የተዋህዶ ልጆች


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
የዚህ ቻናል አላማው
>ኦርቶዶክስ እውነት መሆኗን ማሳየት
>የኦርቶዶክስ ስርአት ማሳየት
>የተለያዪ ጥያቄዎችን መመለስ
>የተለያዪ አዳዲስ መዝሙሮች ማቅረብ
በቅርቡ በYoutube እና በtik tok የተለያዩ የስብከት እና የመሳሰሉትን videoዎች ይዘን እንመጣለን https://youtu.be/dBUdn7vFtm8
ጥያቄ ለመላክ @Yile_Ortodox

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ቻሌንጁን ይቀላቀላሉ ያተርፉበታል።
እስካሁን 400 ሰው ተቀላቅሏል




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
✝አድርጊያለሁ CHALLENGE በTIK TOK
💫 ቻሌጁን ይቀላቀላሉ።
⭐️አላማው መናፍቃን በtik tok ላይ የሚያነሱትን ማንኛውም አይነት ጥያቄ LIVE ገብቶ መመለስ ነው።
ለመቀላቀል👇👇👇👇 https://vm.tiktok.com/ZMdpoKVyK/


እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ።
👉ለባለ ማህተቦች ያጋሩ
💚 @Ortodox_Nane 💚
💛 @Ortodox_Nane 💛
❤️ @Ortodox_Nane ❤️


የተዋህዶ ልጆች dan repost
እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳቹ።የሊቀ መልአኩ ረድኤት እና በረከቱ አይለየን።


Quality Button dan repost
በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅይንኩ [በመላክት ፈጥኖ ደራሽነት የሚያምን እንዲሁም በጌታችን በመድሀኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነት የሚያምን ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባው ቻናል ነው ከስር ጆይን የሚለውን ይንኩይንኩ።


የተዋህዶ ልጆች dan repost
ሰላም 🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
ቻናሎ አላድግ ብሎታል? እንግዲያውስ
ለቻናሎች
1)Cross ከ100-20k
2)Wave ከ200-20k
3)Addmin exchange 100-15k ድረስ
ያለን ቦታ ውስን ነው ቶሎ ይቀላቀሉ
ለግሩፖች
1)Addmin exchange 500-10k
'http://t.me/Ortodox_Nane%0A[ rel="nofollow" target="_blank" href='https://t.me/Yile_Ortodox'>@Yile_Ortodox](t.me/Ortodox_Nane' rel='nofollow'>2)Wave 200-50k ድረስ ለ20 ሰዎች ብቻ ያናግሩን
@YileOrrodox
@YileOrtodox1


✝ እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝ †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††✝ ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ ወሰማዕት ✝†††

††† ቅዱስ ዮሐንስ በቀደመው ዘመን ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ መርባስ ትባላለች:: ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚወዱ: ምጽዋትን የሚያዘወትሩና በበጐው ጐዳና የሚኖሩ ነበሩ:: ነገር ግን ልጅ በማጣታቸው ምክንያት ፈጽመው ያዝኑ: ይጸልዩም ነበር:: በተለይ ለመጥምቁ ዮሐንስ ልዩ ፍቅር ስለ ነበራቸው ዝክሩን ይዘክሩ: በስሙም ይማጸኑ ነበርና መጥምቁ ሰማቸው::

ወደ ፈጣሪውም ልመናቸውን በማድረሱ መልክ ከደም ግባት የተባበረለት ደግ ልጅን ወለዱ:: እጅጉን ደስ ስላላቸው በአካባቢያቸው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስን ቤተ ክርስቲያን በገንዘባቸው አነጹ:: ሕፃኑንም በመጥምቁ ስም "ዮሐንስ" አሉት:: ጻድቁ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አድሮበታልና ሕይወቱ ግሩም ነበር::

በሕፃን ገላው ይጾምና ይሰግድ: በልጅ አንደበቱም ተግቶ ይጸልይ ነበር:: ወላጆቹ ወደ እረኝነት ባሰማሩት ጊዜም መፍቀሬ ነዳያን ነውና ቁርስና ምሳውን ለነዳያን እያበላ እርሱ ጾሙን ይውል ነበር:: አባቱ የሚያደርገውን ሰምቶ ለማረጋገጥ ተከተለው:: እንዳሉትም እናቱ ጋግራ የሰጠችውን ትኩስ ዳቦ ለነዳያን ሲሰጥ አየው::

