Astroግእዝ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, Ruscha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በዚህ ቻናል የአለማዊውን እውቀት ከመፈሳዊው ጋር አንድ ላይ የምንማርበት ፣ የምንወያይበት ፣ ሃሳብ የምንሰጥበት ፣ የምንከራከርበት ቦታ ነው ።
ቻናላችንን ከፈለጉ👇
https://t.me/AstrogeezChannel
ግሩፓችንን ለመቀላቀል👇
https://t.me/AstrogeezGroup
በግል ከፈለጉኝ @Astrogeez

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, Ruscha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🎁 ደቂቃው ሳይሞላ ኑ ተቀላቀሉ እንዳያመልጣችሁ
🏃🏃
Request to JOIN👇👇


📌 ይቅርታ ቤተሰቦቼ

👉 ሰሞኑን ባለሁበት ሁኔታ ጊዜ ስላጣሁኝ እዚህ ቻናል ላይ ለትንሽ ጊዜ መልቀቅ አቆማለሁ 😔🙏

👉 ነገር ግን አታስቡ ፣ ስንመለስ በበለጠ አዳዲስ እና በአስገራሚ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንቀጥላለን 😁🙏 ።

👉 ከናንተ ብቻ የሚጠበቀው ይህችን ቻናል አለመልቀቅ ብቻ ነው 🙏🙏🙏 ። ያለ እናንተ ቻናሉ ባዶ ነውና የቻናሉ ድምቀት የሆናችሁ እናንተን ማጣት ይከብዳል 🙏 ስለዚህ አትልቀቁ 🙏

👉 በቀጣይ ስንገናኝ ስለምን ርዕሰ ጉዳይ እንድንወያይ ትፈልጋላችሁ ? ከስር Comment ስር ላይ አስቀምጡልኝ ።

🫡 መልሰን እስክንገናኝ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ 🙏


👀 ሞክሼ ፊደላት ቃላትን ሲያበላሹ ክፍል ሁለት😬


👉 አንድ ሰው :- ምግቡ ስላለቀ ለሥብሐት እንነሳ

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- 😂😂😂

👉 አንድ ሰው :- ምንድን ነው የሚያስቀው ?

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- ሥብሐት አይባልም ስብሐት እንጂ ። ሥብሐት ማለት ሠብሐ ከሚለው ቃል የመጣ ነው ። ሠብሐ ማለት ሠባ ፣ ደነደነ ፣ ጮማ ሆነ ማለት ነው ። ስለዚህ ሥብሐት ስትል መስባት ፣ ሥብነት እያልክ ነው 😂 ። ነገር ግን ስብሐት ሲል ሰብሐ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን ሰብሐ ማለት አመሰገነ ፣ አከበረ ማለት ነው ። ስለዚህ መጠቀም ያለብህ ትክክለኛው ቃል ስብሐት የሚለውን ነው ።

___________________________________________________


👉 አንድ ሰውዬ :- ዛሬ መምሕራችን መጥቷል እንዴ ?

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- 😂😂😂

👉 አንድ ሰው :- ምነው ትስቃለህ ፣ ችግር አለ እንዴ ?

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- መምሕራችን ማለትህ አስቆኝ ነዋ 😂 ። መምሕር አይባልም መምህር እንጂ ። መምሕር ካልክ መሐረ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው መሐረ = ይቅር አለ ማለት ነው ። መሐረነ አብ ሲባል ሰምተህ አታውቅም ? መሐረነ አብ ማለት አብ ማረን / አባት ማረን እንደማለት ነው ። ነገር ግን መምህር ካልክ መሀረ ፣ አስተማረ ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን መምህር = አስተማሪ ማለት ነው ።

______________________________________________________


👉 አንድ ሰው :- የመጀመርያው ሰው ዐዳም ባያጠፋ ኖሮ እዚህ አንገኝም ነበር ።

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- 😭😭😭

👉 አንድ ሰው :- ምነው ?

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- አጻጻፍህ ትክክል አይደለም ።

👉 አንድ ሰው :- ምኑ ጋር ነው የተሳሳትኩት ?

