በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው፣ በካድሬነት ሥርዓቱን እያገለገሉ የሚገኙትን አካላት ከማንኛውም ማህበራዊ ህይወት እንዲገለሉ፣ ቢሞቱ እንዳትቀብሯቸው፣ አሊያም ዘመድ ቢሞትባቸው እነሱ ጋር ለቅሶ እንዳትደርሷቸው፣ ሰርግና መሰል ፕሮግራሞች ቢኖራቸው ከነሱ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት እንዳይደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
የብልፅግና ካድሬዎች በገጠርም ሆነ በከተማ በሚጠሯቸው ማናቸውም ስብሰባዎች ላይ ሕዝባችን እንዳይገኝ፣ እንዲሁም በጥቅም ተደልለው ይሁን ባለማወቅ በሽምግልና ስም ወዲያ ወዲህ የሚሉ አካላትም ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን::
ማሳሰቢያ
------
በምንወስዳቸው እርምጃዎች ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ ተቋማት፣ ለምሳሌ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሰውና የእንሰሳት የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የግብርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች አይነኩም::
የትግላችን ዋነኛ ትኩረት በነፍጠኛው የአብይ ሥርዓተ-መንግሥት ላይ በመሆኑ፣ ሌሎች የባህል፣ የማሕበረሰብ እና የሀይማኖት ተቋማት በምንም ሁኔታ አይነኩም:: ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ፣ አፈላጊው ጥበቃ ሁሉ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን:: በውስጣችን የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የኛው አካል በመሆናቸው፣ ምንም አይነት ጉዳት አይደርስባቸውም::
ማጠቃለያ
--------
ከላይ በግልፅ እንደተገለፀው፣ ህዝባችን በዚህ ወቅት የገባበት ትግል፣ ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ሀገር ላይ ባለቤት ለመሆን እስኪችል ድረስ የሚቀጥል ይሆናል:: ስለዚህ ይህ የትግል ምእራፍ ሲገባደድ በቀጣይ በመላው ኦሮሚያ የሚደረግ አዲስ የትግል ምእራፍ እንደሚገለፅ ከወዲሁ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን::
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ።