Astroግእዝ🌼


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


በዚህ ቻናል የአለማዊውን እውቀት ከመፈሳዊው ጋር አንድ ላይ የምንማርበት ፣ የምንወያይበት ፣ ሃሳብ የምንሰጥበት ፣ የምንከራከርበት ቦታ ነው ።
ቻናላችንን ከፈለጉ👇
https://t.me/+dlws8CVu41EwMzY8
ግሩፓችንን ለመቀላቀል👇
https://t.me/+7ngf8crgEEdiOWFk
የዩቱብ ቻናላችንን ከፈለጉ👇
youtube.com/@Astrogeez
በግል ከፈለጉኝ @Astrogeez1

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


'አንድ አንዴ ትርጉማቸውን ሳናውቅ በልምድ አሜን ብለን የምንቀበላቸው ቃላቶች አሉ ' አለኝ አንድ ጓደኛዬ ። እንዴት አልኩት ያው ሁልጊዜ መፈላሰፍ ስለሚወድ አሁንም ፍልስፍናው ሊጀምረው ነው ብዬ እያሰብኩ ። ቢሆንም ግን ፍልስፍናውን እወድለታለው ፣ ብዙ ያላስተዋልኩትን እና ያላየሁትን ነገር እንዳይ እና እንዳስተውል ያደርገኛል ። ፍልስፍና ስለሚወድ ነው መሰለኝ ስሙ በእውቀቱ የተባለው ። ስሙን መልአክ ያወጣዋል 😁 ። 'ለምሳሌ እስኪ ልጠይቅህ ' አለኝ ትንሽ ፊቱን ኮስተር አድርጎ 'ተቃራኒ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው እስኪ ንገረኝ ' አለኝ ። ጥያቄዎቹን ከየት እንደሚያመጣቸው ባላውቅም ነገር ግን ሁሌም ግራ እንድጋባ ያደርገኛል ። የዛሬው ግን ለየት ያለ ነው ። 'ምን ማለትህ ነው አልኩት ' ጥያቄው ቢገባኝም ምን መመለስ እንዳለብኝ ስላላወኩ ። 'እየውልህ ዛሬ ወዳጄ ተገኝ መጣና ስራዬ ጠመመብኝ አለኝ ከዛም እኔ አንተ ስለጠመምክበት ነው አልኩት እየቀለድኩ ። አርሱ ግን አምርሮ ለምንድን ነው ሁሌ ተቃራኒ የምትሆነው ብሎኝ ጥሎኝ ሄደ ። ከዛም ተቃራኒ የሚለው ቃል ጆሮዬ ገብቶ ትርጉሙን እየፈልኩ ነው ' አለኝ ። 'በለው' አልኩኝ በውስጤ አሁን ምን ልመልስለት በሚል ውስጤ እያብሰለሰለ ። 'አላውቅም እስኪ ንገረኝ ' አልኩት የምር መልሱን ስላላውኩት ። 'እየውልህ እስኪ ተቃራኒ የሆኑ ነገሮች ንገረኝ ' አለኝ ። 'ብርሃን እና ጨለማ' አልኩት ሃሳቤ ላይ በፍጥነት የመጣውን ። 'ጥሩ ። አሁን ጨለማ እና ብርሃንን ካየሃቸው የአንዱ መኖር ሌላኛውን ያጠፋዋል ። የአንደኛው መጥፋት ደግሞ ሌላኛውን እንዲኖር ያደርገዋል ። አሁን የሰጠኧኝን ምሳሌ ብናይ የብርሃን መኖር ጨለማን ያጠፋዋል ። የብርሃን አለመኖር ደግሞ ጨለማን ያኖረዋል ' ሲለኝ 'ስለዚህ የተቃራኒ ትርጉሙ የአንዱ መኖር ሌላኛውን እንዳይኖር ማድረግ ነው ማለት ነው? ' አልኩት ሃሳቡን በትክክል እንደተረዳሁት ለማሳየት ። 'በትክክል ። ተረድተኧኛል ። ግን አሁንም ትክክል አይደለንም ። ለምን ብትለኝ አንድ ምሳሌ ልጨምርልህ ' አለኝ ። 