Harari Education Bureau


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይሄ ቴሌግራም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚያስተላልፋቸው ትምህርታዊ መልዕክቶችና የተለያዩ መረጃዎች ለትምህርቱ ማህብረሰብና ለተማሪዎች በቀላሉ ተደረሽ እንዲሆን ለማስቻል ነው ፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


#ቀን7/3/13ዓም ሀገሬ ኢትዮጵያ ትጣራለች !

ማክሰኞ ህዳር 8፣ከጠዋቱ 5፡30 በያለንበት በመቆም ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ክብርና ድጋፍ እናሳይ!
# ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ






#ቀን 7/3/2013ዓም የቢሮው ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ አደረጉ !
===============®===============
ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ህዳር 7ቀን 2013 ባካሄዱት ስብሰባ የሀገራችንን ሉዓለዊነት በመጠበቅ ላይ ያለውና ከስግብግብ ጁንታ ጋር ግብግብ ገጥሞ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ከደም ልገሳ ጀምሮ የአንድ ወር ደሙወዛችውን ለመለገሰ ቃል ገብተዋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡ ሠራተኞች ገንዘባችንን ብቻ ሳይሆን አሰፍላጊ ሆኖ ከተገኘ ህይወታችንንም ለመሰጠት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡




#ቀን6/3/13ዓም "መምህራን የሀገር ብርሃን ነቸው ” =======®==========
መምህርነት ራስን እንደሻማ እያቀለጡ ለሌሎች መብራት መሆን ነው፡፡ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ብሎም በክልላችን ከተከሰተ ጀምሮ ከባድ ተፅዕኖ ያሳደረው በትምህርት ዘርፉ ላይ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው ከ 7ወር በላይ ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፡፡ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ፕሮቶኮሎችና ስታንዳርዶች መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህ መካከል ሁሉም መምህራንና ተማሪዎች አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲለብሱ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ 25 ተማሪዎች ብቻ ሆነው እንዲማሩ፣ ተማሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ በትምህርት ቤቶች የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር፣ውሃና ሳሙና እንዲዘጋጁ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ከከፍተኛው አመራር ጀምሮ በየደረጃው የተቋቋመው ግብረ ሃይል እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ያደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በመምህራን ዘንድ የተስተዋለው ተነሳሽነትና የጀብደኝነት ስሜት ግን ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ነው፡፡ በክልላችን ትምህርት በተጀመረበቸው ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና የክፍል ደረጃዎች የመምህራን ተነሳሽነትና ትጋት በተለይም ከኮቪድ በፊት ይዘው ሲያስተምሩ ከነበረው ክፍለጊዜ ላይ ተጨማሪ ክፍለ ጊዜያትን በመያዝ ጭምር ተማሪዎችን ለመርዳት እያደረጉት ያለውን አርአያነት ያለው ስራ የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርጉና የሚያስመሰግኑ ናቸው፡፡ በዚህም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና ያቀርባል ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የክልላችን ነዋሪዎችም መምህራን ለተለያዩ አገልግሎት ፍለጋ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ ቅድሚያ በመስጠትና የሚገባቸውን ክብር በመስጠት እንድታስተናግዱልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን!!
ክብርና ሞገስ የሰውን ልጅ አዕምሮ ለሚያንፁ መምህራን!!






#ቀን5/3/13ዓም የ1ኛ ሩብ አመት የአፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ ! ================®=============== ሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ማለትም ከቀን 5-6/3/13ዓም ድረስ የቢሮውን የ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሙክታር ሳሊህ ሲሆኑ እሳቸውም እንደገለፁት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቢሮው ከባለፉት አመታት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያሰራ እንደሚገኝ አውስተው በተለይም በለፈው አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የገፅ ለገፅ የመማር ማስተማሩ ስራ ቢቋረጥም ቢሮው ከክልሉ መምህራን ጋር በመሆን በደረጉት ከፍተኛ ርብርብ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተማሪዎችን ለመርዳት ያደረጉት ጥረት አበረታች እንደነበረ ኃላፊው ገልፀዋል ፡፡ አያይዘውም ኃላፊው እንደገለፁት በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ኮሮናን እየተከለከልን የመምህርነትን ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ለማድረግ ቢሮው በልዩ ሁኔታ እንደሚሰራ ኃላፊው ገልፀዋል ፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ዳይሬክቶሬቶችና የትምህርት ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ2013ዓም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ፡፡

በውይይቱ ላይ በተለይም ኮሮናን እያተከለከሉ የመማር ማስተማር ስራውን የተሰለጠ ከማድረግ አንፃር መምህራን የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ ከቤቱ በሰፊው የተነሳ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በትምህርት ስርዓቱ ላይ የመምህርነት ሙያ ከምልመላ ጀምሮ የሚታየውን ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል ፡፡

መምህርነትን መርጠውና ፈልገው የሚመጡ ባለሙያዎች በሌሉበት የትምህርት ጥራትን ማሻሻል አስቸጋሪ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

ሙያው የሚጠበቅበትን ተልዕኮ ለማሳካት የሙያው ባለቤት የሆኑ መምህራን በአግባቡ ሊሰለጥኑና የሙያውን ግዴታ መወጣት በሚያስችላቸው ደረጃ ሊዘጋጁ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

መምህርነትን ተመራጭ የሙያ መስክ ለማድረግ የመምህራንን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ፣ የስልጠና ስርዓቱን፣ የኑሮ፣ የስራና የገቢ ሁኔታን በማሻሻል የሙያውን ክብርና ደረጃ ማሳደግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በመጨረሻም መምህራን አሁን የተጀመረውን የገፅ ለገፅ ትምህርት በቀጣይ በዘላቂነት ለማስቀጠል በሚደረገው ከፍተኛ ርብርብ ላይ ድርብ ሃላፊነት ያለበቸው በመሆኑ ከዚህ በፊት ትምህርት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተቋረጠበት ወቅት ተማሪዎችን በየቤታቸው ሆኖ ትምህርቱን እንዲከታተሉ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦና ርብርብ እንዳደረጉ ሁሉ አሁንም ዳግም ትምህርት በመከፈቱ ከዚህ በፊት የጀመሩትን ጉልህ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሮው ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል ፡፡




#ቀን4/3/13ዓም "የህዝቦች እኩልነትና አንድነት ለጋራ ብልጽግና"
የህብረ ብሄራዊነትና የአንድነት ችቦ ከሶማሌ ክልላዊ መንግስት ወደ ሀረሪ ክልል ገብቷል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱም የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የትምህርት ቢሮ ሠራተኞች በዚህ መልኩ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ።



12 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

455

obunachilar
Kanal statistikasi