የኢትዮጵያ ህግ ⚖️


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


እዚህ channel በመቀላቀል
#የኢትዮጵያ_ህጎች_እንዲሁም_አዋጆች
#የህግ_መማሪያ_መፅሀፍት
#የህግ_ማብራሪያዎችን
#የህግ_ማጣቀሻ_መፅሀፍት
#የተለያዩ ዩንቨርስቲ Exam ሞችን ያገኛሉ
ለጥያቄ ,አስተያየት @Ethiolawyers21
#Lawyers_Forever

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በስምምነት የተደረገ የውርስ ኃብት ድርሻ ክፍፍል በሕግ ፊት ስለሚኖረው ውጤት፡፡ 

ወራሾች ራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከፍርድ ቤት ውጪ የውርስ ኃብት ክፍፍል ያደረጉ ከሆነ ይህ ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባይጸድቅም የሚጸና ነው፡፡ ማንኛውም ወገን ስምምነቱ በፍርድ ቤት ቀርቦ አልጸደቀም ስለዚህ ሊጸና አይገባም የሚል መከራከሪያ ቢያቀርብ የሕግ መሰረት የለውም፡፡ ( የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1079(1) እና 1080(1)








#NewsAlert

የአማራ ክልል መንግሥት በሁሉም  የክልሉ ከተሞች  መሬት የማስተላለፍ፣ ማዘጋጀትና አገልግሎት መስጠት ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ እንዲያቆሙ አዟል።

#ዋዜማ


Here we Go 🌼

ለ366 ቀናት ውጣ ውረዶችን አልፈን : የማይረሱ ታሪኮችን ሰርተን : ትምህርታዊ ማህበሪዊና ፖለቲካዊ ፈተናዎችን አልፈን ዛሬ ላይ ደርሰናል ። ያለፈውን አመት በደስታ ጀምረው በተለያዬ አጋጣሚ ዛሬ ላይ በምድር ለሌሉ : ለሀገራቸው መስዋእት ለሆኑ ሁሉ ፈጣሪ ነፍስ ይማርልን ። ለኛም መጭውን አመት የሰላም የትምህርት እንድሁም የጤና ያድርግልን ። ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን 🙏🙏🙏

እንኳም አደረሳችሁ 🌼🙏 


Interesting facts about marriage in Ethiopia family law;

ጋብቻን ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፦
1. ፈቃደኝነት🤝
2. እድሜ👼🔞
3. ዝምድና👪
4. በጋብቻ ላይ ጋብቻ👫+🧍‍♀
5. በብቸኝት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ👩‍👦 ፦
ይሄኛው ቅድመ ሁኔታ ከላይ ካሉት አራት ቅድመ ሁኔታዎች ለየት ባለ መልኩ በሴቶች ላይ ብቻ የተጣለ ነው፡፡
አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ 180 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ቀን ካላለፈ በቀር ሌላ ጋብቻ መፈጸም እንደማትችል ክልከላ ተጥሎባታል፡፡     
ነገር ግን ይህ 180 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ቀን ሳይደርስ

1, የወለደች ከሆን ወይም
2, ጋብቻ የምትፈጽመው ከቀድሞ ባሏ ጋር ከሆነ ወይም
3, እርጉዝ አለመሆኗ በህክምና ከተረጋገጠ ወይም
4, ይህን ጊዜ እንዳትጠብቅ በፍ/ቤት የተወሰነ ከሆነ ይህን ጊዜ ሳትጠብቅ ጋብቻ ልትፈጽም እንደምትችል የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 16 (2) ላይ ተቀምጧል፡፡ 

🔥ይህ ክልከላ በዋነኝነት የተቀመጠው የህፃናትን መብት ለመጠበቅ ነው፡፡



ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏


ነገሩ እንድህ ነው ....

ጦርነት ሲጀምር-ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ-ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ ።

በየቦታውን የሚፈሰውን ደም ማን ያቁመው ? የሚፈናቀለውንስ ?

ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏


ከላይ የቀጠለ ......➡

#የውክልና #አይነቶች

በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::
  
1ኛ.ጠቅላላ ውከልና

ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡-

• የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ
• ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት
• በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ 
• ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ
• ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት
• ሰብሎችን መሸጥ
• ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡

2ኛ ልዩ ውክልና

ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡-

• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ
• አስይዞ መበደር
• ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት
• ስጦታን ማድረግ
• በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡

የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች

የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡ 

በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡    

የውክልና ጥቅም

ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ስለውክልና መቅረት

ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡

ውክልናን መሻር

ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡

የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው

ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡
   
ማጠቃለያ

በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡
               




ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏


#ውክልና
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳዮቻቸውን ራሳቸው መፈፀም የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ሊገጥሟቸው ይችላል፡፡ ለዚህ መፍትሄ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው ውክልና ነው፡፡ ሆኖም ውክልና በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን በህግ በተቀመጠው ሥርአት መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ስለ ውክልና ምንነት፣ ስለውክልና አይነቶች፣ ስለውክልና ጠቀሜታ እና ውክልና ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡
  
የውክልና ምንነት   

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2199 መሰረት ውክልና ማለት ተወካይ የተባለው ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ ሚገባበት ውል ነው፡፡ በዚህም ተወካዩ ልክ እንደወካዩ በመሆን የወካዩን ሥራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚደረግ ውል ነው፡፡
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ እንደ መሆኑ መጠን አንድ ህጋዊ ው
ል ሊያሟላቸው ያሚገባውን በፍትሐብሔር ህጉ በአንቀፅ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይኸውም፡-

👉ውል ለመዋዋል ችሎታ ያለው ሰው መሆን
👉ጉድለት የሌለው ፈቃድ ወይም ስምምነት መኖር
👉በቂ የሆነ እርግጠኝነት ያለው የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ መሆን
👉የውል አፈፃፀም ፎርም በህግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዛዙ ባይፈፀም ፈራሽነት የሚያስከትል ሲሆን ህግ በሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን ናቸው፡፡

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለያየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ግን ይህ መሟላት ይኖርበታል፡፡
   
የውክልና አይነቶች

በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ።

ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏
ይቀጥላል ......


ህዝባችን ሳያውቀው !

በህገ መንግስታችን ከ13 በላይ አንቀጾች በአንድም ሆነ በልላ መንገድ ተሻሽለዋል : ተሰርዘዋል ወይም ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ! ስለሆነም እነዚህን አንቀጾች እንደ መተዳደሪያ ወይም መዳኛ ህግ አይወሰዱም ! ሳናውቀው ተቀይረዋል ። አንድ ምሳሌ : አንቀጽ 52 ክልሎች የራሳቸው ልዩ ሀይል ይኖራቸዋል የምትለው ንዑስ አንቀጽ ። እስኪ የቀሩትን 12 አንቀጾች እራሳችሁ አውጧቸው ።

ሰላም ለሀገራችን 🙏


#እርቅ በወንጀል ጉዳዮች ያለው ፋይዳ!

#አገራችን ኢትዬጲያ የበርካታ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፤ ቋንቋዎች ፣ ባህሎች እና ወጎች ፣ ያላት ሀገር ነች፤የሀገራችን ህዝቦች የየራሳቸውን የሆነ ባህል /ወግ፣ አለባበስ እንዲሁም አገር በቀል የሆነ የዕርቅ፣ የሰላም መጠበቂያ እና የሰላም ግንባታ ስነ-ዘዴዎችም ያሏቸው ህዝቦች ናቸው፤ሀገር በቀል የሰላም መስሪያ ፣ የሰላም መጠበቂያና የሰላም ግንባታ ዘዴ የምንለው ኢ-መደበኛ የሆነው እና ማህበረሰቡ ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰው ሰነ-ዘዴ ነው፡

#በመሆኑም በእንግሊዘኛው አጠራር non-state based customary institutions የሚያመላክት ሆኖ በዚህ የሰላም እና የፍትህ ስርዓት በዳኝነት የሚቀመጡት መንግስት የሾማቸው ዳኞች ሳይሆኖ ማህበረሰቡ አምኖና ተቀብሎ ለዳኝነት የሾማቸው ባለ ልዪ ተስጦኦ የሆኑ የዕድሜ ባለፀጋ ሽማግሌዎች፤ባህላዊ መሪዎች እና ሀይማኖት አባቶች ሲሆኑ በዚህ ሂደት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ይህ መልካም የሆነ ታሪክ እና ባህል በቂ ነው ባይባልም በህጉም እውቅና ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን በፍርድ ቤቶችም ጭምር በወንጀል አድራጊው እና ተበዳይ መካከል እርቅ ሲበረታታ ይታያል፡፡ በሁሉም የወንጀል አይነቶች እርቅ መታረቅ ያልተከለከለ ሲሆን ነገር ግን እንደወንጀሉ አይነት እና በጠቅለላዉ እርቁ ፍትህን የማያረጋግጥ በሆነ ጊዜ ከሆነ እርቁ ተፈጻሚ የማይደረግ ሲሆን ነገር ግን ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንጻር ፍ/ቤቶች ፍርድ ከሰጡ በኀላ ለቅጣት ማቅለያነት ይጠቀሙታል፡፡