'ማወቅ እና አለማወቅ ተቃራኒ ናቸው ። ነገር ግን የአንዱ መኖር ሌላኛውን አያጠፋውም ። አንድ ሰው አወቀ ማለት የማያውቀው የለም ማለት አይደለም ። ስለዚህ ተቃራኒ ለሚለው ቃል ሌላ ትርጉም ልንሰጠው ያስፈልገናል ። ' አለኝ ። እውነቱን ነው ። ታያ ተቃራኒ የምንለው ምንድን ነው ብዬ እራሴን ጠየኩት ። አሁንም ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁለት ወደርሱ ተመልሼ 'ታዲያ ትርጉሙ ምን ይሆናል አልክ አልኩት' ምን ሊመልስ ይችላል ብዬ በማሰብ ። 'ያንተን ባላቅም እንደኔ ግን ተቃራኒ የሚለውን ለሁለት ከፍለን ማየት እንዳለብን ይሰማኛል ። የመጀመርያው የመጠፋፋት ተቃራኒ የምንለው ሲሆን ይህ የተቃራኒ አይነት አንዱ ሲኖር ሌላኛው እንዳይኖር ያደርገዋል ። ሌላኛው አይነት ደግሞ የመረዳዳት ተቃራኒ ነው ። ይህ አይነቱ አንዱ መኖሩ ሌላኛው እንዳይኖር አይከለክለውም ።' አለኝ ። 'ቆይ ስማቸውን እራስህ ነህ ያወጣሃቸው?' አልኩ እየሳኩ ። 'ባክህ ማህበረሰቡ ሃሳቤን ከተቀበለው የተሻለ ስም እሰጣቸዋለው ። ለጊዜው ግን በዚህ እንቀጥላለን ።' 'ጥሩ ሃሳብ ታመጣና አሰያየሙ ላይ ትቸገራለክ ።'አልኩት ንግግራችንን ለመጨረስ እያልኩ ። 'ያው ሰው ሙሉ ሆኖ አይሆን ። አንድ ነገር ሲኖረው አንድ ነገር ይታጣበታል ። ደግሞ የመጨረሻ ነገር ስለ ተቃራኒ ነገር የተፈላሰፍኩትን ልንገርክ ።' ሲለኝ ሎሚ የመጠጠ ሰው የሚያሳየውን ፊት ያዝኩ። አሁን ጨረስኩ ስል ድጋሜ ሌላ ሃሳብ ሊያነሳ ነው አልኩ ። እርሱ ግን ቀጠለ ። 'የሚገርምክ ነገር ደግሞ ያለተቃራኒ የተፈጠረ ነገር የለም ። ሁሉም የየራሱ የሆነ ተቃራኒ ነገር አለው አለኝ' ። እርፍ ደግሞ ምን የሚሉት ነው ይሄ ? ሁሉም ነገርማ ተቃራኒ የላቸውም ። ይህን እርግጠኛ ነበርኩ ነገር ግን ከርሱ ቶሎ ለመላቀቅ እንዲቀጥል ዝም አልኩኝ ። 'ይኧውልህ እኛ አላስተዋልነውም እንጂ ሁሉም ተቃራኒ ነገር አላቸው ። እንዲያ ባይሆንማ 'balance'የሚባለው ነገር ይጠፋል ። ምሳሌ ልስጥክ :- ቅጠላ ቅጠል ለሚበላ ሁሉ ስጋ በሊታ አለው ። ስጋ ለሚበላው ሁሉ ሌላ ስጋ በሊታ አለ ። ለመኖር ሞት አለ ፣ ለመወለድ መቀበር ፣ ለሃዘን ደስታ ፣ ለማግኘት ማጣት ፣ ለጥሩ መጥፎ ፣ በሳይንሱ እራሱ ለacid base ፣ለmatter antimatter ፣ ለመደመር መቀነስ ፣ ለderivate integration አለው ። እንደኔ ሃሳብ ተቃራኒ የሌለው ነገር DOMINATOR (CREATER) ፣ መሆን አለበት እርሱም ፈጣሪ ብቻ ነው ። 'ሲለኝ 'በል ወንድሜ እንደዚ ነገር አይነካካኝ ደና ሁን ' ብዬ ተሰናብትኩት ። ሃሳቡ ትንሽ የሚያሳምን ቢሆንም ሁሉም ተቃራኒ አለው የሚለው ስላሳመነኝ ተቃራኒ የሌለውን ነገር በሃሳቤ መፈለግ ጀመርኩ ...

@AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ጓህለወ = ሸነገለ

@AstrogeezChannel


በድሮ ጊዜ ፣ የሰአት መቁጠርያ ባልነበረበት ፣ ሰዎች ጊዜን እንዴት እንደሚቆጥሩ እጅግ ያስደንቃል ። እስኪ ይህችን እዩዋት 👆

@AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ከወወ = ፈጠነ

@AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ልህቀ = አደገ

@AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ጸውአ = ጠራ

@AstrogeezChannel


ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ ቤተሰቦች 🙌

✅ከዛሬ ጀምሮ እንደ እግዝአብሔር ፈቃድ በየቀኑ አንድ አንድ የግእዝ ቃላት ከነትርጉማቸው ለመልቀቅ አስብያለው ። ብዙ ነገር ሳለን እኛ ግን ለማወቅ ጥረት ስናደርግ አንታይምና ላም አለኝ በሰማይ እንዳይሆን ነገሩ ድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል 🙌

@AstrogeezChannel


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ይህ ነገር Physics ላይ የተማርነውን ህግ ይጥሳል?🤔

@AstrogeezChannel


የሰው ልጅ በእድሜ ዘመኑ 3 ጊዜ ህፃን ይሆናል ይላል አንድ መፅሃፍ 😁 ። የመጀመርያው ገና እንደተወለደ ሲሆን ሁለተኛው ሲሸመግል ነው ። የሰው ልጅ በስተሽምግልናው ዘመኑ የህፃን ባህሪ ተመልሶ ይላበሳል ፣ በትንሹ ያኮርፋል ፣ ተመልሶ ይረሳና ይቅር ይላል ፣ እንደ ህጻናት ጣፋጭ መውደድ ይጀምራል ... (ይህንን የምታነቡ አዛውንት ካላችሁ ይህ እናንተን ለማዋረድ የተፃፈ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ የሚገልጽ እንደሆነ ይታሰብልኝ ፣ ማን ህፃናትን የማይወድ አለ? እንደ ህፃናት መሆን ደግሞ ትልቅ ጸጋ ነው ።) የሚያስገርመው ግን 3ኛው ነው ። የሰው ልጅ ህፃን ከሚሆንባቸው 3ኛው ደግሞ በወጣትንነት ዘመኑ ነው ይላል 😂 ። እንዴት ቢሉ ፍቅር ሲይዘው 😭 ። እኔ እርግጠኛ አይደለሁም 🙌 ። እንደ መፅሃፉ ከሆነ ሰው በፍቅር ከተያዘ በኋላ እንደ ህፃን act ማድረግ ይጀምራል ። በራሱ ዓለም ይወጣል ይወርዳል ፣ ለብቻው ይስቃል ፣ ያለቅሳል 🤷‍♂️ ፣ በትንሹ ነገር ቶሎ ይበሳጫል ፣ ምግብ ተገዶ ነው የሚበላ💀 ፣ ትእግስት ያጣል ... (እንዴት እንዳትሉኝ ፣ እኔ እራሱ ገርሞኝ ነው የምጽፍላችሁ)... ። ለማንኛውም ወደ ህፃንነት ከሚቀይር ፍቅር ይሰውራችሁ ። ፍቅር ትእግስትን ይጨምራል እንጂ አያስጨርስም ፣ ፍቅር ማስተዋልን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም ፣ ፍቅር በሁሉ ተስፋ ያስደርጋል እንጂ በትንሹ ተስፋ አያስቆርጥም (፩ ቆሮ. ፲፫፥፬-፰) ።

ሠናይ ጊዜ ❤️

@AstrogeezChannel


ይቅርታ ወገኖቼ ከላይ የሰራሁት ለስልክ አይሰራም ። አሁን ግን አስተካክየዋለሁ 😁🙏

https://astrogeezmain.github.io/Astrogeez2.github.io/

@AstrogeezChannel


ማንኛውም ቀን ፣ ወር እና ዓመት ኖሮን ግን ዕለቱ ምን ላይ እንደዋለ ለማውቅ የሚረዳ website ነገር ሰርቻለው ። አሰራሩን እናንተም ለማውቅ ከፈለጋችሁ እዛው website ላይ አለ ። ነገር ግን አስራሩ ካልገባችሁ ችግር የለውም ( Normal ነው 😁) ። እዚህ አንድ ላይ እንዴት እንደሚሰራ በሚገባ መልኩ አሳያችኋለው 🙏

https://astrogeezmain.github.io/Astrogeez1.github.io/

ሠናይ ጊዜ ❤️
@AstrogeezChannel


ወንድሞችና እህቶቼ እንደምን ሰንብታችኋል ።

ለሰውነታችን ምግብ መርጠን እንደምንበላ ሁሉ ለጭንቅላታችንም እየመረጥን እውቀት ልንሰጠው ያስፈልጋል ። በአሁኑ ሰአት የታዘብኩት ነገር ቢኖር አሁንም ቢሆን ኦሾ የሚባል ሰው ያወጣውን መፃህፍት የሚያነቡ ብዙ ሰዎች አሉ ፣ እና ይሄም በጣም ያሳዝነኛል ። ሰውዬው እባብ ነው ። ጥሩ ምክር እያስመሰለ ብዙ ሰዎችን አስቷል ከሃይማኖት መስመር አስወጥቷል ፣ ከሰውነት ጎዳና አፈናቅሏል ። ስለዚህ እናንተም ወገኖቼ ከእንደዚህው አይነት ሰውም ሆነ እሱ ከፃፋቸው መፅሃፍት ልንለይ ያስፈልጋል ።

ሠናይ ጊዜ ❤️
@AstrogeezChannel




🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌹እንኳን ለአዲሱ ፳፻፲፯ ዓመት በሰላም ፣ በጤና ከነመላው ቤተሰባችሁ በሰላም
አደረሳችሁ 🥳 በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣ የአንድነት በዓል ያድርግልን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


⭕️እርግጠኛ ነኝ ይህን ምስል አይታችሁት ታውቃላችሁ ።

👉ነገር ግን ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?
👉ምን እንደሰራስ ስንቶቻችን እናውቃለን?

✅ስሙ ቼ ገቫራ ይባላል ። አርጀንቲናዊ ሲሆን ይህ አሁን የምናየው ምስል በዓለም እጅግ ተወዳጅ ምስል ተብሎ የተነገረው ምስሉ ነው ። የሰራው የማይሻር ታሪክ በትንሹ ፅፎ መጨረስ ስለማቻል በቀጣይ በሰፊው እንመለከተዋለን 🙏


🌹ወርሃ ጳጉሜን🌹

✅የኛ ብቻ የሆነችው
✅ሌላ ዓለም ላይ የማትገኝዋ
✅ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት
✅የቤት ኪራይ የማንጠየቅባት 😁
✅በረከትን የምናገኝባት
✅ለኢትዮጵያ ብቻ የታደለችው

🥳 እንኳን ለወርሃ ጳጉሜን በሰላም አደረሳችሁ 🙏 🥳

@AstrogeezChannel


👉 2016 ዓ.ም ላይ አይደለንም ?

🛑 ሁላችንም 2016 ዓመት ላይ ነን ብለን እናስባለን ፣ ነገር ግን ያ ትክክል ነው ?🤔

‼️ በባሕረ ሐሳብ ትምህርት መሰረት 2 አይነት አቅጣጠር አሉ ። አንደኛው የፀሐሃይ ሲሆን ሌላኛው የጨረቃ አቆጣጠር ነው። እኛ 2016 ዓ.ም የምንለው በፀሐይ አቆጣጠር ነው እንጂ በጨረቃ አቆጣጠር 2077 አመት ላይ ነን ። ስለዚህ በቀጣይ 2016 ዓ.ም ስንል በፀሐይ አቆጣጠር መሆኑን መዘንጋት የለብንም ።




መዝገበ ቃላት (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ).pdf
57.3Mb
የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ለሌለው 👆

@AstrogeezChannel


መልካም ጥያቄ ነው በመጀመሪያ መታረም ያለበት .....

[ ዓመተ ፍዳ + ዓመተ ምህረት = ዓመተ ዓለም ]

ወደ ነገሩ ስንመጣ እውነት ነው ጌታ የተወለደው መጋቢት 29 ቀን ነው የድህነት ጅማሬ ነውና ዓመተ ምህረት ተሰኝቷል እንደ ሃገራችን በመጋቢት ለምን የመጀመሪያ ወር አልሆነም ከሆነ ቀድሞ ከስያሜው ትርጉም ነው ምንነሳው ...

መስከረም የሚለው ቃል "ከረመ" ከሚል የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን (መሰስ ከረመ) ይለዋል ይህም ክረምቱ የማለፉን ነገር የሚናገር ነው አንድም "መዘክረ ዓም" ይለዋል ይህም የዓመት መታወሻ ማለት ነውና ።

የፀሐይ እና የጨረቃ ዑደት ታይቶ አበቅኔት ተሰልቶ የተገኘ እንጂ በዘፈቀደ የተሰራ አይደለም ቀደምት አባቶች ለአንድ ነገር ስያሜ ሲሰጡ ያለ ምክንያት መሆኑን እንረዳለን ።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.