ሊቆጣው ፈልጐ "ዳቦህ የታለ?" ቢለው ሕፃኑ ቅዱስ ዮሐንስ "በአገልግሉ ውስጥ አለ" ሲል መለሰለት:: አባት ለመቆጣት እንዲመቸው አገልግሉን ሲከፍተው ግን ያየውን ማመን አልቻለም:: በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ዳቦዎቹ ትኩስ እንደሆኑ ተገኙ::

አባትም ወደ ቤቱ ወስዶ "ልጄ! አንተ የእግዚአብሔር ሰው ስለሆንክ እኛን ሳይሆን እርሱን አገልግል" ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላከው::

በዚህ ምክንያት ቅዱስ ዮሐንስ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ ትምህርት ገባ:: በስድስት ዓመታትም ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አሥራ ስምንት ዓመት ሲሞላው ደግነቱን ወደዋልና በግድ ቅስና ሾሙት:: እርሱ ግን ለተወሰነ ጊዜ አስተምሮ ዘመዱ የሆነውንና ዲያቆኑን ቅዱስ ስምዖንን አስከትሎ መነነ::
በዚያም በፍጹም ገድል ሲኖር ብዙ ተአምራትን ሰርቷል::

¤አንድ ወታደር (አንድ ዐይና ነው) ሊባረክ ብሎ ሲጐነበስ የታወረች ዐይኑን የቅዱስ ዮሐንስ ልብስ ቢነካት በርታለታለች:: ከዚህ አልፎም ቅዱሱ ብዙ ድውያንን ፈውሷል: ለምጻሞችን አድኗል: አጋንንትን ከማደሪያቸው (ከሰው ላይ) አሳድዷል::

ታዲያ አንድ ቀን የወቅቱ የአንጾኪያ ንጉሥ የቅዱስ ዮሐንስን ዜና ይሰማል:: የእርሱ ልጅ ደግሞ አጋንንት አድረውባት ስቃይ ላይ ነበረችና የሚያድናት አልተገኘም:: ንጉሡ "ጻድቁን አምጡልኝ" ብሎ መልዕክተኛ ሲልክ ቅዱስ ዮሐንስ ደመና ጠቅሶ: በዚያውም ላይ ተጭኖ ከተፍ አለ:: ንጉሡ አይቶት ደነገጠ:: አባ ዮሐንስ ግን "እኔ ኃጢአተኛ የሆንኩ ሰው ለምን እንዲህ ትፈልገኛለህ?" ብሎ ታማሚዋን አስጠራ::

ጻድቁ እጆቹን አንስቶ ወደ ፈጣሪው ሲጸልይ በወጣቷ ላይ ያደረው ሰይጣን ሕዝቡ እያዩት ከሆዷ በዘንዶ አምሳል ወጥቶ ሔደ:: ንጉሡ ስለተደረገለት ውለታ ለቅዱስ ዮሐንስ ወርቅና ብር ብዙ ሽልማትም አቀረበ:: አባቶቻችን እንዲህ ዓይነት ነገር አይወዱምና ቅዱሱ "እንቢ አልወስድም" አለ::

ቅዱስ ዮሐንስ "ልሒድ" ብሎ ሲነሳ ንጉሡ "አባቴ ወድጄሃለሁና አትሒድ" ብሎ የልብሱን ዘርፍ (ጫፍ) ያዘው:: በቅጽበት ግን ደመና መጥታ ነጥቃ ወሰደችው:: የቀሚሱ ቁራጭም በንጉሡ እጅ ላይ ቀረች:: እርሱም ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ያችን የተባረከች ጨርቅ በክብር አኑሯታል::

ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ) ግን ከብዙ የተጋድሎ ዓመታት በኋላ ሌላ ክብር መጣላቸው:: "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" የሚል ንጉሥ በመነሳቱም ሒደው በጌታችን ስም መሰከሩ:: በገድል በተቀጠቀጠ ገላቸው ላይ ግርፋትን: እሳትን ታገሱ:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተቆርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል::

††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታችቸውም ያድለን::

††† ሐምሌ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ስምዖን (ደቀ መዝሙሩ)
3.አባ ኢሳይያስ ዘገዳመ አስቄጥስ
4.አባ ገብርኤል ሊቀ ጳጳሳት