👉 ግእዝ የሚያውቀው ሰውዬ :- ዐዳም ተብሎ አይፃፍም ። ዐዳም ካልክ ዐደመ የሚለውን የግእዝ ቃል እየተጠቀምክ ነው ማለት ነው ። ዐደመ ማለት ደግሞ ሤራ አሴረ ማለት ነው ። ዐድማ ሲባል ሰምተህ ከሆነ የቃሉ ትርጉም እራሱ ሤራ ፣ ተንኮል ፣ ወጥመድ ማለት ነው ። ደግሞም ዐደመ ጊዜ ቀጠረ ፣ ቀን ወሰነ ተብሎም ይተርጎማል ። ዕድሜ የሚለው ቀጠሮ ፣ የተወሰነ ጊዜ ማለት ነውና ። ነገር ግን አንተ መጠቀም ያለብህ አዳም የሚለውን ነው ። አዳም ማለት አደመ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን አደመ ማለት በራሱ ውብ ፣ ያማረ ፣ ደስ የሚያሰኝ ፣ መልከመልካም ማለት ነው ። አዳምን እንደምታውቀው እግዚአብሔር ሲፈጥረው ውብ ፣ ማራኪ ፣ ያማረ አድርጎ ነው የፈጠረውና አዳም ተባለ ።


------- Telegram Channel -------

👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

የውሀ = ተሞኘ

@AstrogeezChannel


አንድ አዛውንት ገበሬ እና አንድ ወጣት ፕሮፌሰር በባቡር ጉዞ ላይ ይገናኛሉ። በጉዞው የተሰላቸው ፕሮፌሰር ጊዜ ማሳለፊያ እንዲሆናቸው በማሰብ ከገበሬው ጋር አንድ ጨዋታ ለመጫወት ይወስናል።

ፕሮፌሰሩም የጨዋታውን ህግ ለገበሬው አብራራ "ጥያቄ እጠይቆታለሁ፤ መልሱን ካላወቁ 5 ብር ይሰጡኛል። ከዛ እርሶም ጥያቄ ይጠይቁኛል፤ መልሱን ካላወኩት 500 ብር እሰጦታለሁ።"

ገበሬው በእሺታ አንገታቸውን ነቀነቁ።

ፕሮፌሰሩ: "በምድር እና በጨረቃ መካከል ያለው ርቀት ምን ያህል ነው?"

ገበሬው: በዝምታ ከኪሳቸው 5 ብር አውጥተው ከሰጡት በሗላ ጥያቄያቸውን አስከተሉ "ተራራ ሲወጣ አራት እግር ሲወርድ ደግሞ ሶስት እግር ያለው እንሰሳ ምንድን ነው?"

ፕሮፌሰሩ ደነገጠ! ምክንያታዊ የሆነ መልስ አሰበ፤ ስልኩን ጎሩጎረ ግን መልስ ማግኘት አልቻለም። በመሸነፍ ስሜት ቅጣቱን 500 ብር ለገበሬው ሰጣቸው።

ገበሬውም ብሩን ተቀብለው ምንም ሳይሉት ጋደም ይላሉ። የሽንፈት ስሜት እና መልሱን የማወቅ ጉጉት ውስጡን የበላው ፕሮፌሰር እንደ መበሳጨት እያደረገው "እና እንሰሳው ምንድን ነው?" ሲል ገበሬውን ይጠይቃል።

ገበሬውም ለአፍታ በምጸት ፈገግታ ካስተዋሉት በሗላ...አምስት ብር ሰጥተውት መልሰው ጋደም አሉ።

ትዕቢት የውድቀት መጀመሪያ ነው! ትልቅ ነገር አውቃለሁ ብሎ የሚታበይ ትንንሽ ነገሮችን ለማስተዋል አይቻለውም።

ትህትና የዕውቀት መጀመሪያ ነው !

------- Telegram Channel -------

👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ከልሐ = ጮኸ

@AstrogeezChannel


እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዐመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ❤️

@AstrogeezChannel


💀 ግጥም በAI 💀

✅ ክቡራት እና ክቡራን የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁልን ፣ በሰሞኑን እጅግ አስገራሚ ዜና ተሰምቷል !

✅ እንደምናቀው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለው AI ፣ Chatgpt እንደሆነ እናውቃለን ። ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ለኛ ለኢትዮጵያውያን በአማርኛ ብንጽፍለት የተበላሸ ፣ የተቆራረጠ አማርኛ ነው የሚጽፍልን ።

🛑 በሰሞኑን የተሰማው AI ግን ከዚህ ለየት ይላል ፣ እንደ Chatgpt እንግሊዘኛ ቋንቋ ሲቀበል ፣ ከሌሎቹ AI ግን የሚለየው አማርኛን በትክክለኛው መንገድ ፣ በስርዐት መመለስ መቻሉ ነው ። እንግዲያውስ ስሙ ማን ይባላል ካላችሁኝ DEEPSEEK ይባላል ።

😁 ከላይ እንደምታዩት ሁለቱንም ግጥም እንዲገጥሙልኝ ነግሬያቸው ነበር 😂። የትኛው የተሻለ ግጥም እንደጻፈ ፣ ፍርዱን ለናንተ ይሆን ዘንድ ከታች የሁለቱንም ግጥም አስቀምጬላችኋለው ።

