحمة الله,
       السلام عليكم ورحمة الله»
ይላል።


 
 
        🔘አንዳንድ ነጥቦች

💫ጀናዛው ከኢማሙ ፊት
ቀመጣል።
ጀናዛው የወንድ
ከሆነ;
   ኢማሙ ጭንቅላቱጋ ይቆማል።
ጀናዛው የሴት ከሆነ;
   ኢማሙ ወገቧ አካባቢ ይቆማል።

💫ባለው የሰጋጆች ብዛት ረዥም ሰፍ ከመስራት ይልቅ ሰፎቹ መብዛታቸው ይመረጣል።

💫አራቱንም ተክቢራዎች ሲባሉ እጅ ማንሳቱ የተሻለ የተወደደ ነው።

💫አንድ ሰው ኢማሙ የተወሰነ ከሰገደ በኋላ ደርሶ ወደ ሰላቱ ቢገባ የሚጀምረው ኢማሙ ከደረሰበት ቦታ ሳይሆን ከመጀመሪያው ቦታ ነው።
ለምሳሌ፦
ኢማሙ የሁለተኛው ተክቢራ ሲያደርግ ቢደርስ እሱ የሚያደርገው ሰለዋት ማውረድ ሳይሆን ፋቲሃን መቅራ
ት ነው; በመጨረሻ ኢማሙ ሲያሰላምት ቶሎ ቶሎ ብሎ ይጨርስና ያሰላምታል።

💫ጀናዛው የሆነ ቦታ ተሰግዶበት የተቀበረ ከሆነ ሌላ ቦታ "ሰላተል غይብ" ተብሎ አይሰገድበትም።

💫አንድ ሰው ሰላተል ጀናዛ ቢያመልጠውና መስገድ ቢፈልግ ጀናዛው ቢቀበር እንኳ ቀብሩ አጠገብ ሄዶ ይሰግድበታል።


        🔘ማሳሰቢያ

✏️ቀላል ከመሆኑም ጋ ብዙሃኖች የሚከብድ መስሏቸው ብዙ ጊዜ ከመስገድ ሲቆጠቡ ይታያሉና ሼር አድርጉላቸው።

  🤲አላመጨረሻችን አሳምሮ ይውሰደን🤲
         ✍ሐምዱ
ቋንጤ
              🕌ከፉርቃን ሰማይ ስር

                🔗 t.me/hamd
quante href='' rel='nofollow'>


👉ከወንጀል መጠበቅ👈

🔖 በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

ነሲሀው ላይ ከተነሱ ነጠቦች
👉አላህ የዋለልን ፀጋ ማመስገን እንዳለብን፤
👉 ወንጀልን ከመዳፈር መቆጠብ እንዳለብን፤
👉ኢስቲغፋር ማብዛት እንዳለብንና ሌሎችም ነጥቦች ተዳሰውበታል።

🎙️ በኡስታዝ አቡ ዓብዱልሀሊም ሸምስ አላህ ይጠብቀው።

📅 እሁድ 21/05/2015E.C 🗓️

🕌 በመስጂድ ረሕማን ዳለቲ

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/12604


እፍረት ለሴት ልጅ ዋና ንብረቷ ነው።
ልቅናዋም ክብሯም ያለው እፍረቷ ውስጥ ነው።

https://t.me/AbuEkrima


👉አንዲት የገጠር ነዋሪ በጭንቅንቅ ምክንያት ልጇ ይጠፋባታል ከዛም እየተጣራች ልጇን መፈለግ ጀመረች
  ይህን ያዩ ሰዎች እንዲህ አሏት ለምን ፊትሽን አትከፍቺም ሲያይሽ ወደ አንቺ ይመጣ ዘነድ❗️
   እሷም እንዲህ ስትል መለሰችላቸው
እፍረቴ(ሃያዬ) ከሚጠፋ ልጄ ይጥፋ ❗️

https://t.me/AbuEkrima


👌ፉደይል ኢብን ዒያድ (አላህ ይዘንለትና)
ልጁ በልብሱ ጫፍ የሚዛኑን ሰሃን ሲጠርግ ያየዋል:  ከዛም ለምን ይህን ታደርጋለህ ሲል ጠየቀው?