#በወንጀል ህጉ በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ ወንጀሎችን በአፈፃፀሙ እና ቅጣቱ ቀላል በመሆኑ የህብረተሰቡን ሰላም እና መልካም ግንኙነት ተጠብቆ ለማቆየት እንደሚጠቅም ተመልክተዋል፡፡
ሌላው በወንጀል ጉዳይ የመታረቅ ጥቅሙ፡ -የመዝገብ ክምችትን ይቀንሳል፣ ከእስራት ይልቅ በእርቅ ማለቁ ለሁለቱም ወገን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በወንጀል አድራጊው ላይ የባህሪ ለውጥ ሊመጣ ስለሚችል፣ እንዲሁም የፍርድ ቤቶችን የስራ ጫና እና የተከራካሪዎችን ግዜ ፣ ወጭ እና ጉልበት ያቀላል፡፡

#ከዚህም ባሻገር እርቅ ቀጣይነት ያለውን ሰላም በማስፈን፣የተጎዳን በመካስ ብሎም ሁለንተናዊ የሆነ ማህበራዊ ተግባቦትን በመመለስ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ነገር ግን እርቅና የተለያዩ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሀገር በቀል እውቀቶችና ስርዐቶች እየተረሱና እየተሸረሸሩ በመሄዳቸው በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ለመፈናቀል ለሞት እና
ለንብረት ውድመት ሰለባ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች ተከስተዋል፡፡

#በመሆኑም በአገር በቀል የግጭት አፈታት እና የዕርቅ ሥርዓቶች ላይ ትኩረት በማደረግ ወደ ቦታቸው መመለስ እንዲሁም በህግ ማዕቀፎቻችንም በሰፊው እንዲካተቱና እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ህብረተሰቡን በሰፊው የሚጠቅም ከመሆኑም በላይ በፍትህ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሠረታዊነት የሚፈታ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏


አድሱ ትውልድ ህግንና ህግን ብቻ መሰረት አድርጎ ህብረተሰቡን ማገልገል አለበት !

በያዝነው ወር በሀገራችን በተፈጠረው አለመረጋጋት ከ1.5 ሚሊየን በላይ ወጣት በማንነቱ ታፍኖ የት እንደገባ አይታወቅም ይባስ ብሎ ፍትህ ሚኒስቴር በአስቸኳይ አዋጅ አስፈጻሚዎች ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈጸሙ : በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ ፍርድ ቤት ታጉረው እየተደበደቡ ነው ተብሎ ሲጠየቅ የምን አገባኝ አይነት መልስ መልሷል ። ከወር በፊት በነ መስከረም አበራና ዶ/ር ወንደሰን ክስ የፍርድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ያየሁት ነገር እጅግ በጣም አሳፋሪና የማይነገር ነው !። እንደት የፌደራል ዳኛ ሆኖ ተከሳሽን ይሳደባል !? ለዚያውም ዘርን መሰረት አድርጎ !🤔 ። በሀገራችን በፍትህና ተጠያቂነት ችግር ምክንያት በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ሲንገላቱ : ሲታረዱ :ሲፈናቀሉ : ሲሳደዱና ሲታፈኑ ይስተዋላል ። ስለሆነም አድሱ ትውልድ ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ከአባቶቹ ስህተት መማር አለበት ።

አንድ ህዝብ አንድ ሀገር !

ያሳደገንና ያስተማረንን ህዝብ በቅንነት እናገልግል !!!

ሰላም ለሀገራችን 🙏


ልዩነታቸው አደናጋሪ የሆኑ 5 የህግ ቃላት
የጊዜ ገደብ እና ይርጋ፥ በጽሑድ መደረግና በጽሑፍ መረጋገጥ ያለበት ውል፥ የልዩነት ሀሳብ እና የመስማሚያ ሀሳብ፥ የውል መሰረዝ እና የውል መፍረስ፥ ሐራጅ እና ጨረታ 😍



ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏


በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
 
ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።

  የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።

  የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች

አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-

• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።

ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡

   በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ 

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል። 
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።

ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።

በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ሰላም ለሀገራችን 🙏


የተያዙ ሰዎች መብት

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 19 መሰረት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተያዙ ሰዎች የሚከተሉት መብቶች አሏቸዉ፡፡

