ከላይ የቀጠለ ......➡
#የውክልና #አይነቶች
በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::
1ኛ.ጠቅላላ ውከልና
ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡-
• የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ
• ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት
• በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ
• ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ
• ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት
• ሰብሎችን መሸጥ
• ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡
2ኛ ልዩ ውክልና
ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡-
• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ
• አስይዞ መበደር
• ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት
• ስጦታን ማድረግ
• በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡
የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች
የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡
በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡
የውክልና ጥቅም
ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
ስለውክልና መቅረት
ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡
ውክልናን መሻር
ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡
የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው
ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡
ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