'ብላ ፣ ጠጣ ፣ ተደሰት ነገ ሟች ነህና!>
ሄዶኒዝም
ምንጭ ፦ ከፈላስፎች ዓለም
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
የህይወት ተቀዳሚ አላማ ደስታን አግኝቶ ስቃይን ማስወገድ ነው። እያንዳንዱ እንቅስቃሴና ድርጊት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከዚህ ውስጣዊ ፍላጎት ይመነጫል።
በሄዶኒዝም ፍልስፍና መሰረት የሰው ልጅ የሞራል ግዴታ አንድና አንድ ነው ደስታን አግኝቶ ስቃይን ማስወገድ በሌላ አገላለጽ ደስታ ለማግኘት ያለውን ጥልቅ ጉጉት ማሟላትና በተቻለው አቅም ስቃይን ማጥፋት፡ ካልሆነም መቀነስ።
በሄዶኒዝም ፍልስፍና ውስጥ የተለያዩ ፈርጆች አሉ። አንዳንዶቹ ቅጽበታዊ ለሆኑ ስሜታዊ ፈንጠዝያዎች ትኩረት ሲሰጡ አንዳንዶቹ ደግሞ ለመንፈሳዊ የደስታ ምንጮች ቅድሚያ ይሰጣሉ።
አሪስቲፐስን የመሳሰሉ ሄዶኒስቶች አካላዊ ደስታ የህይወት ተቀዳሚ ግብ እንደሆነ ይሰብካሉ። በአሪስቲፐስ ፍልስፍና መሰረት ደስታ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት እንደመሆኑ ሰዎች ህይወት የቸረቻቸውን አጋጣሚ አሟጠው መጠቀም አለባቸው።
አካላዊና መንፈሳዊ ተብሎ የሚፈረጅ የደስታ ምንጭ የለም። መሰረታዊው ነገር በተገኘው አጋጣሚ መደሰት፣ በተቻለን አቅም ስቃይን ማስወገድ እስከሆነ ድረስ ማንኛውም አይነት የደስታ ቅጽበት መባከን የለበትም። ምክንያቱም እያንዳንዱ የደስታ ቅጽበት ተመልሶ አይገኝም። በመሆኑም የህይወት መርህ ቀላልና ፍጹም የማያወላዳ ነው - "ብላ፣ ጠጣ ተደሰት - ነገ ሟች ነህና››
የዚህ ፍልስፍና አራማጆች ከዛሬ ደስታቸው ባሻገር ስላለው ነገ አይጨነቁም። ደስታ ብቸኛው የህይወት ግብ በመሆኑ እያንዳንዱ ሰው የደስታ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ምቹ አጋጣሚዎችን ሳይሰስት መጠቀም አለበት።
ከጥንታዊ የሄዶኒዝም ፍልስፍና አራማጆች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው ኢፒካረስ ይህን አይነቱን ክፉን ከደግ ሳይለዩ ደስታን የማሳደድ መርህ ይቃወማል። ደስታ የሀይወት ታላቁ ገጸ በረከት ቢሆንም አንዳንድ የደስታ ምንጮች ጎጂ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ።
'ብላ ጠጣ፣ ተደሰት ነገ ሟች ነህና' በሚል መርህ የሚመሩ ግለሰቦች የማታ ማታ ለጉዳት መዳረጋቸው አይቀርም። ሞት በቀላሉ የሚከሰት ባለመሆኑ ሁሉም ሰው የአፍራሽ ድርጊቱን ምንዳ ለመቀበል ይገደዳል። ነገራትን ግራ ቀኝ ሳያጤኑ ባልተገራ የደስታ አሳዳጅነት ስሜት መነዳት ደስታን ሊያመናምን፣ ሊያጠፋ ወይም ከነአካቴው ደስታን ወደ ስቃይ ሊቀይር ይችላል።