1, የቀረበባቸውን ክስና ምክንያቶቹን በዝርዝር ወዲያውኑ በሚገባቸው ቋንቋ የመነገር መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ከሕገ- መንግስቱ በተጨማሪ በሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/2/ ስር የተቀመጠ ሲሆን በዚህም መሰረት ማንኛው ሰው በሚያዝበት ጊዜ የተያዘበትን ምክንያት የቀረበበትን ክስ ምንነት ወዲያውኑ የማወቅ መብት አለው፡፡

2, የተያዙ ሰዎች ላለመናገር መብት አላቸው፣ የሚሰጡትን ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብባቸው ስለሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያዉኑ ማስገንዘቢያ እንዲሰጣቸው መብት አላቸው፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው በፖሊስ ወይም ስልጣን ባለው ሌላ አካል ከተያዘ በኋላ ስለቀረበበት ክስም ሆነ ስለሌላ ጉዳይ አልናገርም የማለት ሙሉ መብት አለው፡፡ በተጨማሪም የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም ይህ ባይሆንና የተሰጣቸውን ህገ-መንግስታዊ ያለመናገርና ተገዶ ያለማመን መብት በመጣስ ማንኛውም ማስረጃ በማስገደድ ቢገኝ ይህ ማስረጃ ተቀባይነት እንደማይኖረው እና ውድቅ እንደሚደረግ ህገ-መንግስቱ ይደነግጋል፡፡

3, የተያዙ ሰዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም፡፡ ወዲያውኑ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመታሰር የሚበቃ ምክንያት ያለ መሆኑ ታይቶ እንዲገለጽላቸው መብት አላቸው ፍርድ ቤትም በቂ ምክንያት ካላገኘ ሰውየው እንዲለቀቅ ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡

4, የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት አላቸው፡፡ ሆኖም በህግ በተደነገጉ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ማዘዝ ይችላል፡፡

#ሀገራችንን_ሠላም_ያድርግልን🙏

@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s


ወድ የዚህ ጣቢያ ተከታዮች : ሰሞኑን እየተጠፋፋን ያለነው እንደምታውቁት በአማራ ክልል የበይነ መረብ አገልግሎት ስለተቋረጠ ነው ። ይህም ሆኖ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ጉዳዮች እንገናኛለን ::

አጋሩ

ሰላም ለሀገራችን 🙏 ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን 🙏🙏🙏

@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_s


የቀብድ ህጋዊ ውጤት
🎯🎯🎯🎯🎯

1 ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1883 ይደነግጋል።

ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍትሀ ብሄር ህግ 1723(1) ስር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በህግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የህጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል።

(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ መዝገብ/ቁ 56794 ቅፅ 12)

የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

2 የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1885)

ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።

የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ህገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።

3 ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1884)
Join us👇
@Ethiopianlaw_s
@Ethiopianlaw_
s
@Ethiopianlaw_s


አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሟል ሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው?
**
ህንዳይ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 23 ይመለከተዋል። በዚህ አንቀፅ መሰረትም አንድ ወንጀል ተፈፅሟል ለማለት ከታች የተዘረዘሩት ሶስት ነገሮችን ሊያሟላ ይገባል። እነዚህም፣
1) ወንጀሉን የሚያቋቀቁመዉ ህጋዊ ፍሬ ነገር ሊኖር ይገባል no law, no crime
ይህም ማለት አንድ ድርጊት ወንጀል ነው ለማለት የግድ በህግ ወንጀል ነው ተብሎ ሊደነገግ ይገባል:: ስለዚህ ድርጊቱ ምንም እንኳን የተወገዘ ቢሆንም በ ህግ እስካልተደነገገ ድረስ ፈፃሚው በወንጀል ጥፋተኛ አይባልም።
2) ወንጀሉን የሚያቋቀቁመዉ ግዙፋዊ ፍሬ ነገር ሊኖር ይገባል
በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው በህግ የተከለከለው ነገር ካላደረገ ወይም የታዘዘውን ነገር ከማድረግ ካልተቆጠበ በቀር ጥፋተኛ አይባልም።
3 አንድ ሰው ምንም እንኳን በ ህግ የተከለከለውን ነገር ቢፈፀምም ያንን ድርጊት ለመፈፀም አስቦ ካልሆነ ወይም ህጉ በግልፅ በቸልተኝነት ያስቀጣሉ ብሎ ባስቀመጣቸው ወንጀሎች በቸልተኝነት ካልፈፀመው በቀር ጥፋተኛ አይባልም።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Law of civil procedure lecture Two
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @Ethiolawyers21
ከወደዳቹህት 👉❤️‍🔥
Share share👇
@Ethiopianlaw_s 
@Ethiopianlaw_s 
@Ethiopianlaw_s 

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

462

obunachilar
Kanal statistikasi