CHATGPT

ለአባቴ የልቤ መልዕክት
አባቴ ሆይ ብርሃኔ፣ የህይወቴ ተስፋ፣
በእርስዎ ጥበብ ውስጥ ተንገድላለሁ በረከት ሆኜ በማ፣
እንደ አንበሳ የልብህን ጠንካራነት እያየሁ፣
ለቤተሰብ ተድላ ነበርህ፣ ለልጆችህ ታላቅ መብራት።

እንባዬን በእጅህ አጽዳህ፣ ሥቃዬን በልብህ ተሸከምህ፣
የህይወቴ የመጀመሪያ አስተማሪ አንተ ነህ፣
በቃልህ ሳልኖር ለዘላለም በምስጋና እኖራለሁ።

እስከ ፍጻሜ ድረስ ለዘላለም ይህን እላለሁ፤
አባቴ ሆይ፣ ወድዴ የሚያልፍህ የለም።

DEEPSEEK

ለአባቴ

አባቴ ማንቺው ነህ፣ ጠላት ቢያባርርህ፣
በልቤ ውስጥ ሁልጊዜ አንተ ነህ።
እጅህ በረከት፣ ልብህ ሰላም፣
በጨለማ ውስጥ አንተ ነህ ብርሃን።

የትም ብኼድ፣ የትም ብቆም፣
አንተ ትረሳኝ አትችልም።
አባቴ ማንቺው ነህ፣ ምስጋናዬ ነህ፣
በሕይወቴ ውስጥ ሁልጊዜ አንተ ነህ።

📌 ይህ ነገር ማስታወቂያ አይደለም ! ለጠቅላላ ዕውቀት ይሆን ዘንድ እንጂ !

------- Telegram Channel -------

👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel
👉 @AstrogeezChannel




❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ረምየ = ወጋ

@AstrogeezChannel


ዛጉዌ ምን ማለት ነው 🤔

✨ ዛጉዌ የሚለው ቃል አንድአንድ ሰዎች እንደተረጎሙት "ዘአገዌ" ከአገው ማለት ነው ። ደግሞ ሌሎችሁ እንደተረጎሙት በግእዝ ቋንቋ ጐየ ሸሸ ማለት ነውና ድልነዓድ የተባለውን የዛን ጊዜ የነበረ ንጉሥ ስላባረረ "ዘአጉየየ" ትርጉሙም ያባረረ ፣ ያሸሸ ማለት ነው ይላሉ ።

@AstrogeezChannel


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ኖኀ = ረዘመ

@AstrogeezChannel


በዚህ ቻናል ላይ የቆዩም ሆነ አዳዲስ የሆኑ የተለያዩ መፃህፍት በPDF መልክ ያገኛሉ ። ሌላ ቦታ ሊገኙ የማይችሉ መጻሕፍትም ጭምር የሚለቀቁበት ቻናል ነው 👍።

👇👇👇
@Yemesahft_Alem
@Yemesahft_Alem


መፅሐፈ ጥበብ ወዕፀ ደብዳቤ.pdf
54.0Mb
📚ርዕስ:- መፅሐፈ ጥበብ
📝ደራሲ:- ድድቅ ወልደማርያም
📖የገፅ ብዛት:- 261
📅 ዓ.ም :- 2016

📌ማጋራት አይዘንጋ!
@Yemesahft_Alem
@Yemesahft_Alem
@Yemesahft_Alem


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ቄሐ = ቀላ

@AstrogeezChannel


😁🙌 ከሁሉም በበለጠ ደስ የሚላችሁ የትኛው ነው ?
So‘rovnoma
  •   ታሪክ
  •   ጥንታዊ ጥበባት
  •   ፍልስፍና
  •   ቋንቋ እና ባሕል
  •   ሌላ
32 ta ovoz


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ነዝኀ = ረጨ

@AstrogeezChannel


የማለዳ ብስራት dan repost
አቡንቱ (Ubuntu)

   በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ የገጠር መንደሮች አንድ አስገራሚ ባህል አላቸው። አንድ ሰው ስህተት ሲሰራ በዛ መንደር ቅጣት የለም። ሞራል የሚነካ ስድብ፣ ቅስም የሚሰብር ንግግር፣ ማግለልና መድሎ፣ ከጀርባ ሆኖ በሃሜት የሰው ስጋ መብላት የሚባል ነገር የለም።

