📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
የመፃህፍት ጥቆማ
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ሠላም እንደምን ናችሁ ውድ የአምዳችን ቤተሰቦች፤እንደምን ናችሁ? የዛሬው የመፃህፍት ዳሰሳችን የሚዳስሰው መፃሃፍ፦
አርዕስት ፦ የህሊና ደወል
ደራሲ፦ በዓሉ ግርማ (ልብ ወለድ)
በማንኩሳ አሳታሚ
ሦስተኛ ዕትም 2005 ዓ.ም
የመሸጫ ዋጋ 150(አንድ መቶ ሃምሳ ብር)
የገፅ ብዛት 248
ይህ መፃሃፍ የመጀመርያ ዕትሙ በ1966 ዓ.ም ነው።የእውነት ሀዲስ ሳህሌ የኛ ዘመን ወጣት ክፍተትን የሚያነሳ፤ከብዙ ተቃውሞ፣ከብዙ ሁካት ጥቂት ሥራ ብዙ ትርጉም እንዳለው ልባችን ውስጥ በሥራው ሥራ በዝምተኝነት ያነቃናል።
ፊታውራሪ ተካ በእምነታቸው ጥንካሬ ልጃቸውን ሊወስድ የመጣን ሙሽራ መልሰው እኛስ? በእምነታችን እስከየት ድረስ ነን ያስብሉናል።
አይናለም የፊትአውራሪ ተካ ልጅ በአባቷ እምነት መታመን አድጋ፣ባለቤቷን ሀዲስ አግብታ ያመነችበትን ለመፈፀም በምትሄደው ጉዛ ውስጥ እኔስ ምንም አላዋቂ ብሆን እንዴት እንደ ቶሎሳ ላመንኩበት ህልሜ በኔው መንገድ አልሞትም...በራሴ መንገድ መኖር አልቻልኩም!፣እሺ ቢያንስ ለተስፋዬ፣ለቃሌ በኔ መንገድ አልሞትም?
የበዓሉ አተራረክ፣በዚህ ውብ የልቦለድ አለም ውስጥ ተሸምኖ እነሆ በረከት ይላችኃል፣እነሆ በረከት፦
"ህይወት ራሱ ህልም - ቅዠት መስሎ ታየው።ምናልባት ከዚህ ቅዠት አምልጠን ወደውነተኛው ህይወት ዘለአለማዊ ህይወት የምንገባውና ከፍጥረት ጋር የምንዋሀደው በሞት ብቻ ይሆናል፤ሞት ብቻ ነው የፍጥረት ሁሉ የመጨረሻ ግብ - "
ገፅ-170
ደሞ አንድ ቀን ኢትዮጵያ ሀገራችን
"እጅህን በተስፋ ስጠባበቅ ኖርኩ ልጄ አሁንስ ታከተኝ.."
እንዳትለን በፍቅር የተሞላ ልባችንን፣በእምነት የተሞላ ኑሯችንን እና በሥራ የተሞላ እጃችንን አንንፈጋት።
መልካም ንባብ
@mekerezeአግኙን
@zeki23Etete@aduyes@test17 ዘካርያስ ምህረቱ ወ.በ
5/12/2013ዓ.ም
ፈጣሪ በምህረት ዐይኑ ምድራችንን ይመልከትልን ።
አሜን !!!