እንዲህም አለ፦ ለሙስሊሞች የመንገድ አቧራን እንዳልመዝንላቸው ስል አለው።

ፋደይል አለቀሰ ከዛም እንዲህ አለ፦
ልጄ ሆይ! ይህ ተግባርክ እኔ ዘንድ ከሁለት ሀጆች እንዲሁም ከአስር ዑምራዎች የበለጡ ናቸው።


أمة العظماء 336📚

https://t.me/AbuEkrima


💫ዱንያ ጀርባዋን ሰጥታ  ሄዳለች
አኼራ ደግሞ ፊቷን ሰጥታ መጥታለች
ለሁለቱም ልጆች አሏቸው
የአኼራ ልጆች ሁኑ የዱንያ ልጆች እንዳትሆኑ  ❗️
   ዛሬ ስራ ነው ምንዳ የለም ነገ ደግሞ ምንዳ እንጂ ስራ የለም❗️

👉ዓልይ ኢብን አቢ ጣሊብ
صحيح البخاري ، كتاب الرقاق
‏باب في الأمل وطوله
📚

ከፊል ሁከማዎች እንዲህ ይላሉ ፦ ጀርባውን ሰጥቶ ለሚሄደው ዱንያ ፊቱን የሰጠና ፊቱን ሰጥቶት ወደሱ ለሚመጣው አኼራ ጀርባውን የሚሰጥ አካል ያስገርማል።

https://t.me/AbuEkrima


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ቁርኣን 👉🌷የህይወት ስንቅ 🌷

https://t.me/AbuEkrima


ብዙዎቻችን የተዘናጋንበት ስለሆነው
               👇👇
         ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
🚫🚫ውሸትና ውሸተኞች አኼራ ላይ ምን እንደ ሚጠብቃቸው🚫🚫

🔖 በሚል ርዕስ የተዘጋጀ👉 እራሳችን ልንፈትሽበት የሚገባ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

ሙሀደራው ላይ ከተነሱ ነጥቦች መሀከል⤵️⤵️
👇
📮💥ውሸት የሙናፊቆች፣የኩፋሮች እንጂ የሙእሚኖች ባህሪ እንዳልሆነ፤    
📮💥 ግብይት ላይ ሰዎች ሀላል እንደሆነ ነገር በቀላሉ እንዴት እንደሚዋሹ፤ 
📮💥በትንሹ የተለመደ ውሽት መጨረሻው እንዴት እንደሆነ፤
 📮💥እንደ አጠቃላይ ሙስሊሞች በልዩ መልኩ ደግሞ ሰለፍዮች ከዚህ ባህሪ ሊጠነቀቁ እንደሚገባና ሌሎችም ስለ ውሸትና የውሸት አስከፊነት ተዳሰውበታል الله ሰምተው ከሚጠቀሙ ያድርገን።   

🎙️ በኡስታዝ አቡ ዐማር ዐብዱልዐዚዝ ቢን ፈረጃ አላህ ይጠብቀው።


💥 ሙሀደራ መስጂደ ረህማን ነው‼️

   ↪️ ልዩ
       ↪️ የዳዕዋ
           ↪️ፕሮግራም‼️


💥 በጉጉት እና በናፍቆት የሚጠበቀው ሳምንታዊው የሙሀደራ ፕሮግራም‼

🚦 ዳለቲ መስጂደ ረህማን ነው።

     🕌🕌 መስጂደ~ ረህማን 🕌🕌

  🗓️ እሁድ ጥር 21/ 2015E.C
 
📮 ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ይደረጋል።

🚙 ሰፊና አስተማማኝ ጥበቃ ያለው የመኪና ማቆሚያ አለ።

💥 ሁሉም ሰው ተገኝቶ እንዲሳተፍ ከወዲሁ ጥሪያችን እናስተላልፋለን‼️


↪️ መገኘት ምትችሉ ⤵️⤵️⤵️
🚧እ
    🚧ን
        🚧ዳ
            🚧ት
                🚧ቀ
                    🚧ሩ!!!