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት

††† "ሒዳችሁም መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ:: ድውዮችን ፈውሱ: ሙታንን አንሱ: ለምጻሞችን አንጹ: አጋንንትን አውጡ:: በከንቱ ተቀብላችሁ በከንቱ ስጡ:: ወርቅ: ወይም ብር: ወይም ናስ በመቀነታችሁ: ወይም ለመንገድ ከረጢት: ወይም ሁለት እጀ ጠባብ: ወይም ጫማ: ወይም በትር: አታግኙ:: ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና::" †††
(ማቴ. ፲፥፯)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@Ortodox_Nane


💖 🕊 💖

🕊 ድንቅ ተአምር 🕊

🕊

ትላንት ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓም በቅድሥት ሥላሴ " ካቴድራል " አዲስ አበባ የተሰጠ ምስክርነት !

🕊

መስካሪዋ እናት ናቸው። የሁለት ልጆች እናት። ሁለተኛው ልጃቸው ዳንኤል ይባላል፡፡ የአራት አመት ልጅ ሆኖ በድንገት ራሴን ወጋኝ አይኔንም አቃጠለኝ ብሎ አለቀሰ።

ልጁ ህመሙ ጸናበት በአራተኛው ቀን ሁለት አይኖቹ ታወሩ። ሁለት ጆሮቹም ደንቆሩ። ጤነኛ ልጅ ወልዶ በአንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ችግር ውስጥ መውደቅ ያሳዝናል። አሜሪካን አገር የሚኖረው የዳንኤል አባትም ፍጹም ሀዘን እና ጭንቀት ውስጥ ወደቀ። እናት ሥራቸውን ለቀቁ በርካታ ገንዘብ እየተከፈለ የዳንኤል ህክምናው በየአቅጣጫው ቀጠለ። አልተሳካም።

ወላጅ እናት ሕጻን ዳንኤልን ይዘው ወደ የጠበል ጉዞ ሆነ። አራት ዓመት ሙሉ በጸሎት ፤ በጠበልና በእምነት እግዚአብሔር ሲማጸኑ ቆዩ። ለአራት አመታት ሙሉ ልጃቸው ዳንኤል ዓይኑ እንደታወረ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ኑሮ ቀጠለ። የአባት እና እናት ጸሎትና ተማጽኖ ቀጠለ።

ከትናንትና በስቲያ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም እናት ልጃቸው ዳንኤልን በመኪናቸው ይዘው አራት ኪሎ ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል መጡ። ቅዳሴ የተቀደሰበትን እምነት ግቢው ውስጥ ባለው የቅድስት ሥላሴ ጠበል በጥብጠው የልጃቸውን የታወሩ አይኖቹን በእምነቱ ለቀለቋቸው። ሁለት ጆሮቹንም እምነቱን ቀቧቸው። እንዲህ ብለውም ተማጸኑ ፦ 'አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ እርዱኝ ልጄ ቢያንስ ድምጼን ስምቶ እንድንግባባ ፤ ባይሆን ጆሮውን እንኳን ክፈቱልኝ' ብለው ተማጸኑ። ከዚያም ልጃቸውን ይዘው መኪናቸውን እየነዱ ወደቤታቸው ሄዱ።

በዛኑ ቀን ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ከሌሉቱ ሰባት ሰዓት ላይ ህጻን ዳንኤል በአልጋው ሆኖ እናቱን ተጣራ። 'ምነው ልጄ ደሞ ታመመብኝ ይሆን በሌሊት የሚጠራኝ?' ብለው ወደ ልጁ ሄዱ።

እማዬ አይታይሽም ? ... አይታይሽም ? ... አይታይሽም ? ብሎ ጮኽ ህጻን ዳንኤል። የሚሰማኝ ይመስል ምንድነው ? ሥለው ልጄ ዳንኤል ድምጼን ሰማኝ ! እማ .. እማ አለ..... ጆሮው ተከፍቶ ድምጼን ሰምቶ ! እይው ... እይው... ያንን መስቀል አለኝ። ለእኔ የሚታየኝ ነገር አልነበረም ፈዝዤ ቀረሁ። እይው የሚያበራ መስቀል እና መስቀሉ ላይ ያሉትን ሦስት ትልልቅ ሰዎች እያቸው ... እያቸው ... እያቸው አለኝ። እነዚህ ሦስት ሰዎች መስቀሉ ላይ ሆነው አይኔን አበሩልኝ ጆሮዬንም አዳኑኝ ብሎ ተናገረ።

