#ቀን6/3/13ዓም "መምህራን የሀገር ብርሃን ነቸው ” =======®==========
መምህርነት ራስን እንደሻማ እያቀለጡ ለሌሎች መብራት መሆን ነው፡፡ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ከተከሰተ ጀምሮ ከባድ ተፅዕኖ ያሳደረው በትምህርት ዘርፉ ላይ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው ከ 7ወር በላይ ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፡፡ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ፕሮቶኮሎችና ስታንዳርዶች መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህ መካከል ሁሉም መምህራንና ተማሪዎች አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲለብሱ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ 25 ተማሪዎች ብቻ ሆነው እንዲማሩ፣ ተማሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ በትምህርት ቤቶች የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር፣ውሃና ሳሙና እንዲዘጋጁ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ከከፍተኛው አመራር ጀምሮ በየደረጃው የተቋቋመው ግብረ ሃይል እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ያደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በመምህራን ዘንድ የተስተዋለው ተነሳሽነትና የጀብደኝነት ስሜት ግን ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ነው፡፡ በክልላችን ትምህርት በተጀመረበቸው ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና የክፍል ደረጃዎች የመምህራን ተነሳሽነትና ትጋት በተለይም ከኮቪድ በፊት ይዘው ሲያስተምሩ ከነበረው ክፍለጊዜ ላይ ተጨማሪ ክፍለ ጊዜያትን በመያዝ ጭምር ተማሪዎችን ለመርዳት እያደረጉት ያለውን አርአያነት ያለው ስራ የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርጉና የሚያስመሰግኑ ናቸው፡፡ በዚህም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና ያቀርባል ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የክልላችን ነዋሪዎችም መምህራን ለተለያዩ አገልግሎት ፍለጋ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ ቅድሚያ በመስጠትና የሚገባቸውን ክብር በመስጠት እንድታስተናግዱልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን!!
ክብርና ሞገስ የሰውን ልጅ አዕምሮ ለሚያንፁ መምህራን!!