ከዚህ በመነሳት ጥንታዊው ፈላስፋ ኤፒካረስ 'ደስታን የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተመሳሳይ ዋጋ የለውምና ሰዎች የደስታ ምንጮቻቸውን ለያይተው ማጤን ይኖርባቸዋል› ይለናል። የተሻለ መጻኢ ጊዜን ለመፍጠር አንዳንድ የደስታ ምንጮች መወገድ ሲኖርባቸው አንዳንድ ስቃይን ሊያስከትሉ የሚችሉ ተሞክሮዎች በጽናት ሊታለፉ ይገባል። አንድ የታመመ ሰው ጤናማ መሆን ይችል ዘንድ ጎምዛዛ መድሀኒቶችን መውሰድ ብሎም አሰቃቂ ቀዶ ጥገናዎችን ማካሄድ ይጠበቅበታል።
ለኤፒካረስ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት አስተውሎ ነው። በርግጥ ተገቢ ካልሆኑ የደስታ ምንጮች ታድጎ መልካም ወደሆኑት የሚመራን አስተዋይነት በመሆኑ መልካም የሆኑ የደስታ ምንጮችን መለያ ሚዛን ይሆናል። ለዘላቂ ስኬትና ደስታ ጊዜያዊ የስቃይ ስሜቶችን በጽናት መቋቋም ይችል ዘንድ ሰው አስተዋይ ልቡና ያስፈልገዋል።
የኤፒካረስ ፍልስፍና ደስታን ከመሻት ይልቅ ስቃይን ስለማስወገድ አጽንኦት ይሰጣል። ምክንያቱም ህይወት ራሷ ከሁሉ የላቀች ሀብት እንደመሇኗ ከስቃይ፣ ህመም፣ ፍርሀትና ሞት ጋር አብራ የምትሄድ አይደለችም።
በኤፒካረስ አገላለጽ ‹‹ደስታ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት ቢሆንም ይህ ደስታ ከአካላዊና ስሜታዊ ብኩንነት የሚመነጭ አይደለም" ይህ አይነቱ ደስታ በስካርና ዝሙት ህሊናን በማወር የሚገኘው ከንቱነት አይደለም። ይህ አይነቱ ደስታ ከአካላዊ ህመምና ከአእምሯዊ ስቃይ ነጻ ከመውጣት የሚገኘው እፎይታ ነው። የአእምሮ ህመም ከአካላዊው የከፋ ሲሆን ለክፋትም ሁሉ ስር ነው። አካላዊ ህመም በጽናት ሊታለፍ ይችላል። ካልታለፈም ፍጻሜው ሞት ይሆናል። ሞት ደግሞ የከፋ ውስጣዊ ውጥረትን የሚፈጥር መሆን የለበትም። ምክንያቱም በህይወት እስካለን ሞት ከእኛ ዘንድ የለም። ሞት ሲመጣ ደግሞ እኛ በሀይወት የለንም››
ኤፒካረስ ፍርሀት፣ በተለይም ፍርሀተ ሞት ለደስታ ማጣት ስረ መሰረት ነው ብሎ ያስባል። በመሆኑም ፍርሀተ ሞትን ማሸነፍ ህይወትን አስደሳች እንደሚያደርጋት ይገልጻል።
ከዚህ በመነሳት ሰዎች ሞትን እንዳይፈሩ ለማሳመን ሞጋች የሆነ ምክንያታዊ እሳቤ ያቀርባል። እንደ ኤፒካረስ አመለካከት ሞትን መፍራት አያስፈልግም።ምክንያቱም በህይወት እስካለን ድረስ ሞት የሚባል ነገር የለም። ስንሞት ደግሞ አንድም ሙሉ ለሙሉ እንጠፋለን፤ ካልሆነም ከሞት በኋላ ህይወት ይኖረናል። ከሞት በኋላ ህይወት ካለ በህይወት እያለን ስለ ሞት ልንጨነቅ አይገባም። ከሌለም ወደ ኦናነት መቀየር ነውና ከህይወት በኋላ ላለው ልንፈራና ልንጨነቅ አይገባም። በመሆኑም በማንኛውም መልኩ ሞትን መፍራት አላስፈላጊ ነው።