እናት እ እ... ልጄ.. ድምጼን እየሰማህ ነው ? እ እኔ እታይሃለሁ ? ብለው በድንጋጤ ሆነው ጠየቁ፡፡
'.... አዎ አዎ እማዬ' የልጃቸው መልስ ነበር፡፡ እናት እንዲህ አሉ ...ልብስ ደረብኩ እና ምን አይነት ልብስ ነው የለበስኩት? አልኩት ልጄን፡፡ 'እናቴ ነጭ እኮ ነው' ብሎ በትክክል ነገረኝ። እናትና ልጅ ተቃቅፈው በለቅሶ ተዋጡ። ከአራት አመታት በኋላ ልጅ የእናቱን ድምጽ ሰማ ! የእናቱን ፊት አየ.....

ወዲያው እናት እና ልጅ ልብሳቸውን ለብሰው ሌሊቱን መኪናቸውን እየነዱ ወደ ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል መጡ። ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ልጅ የቅድሥት ሥላሴን ሥዕል አየ። 'እማዬ እነዚህ ናቸው እኮ ማታ መስቀሉ ላይ ያየኋቸው ! እነዚህ ናቸው እኮ ያዳኑኝ' ብሎ በገሀድ ተናገረ።

የቅድስት ሥላሴን በዓል ሊያከብር የተሰበሰበው ምዕመን እግዚአብሔርን አመሠገነ፡፡ እልልታ እና ለቅሶ ቀጠለ .... ምሥክርነቱ ተሰጠ። የቃል ኪዳኑ ታቦት ዞሮ እንደቆመ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደቆሙ እኛ ሁላችን እንደቆምን ምስክርነቱ በገሃድ ለህዝበ ክርስቲያን ታወጀ።

አይኖቻቸው በእንባ የረጠቡ አዕላፍ ምዕመናን በማያቋርጥ እልልታ ግቢውን አናጉት። የደስታ እንባ ከሁላችንም አይኖች ፈሰሰ ....

ክብር ምሥጋና ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴ !

ይህንን ተአምር ታቦቱ ፊት ቆሜ እንደሰማሁ ወዲያውኑ ዛሬ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ከጠዋቱ አምስት ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ላይ ጻፍኩት።

የሥላሴ ቤተሰቦች ደስ ይላችሁ ዘንድም ለሁላችሁም ላኩላችሁ። ሥላሴን አመስግኑ !


" እባካችሁ ወገኖቼ በእምነታችሁ ጽኑ ! " ምስክርነቱን ያደረሰን የወንድማችን ምክር ነው፡፡

[ የተዋህዶ ልጆች ]

🕊

" አቤቱ ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።

በአንተ ደስ ይለኛል ፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ ፤ ልዑል ሆይ ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።" [ መዝ.፱፥፩]

💖 🕊 💖
@Ortodox_Nane


#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@Ortodox_Nane


የተዋህዶ ልጆች dan repost
ድንግል ማርያምን የሚወድ ብቻ JOIN ይበል።




የተዋህዶ ልጆች dan repost
በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅይንኩ(t.me/ortodox_Nane) [በመላክት ፈጥኖ ደራሽነት የሚያምን እንዲሁም በጌታችን በመድሀኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ፈራጅነት የሚያምን ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባው ቻናል ነው ከስር ጆይን የሚለውን ይንኩይንኩ።


Quality Button dan repost
ወዳጆቼ ሆይ ከፆም እና ከፀሎት በኋላ እንዲህ ማለት ይልመድብን።

ፆም ፀሎታችንን ተቀበልልን ፣
ደስ የሚያሰኘን ይሁንልን ፣
እንዳንሸነፍ ሃይልህን ስጠን ፣
አፍሮ ይመለስ ይውደቅ ሰይጣን ፣


Quality Button dan repost
ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።


የተዋህዶ ልጆች dan repost
ስለ ንቅሳት በተከታታይ ያቀረብነውን ፅሁፍ በድምፅ እና በቪዲዮ አዘጋጅተናል ይንኩትና ይመልከቱ









20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

412

obunachilar
Kanal statistikasi