📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ከመቅረዝ ማህደር
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
1) ጠይቃለው !!!
ለምንድን ነው የምትኖረው ?
እኔው ?
እሺ ለምንድን ነው የማትሞተው ?
ካለው ?
ማን እየጠየቀኝ፤ጥያቄስ ምንድን ነው ?
እያልኩኝ፣እላለው
ማለትስ ምንድን ነው ?
ዘርፋፋ ሕይወትን፤በሎጋ ጣቶቼ
መንካት፣መዳሰስን ትቼ ላልተው ትቼ
ምን ደረሰ ዘመን፤የማን ?
ምን ተገኘ፤ከምን ?
ማን እየጠየቀኝ፤ጥያቄስ ምንድን ነው ?
እያልኩኝ፣እላለው
ማለትስ ምንድን ነው ?
ዘካርያስ ምህረቱ ወ.በ
2013 ዓ.ም
2 ) ነይ...፤
ነይ አንቺ አሳ፣
ብርድ እኮ ነው አበሳ ፤
ግቢ ከኔ መረብ፤
ምን ደሃ ሆኜ ብራብ፣
እሳት አይጠፋኝም የሚደረብ፤
ከጥዑም ቅቤም ባለኝ፣
ብነፍግ ሆዴ አይቀበለኝ !፤
ነይ አንቺ አሳ፣
ብርድ እኮ ነው አበሳ፤
ዘካርያስ ምህረቱ ወ.በ
2013 ዓ.ም
(መነሻ ሀሳብ ከመጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
ከዘነብ ኢትዮጵያዊ)
መልካም ሰንበት !
ከመቅረዝ ማህደር
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
1) ጠይቃለው !!!
ለምንድን ነው የምትኖረው ?
እኔው ?
እሺ ለምንድን ነው የማትሞተው ?
ካለው ?
ማን እየጠየቀኝ፤ጥያቄስ ምንድን ነው ?
እያልኩኝ፣እላለው
ማለትስ ምንድን ነው ?
ዘርፋፋ ሕይወትን፤በሎጋ ጣቶቼ
መንካት፣መዳሰስን ትቼ ላልተው ትቼ
ምን ደረሰ ዘመን፤የማን ?
ምን ተገኘ፤ከምን ?
ማን እየጠየቀኝ፤ጥያቄስ ምንድን ነው ?
እያልኩኝ፣እላለው
ማለትስ ምንድን ነው ?
ዘካርያስ ምህረቱ ወ.በ
2013 ዓ.ም
2 ) ነይ...፤
ነይ አንቺ አሳ፣
ብርድ እኮ ነው አበሳ ፤
ግቢ ከኔ መረብ፤
ምን ደሃ ሆኜ ብራብ፣
እሳት አይጠፋኝም የሚደረብ፤
ከጥዑም ቅቤም ባለኝ፣
ብነፍግ ሆዴ አይቀበለኝ !፤
ነይ አንቺ አሳ፣
ብርድ እኮ ነው አበሳ፤
ዘካርያስ ምህረቱ ወ.በ
2013 ዓ.ም
(መነሻ ሀሳብ ከመጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
ከዘነብ ኢትዮጵያዊ)
መልካም ሰንበት !