የመጨረሻ ክፍል
✝የንቅሳት መንፈስ ፦
"#ከእግዚአብሔር_እንደ ሆንን አለም በመላው በክፉው እንደተያዘ እናቃለን" 1ዮሐ 5፥19
💠 በዘመናችን የክፉ መንፈስ ወይም የዲያቢሎስ አደጋዎች መካከል ፤ በተለይ በእኛ ወጣቶች ላይ ትልቅ ጉዳት እና አስከፊ ተፅዕኖ እያሳደረ ያለ መንፈስ ነው የንቅሳት መንፈስ ። በአሁኑ ባለንበት ዘመን አብዛኛው ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ፤ በተለያየ አካላቸው ላይ የሚነቀሱት ፤ ድራገን ፤ እባብ ፤ ዳይናሶር ፤ አንበሳ ፤ ነብር ፤ ዝንጀሮ ፤ ተኩላ ፤ ጊንጥ ፤ አሞራ ፤ የእሳት ነበልባል ፤ ጦር ፤ ሠይፍ ፤ ተራራ ገደል ፤ አበባ እና የተለያዩ መናፍስታዊ ቁጥሮች ለምሳሌ ፤ 666 ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት ናቸው።
💠 በዚህም ከላይ በዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ ክፉው መንፈስ የንቅሳቱን አውሬና ነፍሳት ጠባይ አስከትሎ ወደ ሰዎቹ ይገባል። የሰዎቹን ምርጫ ተከትሎ ማለትም ልጁ ወይም ልጅቷ እንደ ተነቀሱት የንቅሳት አይነት ለምሳሌ ፥ ድራገን ፤ እባብ ቢነቀሱ እነደነዚ እንስሳት የነሱን ባህሪ ፈተናውን ችግሩን ያበዛባቸዋል ፤ እናም ይሄ የንቅሳት መንፈስ ከነፍሳችን ጋር ሲዋሀድ እና ሊቆራኘን ሲል እንደነዚህ አይነት ፈተናዎችን ያበዛብናል ፦
✔️በሕልም በመቃዠት
✔️በውን በምናብ መዘበራረቅ ይህም ማለት በቀንም ሆነ በማታ በውልብታ በማስደንገጥ
✔️ አለማስተዋል ግራ መጋባት
✔️ በሁሉም ነገሮች ላይ መወሰን አለመቻል
✔️ቸልተኝነት
✔️ክፉውን ደጉን አለመለየት
✔️ሁል ጊዜ ተቃራኒ ሀሳብ መያዝና መውደድ
✔️ሙሉ በሙሉ በራሱ የመሻት ፍላጐት የማጣት ሕይወት ፤ እንዲኖረን ያደርጋል።
🔴 ከዚህ መንፈስ ለመላቀቅ ምን እናድርግ ??
💠 በመጀመሪያ በስሜታዊነትም ተነስተን ወይም በጓደኞቻችን ግፊት እና የዘመኑን (Fashion) ተከታይ ወይም በዘመኑ አባባል አራዳ (አዋቂ) ለመባል በተለያዩ በሰውነታችን ቦታዎች ላይ ይሄን ንቅሳት እንነቀሳለን ፤ ከዛም ከላይ እንዳየነው ይህ የንቅሳት መንፈስ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ከተቆጣጠረን ህይወታችን ፤ የመከራ ፤ የስቃይ ያረግብናል ።
💠 በአጠቃላይ ይህን ክፉ መንፈስ የምናሸንፈው ደግሞ ለእግዚአብሔር ስንገዛ ፤ ዘወትር በህይወታችን ውስጥ ለአምልኮት ጊዜ ና አክብሮት ስንሰጥ ፤ በስግደት ፤ በአስራት በኩራት ለ ቤተ ክርስቲያን በምንሰጠው ነገር ፤ በንስሀ በመመለስ ፤ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል ፤ #ከእግዚአብሔር ጋር ይህን መንፈስ መቃወም እንችላለን ማለት ነው ። የተስፋው ቃል እንዲህ ይላል ፦ "#በወደደን_በእሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን " (ሮሜ 8፥37 )
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች ሁል ጊዜ በፀሎት እየተጋን ፤ ጉልበታችንን በስግደት#ለእግዚአብሔር በማስገዛት ፤ የወጣትነት እድሜያችንን ( ጊዜያችንን) #ለኢየሱስ ክርስቶስ በመስጠት ፤ እንድንኖር #እግዚአብሔር_ይርዳን!!
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
🙏ወለወላዲቱ ድንግል!
🙏ወለመስቀሉ ክቡር!
®የተዋህዶ ልጆች
💚
@Ortodox_Nanev 💚
💛
@Ortodox_Nane 💛
❤️
@Ortodox_Nane ❤️