     ስህተት የሚሰራ ሰው ግን በአንፃሩ በገጠሩ ሰው ይከበብና ለሁለት ቀናት ያህል ከዚህ በፊት የሰራቸው መልካም ነገሮች በሙሉ ይነገረዋል። በእነሱ እምነት ሁሉም ሰው መልካም ነው። አንዳንዴ ግን ስህተት ይሰራል። ስህተት ሲሰራ ይላሉ፤ መልካሙን ማንነቱን ብናስታውሰው ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር ይገናኛል ይላሉ። ይህም ተግባር አቡንቱ (Ubuntu) ተብሎ ይጠራል። ለዘመናት የቆየ የመኖር ጥበብ።

የሰውን ልጅ በኃይል ሳይሆን እንዲህ ባለ ጥበብ ወደ ቀልቡ መመለስ ይቻላል። እኛም ብንሞክረው ብዬ ነው ያቀረብኩት።

መልካም ቀን

🤙 ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

👇👇👇👇

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5


❤️የዛሬው የግእዝ ቃላችን❤️

ረስሐ = አደፈ

@AstrogeezChannel


ጥንታዊ ጥበባት dan repost
7ቱ ባህሪያት

በስነ-ፍጥረት አፈጣጠር ሂደት ውስጥ ማወቅ የሚገቡን ባህርያት አሉ፡፡ እኑሱም የስጋ እና የነፍስን ባህርያት ነው፡፡ የስጋ ባህርያት አራት ሲሆኑ የነፍስ ደግሞ ሶስት ናቸው፡፡ እነዚህን ማወቅ ለህይወታችን እጅግ ይበጃል፡፡አራቱ ባህሪያተ ስጋ የሚባሉት

1.እሳት ፦ ሀያል ነው በተነሳ ጊዜ እርጥቡን ደረቁን ሁሉ ያቃጥላል ውሃ ካልከለከለው በስተቀር ገደል ካላጋጠመው በቀር ማቃጠሉን አያቆምም እግዚአብሔርም ቸርነቱና ምህረቱ ካልገደበው በቀር ሁሉን ያሻውን መስራት የሚችል አምላክ መሆኑን እንረዳበታለን፡፡

2.ነፋስ ፦ ፍሬን ከገለባ ይለያል እንዲሁም ጌታችን ፃድቅን ከአጥአን ይለያል ማቴ 3፡12 ላይ እንደተፃፈ “አውድማውን ፈፅሞ ያጣራል ስንዴዎንም በጎተራ ይከታል ገለባውን ግን ያቃጥላል” በሌላም ቦታ “አህዛብንም ሁሉ ከፊቱ ይሰበስባል እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ሁሉ እርስ በእርሳቸው ይለያያቸዋል” ማቴ 25፣32

3.ውሃ ፦ ያደፈውን የቆሸሸውን ሁሉ ቢያጥቡበት ያነጣል እግዚአብሔርም በክፉ ስራ ያደፋውን የሰውን ነፍስ ይቅር በለኝ ቢሉት በንስሀ ሣሙና ያነፃልና ነው፡፡ በተጨማሪም ጌታችንም ራሱ በውሃ ይመሰላል “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ” በማለት ራሱን በውሃ መስሏል፡፡ በሌላ በኩል ውሃ የሚጠጣውን ያረካል “እግዚአብሔርም በኔ ብታምኑ ነፍሰ እርካታን ታገኛላችሁ” ሲል ተናግሮዋል፡፡ ዮሐ 4፡14 ዮሐ 7፡37

4.መሬት ፦ “በዓለ ፀጋ” ናት ሁሉን የሚያስገኝ ፀጋ ሐብት ያለው መሆኑን ለማጠየቅ አንድም መሬት ለሰው ልጅ ያሻውን አብቅላ ምግቡን ልብሱን እንደምትሰጠው ሁሉ እግዚአብሔርም ልክ እንደመሬት ለሁሉ የሚበቃ ሀብት ያለው ለሰው ልጅ ምግበ ስጋና ምግበ ነፍስ የሚመግብ ባለጠጋ ነው፡፡በተጨማሪም መሬት የፈለጉትን ቢያደርጓት ቢያርሷት ቢቆፍሯት ምንም የማትል ታጋሽ እንደሆነች እንዲሁ እግዚአብሔርም ዕለት ዕለት የበደልነውን አይቶ እንዳላየ ሁሉን ቻይ ታጋሽ ጌታ ነው፡፡

ሶስቱ ባህሪያተ ነፍስ የሚባሉት

፩.ለባዊነት ፦ ማሰብ /ማገናዘብ፣ አሳቢነት/
፪.ነባቢነት ፦ መናገር /ቋንቋ ፣ተናጋሪነት/
፫.ሕያውነት ፦ ዘላለማዊነት

©ፍሬ ተዋህዶ..የተዋህዶ ልጆች(Facebook)

👉ጥንታዊ ጥበባት

Channel👉@ancient_wisdoms
Group👉@ancient_wisdoms_group

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.