የሰው ልጅ በእድሜ ዘመኑ 3 ጊዜ ህፃን ይሆናል ይላል አንድ መፅሃፍ 😁 ። የመጀመርያው ገና እንደተወለደ ሲሆን ሁለተኛው ሲሸመግል ነው ። የሰው ልጅ በስተሽምግልናው ዘመኑ የህፃን ባህሪ ተመልሶ ይላበሳል ፣ በትንሹ ያኮርፋል ፣ ተመልሶ ይረሳና ይቅር ይላል ፣ እንደ ህጻናት ጣፋጭ መውደድ ይጀምራል ... (ይህንን የምታነቡ አዛውንት ካላችሁ ይህ እናንተን ለማዋረድ የተፃፈ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ የሚገልጽ እንደሆነ ይታሰብልኝ ፣ ማን ህፃናትን የማይወድ አለ? እንደ ህፃናት መሆን ደግሞ ትልቅ ጸጋ ነው ።) የሚያስገርመው ግን 3ኛው ነው ። የሰው ልጅ ህፃን ከሚሆንባቸው 3ኛው ደግሞ በወጣትንነት ዘመኑ ነው ይላል 😂 ። እንዴት ቢሉ ፍቅር ሲይዘው 😭 ። እኔ እርግጠኛ አይደለሁም 🙌 ። እንደ መፅሃፉ ከሆነ ሰው በፍቅር ከተያዘ በኋላ እንደ ህፃን act ማድረግ ይጀምራል ። በራሱ ዓለም ይወጣል ይወርዳል ፣ ለብቻው ይስቃል ፣ ያለቅሳል 🤷♂️ ፣ በትንሹ ነገር ቶሎ ይበሳጫል ፣ ምግብ ተገዶ ነው የሚበላ💀 ፣ ትእግስት ያጣል ... (እንዴት እንዳትሉኝ ፣ እኔ እራሱ ገርሞኝ ነው የምጽፍላችሁ)... ። ለማንኛውም ወደ ህፃንነት ከሚቀይር ፍቅር ይሰውራችሁ ። ፍቅር ትእግስትን ይጨምራል እንጂ አያስጨርስም ፣ ፍቅር ማስተዋልን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም ፣ ፍቅር በሁሉ ተስፋ ያስደርጋል እንጂ በትንሹ ተስፋ አያስቆርጥም (፩ ቆሮ. ፲፫፥፬-፰) ።
ሠናይ ጊዜ ❤️
@AstrogeezChannel
ሠናይ ጊዜ ❤️
@AstrogeezChannel