🔄 Play ▶️ ────◉ 07:10 AM
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል:-

🖥️ በ Telegram~Channel
📎 https://t.me/joinchat/PxPlMEUUkI0Q0MIx

🖥 በ Facebook~page
🌐 https://www.facebook.com/Al.Furqan.Islamic.Studio


የአላን ፀጋ ሁሌም ልናስታውስና ልናመሰግን ይገባናል ❗️❗️❗️

አንድ የኩላሊት ህመምተኛ በወር ውስጥ 15 ጊዜ የኩላሊት  ትጥበት ይደረግለታል ታዲያ በዚህ ወቅት ይህ ነው የማይባል ትልቅ ህመም ይሰማዋል።

ጤነኛ ሰው ግን ያለ ምንም ህመም በቀን 32 ጊዜ በተፈጥሮ ኩላሊቶቹ ይታጠቡለታል።

   👉 የአላህን ፀጋ ብትቆጥሩት አትዘልቁትም❗️

https://t.me/AbuEkrima


የአላን ፀጋ ሁሌም ልናስታውስና ልናመሰግን ይገባናል ❗️❗️❗️

አንድ የኩላሊት ህመምተኛ በወር ውስጥ 15 ጊዜ የኩላሊት ትጥበት ይደረግለታል ታዲያ በዚህ ወቅት ይህ ነው የማይባል ትልቅ ህመም ይሰማዋል።

ጤነኛ ሰው ግን ያለ ምንም ህመም በቀን 32 ጊዜ በተፈጥሮ ኩላሊቶቹ ይታጠቡለታል።

👉 የአላህን ፀጋ ብትቆጥሩት አትዘልቁትም❗️

https://t.me/AbuEkrima


የረጀብን ወር መፆም...

بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم.

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
በአላህ ስም እጀምራለሁ።

حكم صيام شهر رجب كاملاً

السؤال: ماذا على الذي يصوم شهر رجب كاملاً كما يصوم رمضان، وهذا السؤال من المستمع علي عثمان محمد؟

ጥያቄ ፦

የረመዳን ወር ሙሉ እንደሚፆመው የረጀብን ወር አሟልቶ የሚፆም ሰው ላይ ምን አለበት ?... ?

الجواب: صيام رجب مكروه؛ لأنه من سنة الجاهلية، لا يصومه، صرح كثير من أهل العلم بكراهته؛ لأن النبي ﷺ نهى عن صيام رجب، المقصود أنه من سنة الجاهلية، فلا، لكن إذا صام بعض الأيام يوم الإثنين، يوم الخميس لا يضر، أو ثلاثة أيام من كل شهر لا بأس، أما إذا تعمد صيامه فهذا مكروه.
المقدم: بارك الله فيكم

(فتاوى نور على الدرب)
لسماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله

መልስ ፦

የ"ረጀብ" ወር ፆም የተጠላ ነው‼️
ምክንያቱም ፦ የ"ጃሂሊያ" ፈለግ ነው !!! አይፁመው‼️አብዛኛዎቹ ዑለማዎች የተጠላ በመሆኑ ላይ ግልፅ አርገዋል።

ምክንያቱም ፦ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የ"ረጀብ"ን ወር ከመፆም ከልክለዋል።

የ"ረጀብ"ን ወር በመፆም የተፈለገበት የ"ጃሂሊያ"ን ሱና ነው‼️

አይቻልም (አይሆንም‼️)

ነገር ግን ሰኞና ሐሙስ እንዲሁም ከወሩ ሦስት ቀንን የመሰለ ከፊል ወቅት ቢፆም አይጎዳውም።ችግር የለውም።
ካልሆነ ግን አውቆ (ለመፆም) አስቦበት
ከሆነ የተጠላ ነው።

ፕሮግራም አቅራቢ ፦ (( አላህ ረድሄቱን ይስጦት !!! ))

(ኑሩን አለ-ደርብ)

"ሰማሓቱ ሸይኽ ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላ ቢን ባዝ

📝 … ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/amr_nahy1


ረጀብ ወርን በተመለከ ነብዩ ﷺነጥለው የሚሰሩት አምልኮ ነበረ?

አሁን ያለንበት ወር ረጀብ ይባላል ይህ ወር ከአራቱ ከተከበሩ ወራቶች ውስጥ አንደኛው ነው። አራቱ የተከበሩ ወራቶች የሚባሉት፦ ዙል ቂዕዳ፣ ዙል ሂጃ፣ ሙሃረምና ረጀብ ናቸው።
አላህ እንዳለው ፦ {የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መፅሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ወቅት አስራ ሁለት ወር ነው። ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው}። (ተውባ :36)

በዚህ ወር ላይ ሰላት ማብዛት ፣ መፆም አዝካርን በተመለከ የወረዱ ሀዲሶች አሉ ነገር ግን ሁሉም ደዒፍ( ደካማ) ሀዲሶች ናቸው ለመራጃ አይሆኑም። ማስረጃም ሱናም አይደግፋቸውም

ሚደግፋቸው ነገር ቢኖር እንኳን ይህ ረጀብ ወር ነውና መልካም ስራ ላብዛ ሰለቴ ላይ ልጨምር ዚክሬ ላይ ልጨምር ሊል አይገባውም አይቻልለትም።

ምክንያቱም ነብዩ ይህን ወር አግኝተውታል ። ታዲያ ነብዩ የጨመሩት ነገር አለን? በጭራሽ❗️ስለዚህ ነብዩ ያልጨመሩት ነገር እኛ የተከበረ ወር ነውና እንጨምራለን ማለት አንችልም! ምክንያቱም እኛ ተከታዮች እንጂ አዲስ ነገር ፈጣሪዎች ስላልሆንን።
አንድ ሰው ወደ አላህ በሚያቃርበው ስራ ላይ ስሜቱን እንዲሁም ፍላጎቱን{ ከተከተለ እምነት አልባ ይሆናል ምክንያቱም ስሜቱን ስለሚከተል።

አለህ በርግጥ እንዲህ ብሏል፦
{ ከአላህም የሆነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም}።
( ቀሰስ: 50)


ስለዚህ በእኛ ላይ ያለው ነገር ምንድን ነው ይህን ወር አላህ እንዲሁም ነብዩ ይሄን አድርጉ ብለው በነጠሉት ነገር ቢሆን እንጂ መነጠል አይቻልም

ነገር ግን ይህ የተከበረ ወር በመሆኑ ምክንያት አላህ ራቁ ያለውን ነገር ልንርቅ ይገባል። በዚህ ወር ላይ ከካፊሮች ጋር ግድያ አይቻልም ።
በዚህ ወር ላይ መጋደል ክልክል ነው እነሱ በግድያ እስካልጀመሩን ድረስ ወይም ደግሞ ተከታታይ ግድያ ኖሮ እስከዚህ ወር ድረስ ከዘለቀ በዚህ ጊዜ ይቻላል ማለት ነው።

📚ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን

https://t.me/AbuEkrima


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
يجب على المؤمن ان يكون خلقه القران

للإمام ابن باز رحمه الله


💫አባታችን አደም ወንጀልን በሰራ ጊዜ  ወዲያው ምህረትን ጠየቀ ጌታውም ተውበቱን ተቀበለው መረጠውም ቅኑንም መንገድ መራው።

      ሸይጣን ደግሞ በአመፁ ላይ ችክ አለ ተኩራራ፣ በቀደርም አሳበበ።   አላህም ረገመው ከራህመቱም አራቀው። ❗️

   ተውበት ያደረገ 👉ሰውኛ ባህሪን ይዟል

በወንጀሉ ላይ የፀና በቀደር ያስተባበለ ሸይጣናዊ የሆነን ባህሪ ይዟል።

     እድለኞች አባታቸውን አደምን ይከተላሉ።
    
       እድለቢሶች ደግሞ ጠላታቸው ሸይጧንን ይከተላሉ ❗️❗️❗️

📚መጅሙዑል ፈታዋ
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ

https://t.me/AbuEkrima


በአሁኑ ሰኣት ስማርት ስልኮችን ለመጠቀም ሁለት ወሳኝ ነገራቶች ያስፈልጋሉ

① ሹብሃቶችን ሊገፈትርበት የሚያስችል እውቀትና
② የአላህ ፍራቻ

ሸይኽ የህያ حفظه الله


👉ኢማሙ አህመድ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ

አንድ ሰው በእጁ ላይ አንድ ሺ ዲናር እያለው ዛሂድ(ዱንያን ችላ ያለ) ሊባል ይችላል?

አዎን ነገር ግን በሸርጥ እሱም ገንዘቡ ሲጨምር ላይደሰት ሲጎድልም ላያዝን
👌

مدارج السالكين📚

https://t.me/AbuEkrima

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

344

obunachilar
Kanal statistikasi