ሳባ ሚድያ⛲ Sabawi


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣቹ ዩቲብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👉👉👉 https://youtu.be/Jl8O2VzYRJM
👉👉👉👉👉 https://youtu.be/MXnbplyjW2Y

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ከላይ የቀጠለ
ዓለም ላይ ካሉ እጅግ ሀብታም ቤተሰቦች አንዱ እነሱ ናቸው። ኢንግሊዞቹን ተጠቅመው ከኢራን/ፐርሺያ ከህንድ ወዘተ ተዝቆ የማያልቅ ወርቅ ዘርፈዋል። የኢንግሊዙን British east india ድርጅት ተጠቅመው ለቻይና ህዝብ ኦፒየም ዕፅ እየነገዱ የትየለሌ ሀብት አፍርተዋል። ይህ ንግድ እጅግ አትራፊ ከመሆኑ የተነሳ ለኢንዱስትሪ አብዮቱ ዘመንም ጭምር መነሻ ካፒታል ለመሆን የበቃ ነው። እንደ ሆንግ ኮንግ እና ሻንጋይ ያሉ ከተሞች የዚህ ንግድ ማሳለጫ ማዕከል የነበሩ ናቸው። በዚህም ሮዝቻይልዶች ከሩቅ ምስራቅ እስከ አውሮፓ ሁሉን የተቆጣጠሩ ነበር። የአውሮፓ መሪዎችና ነገስታት ይፈሯቸው ነበር። ነገር ግን ሀብታቸው በዚህ ሁሉ የሚገለጽ አልነበረም። ከዚህም እጅግ እጅግ የሚበልጥ ሀብት ነበራቸው። ሀብታም ከመሆናቸው የተነሳ ማንም የነሱን ቤተሰብ እንዲያገባ አይፈቅዱም። የቤተሰቡ የመጀመሪያ ሰው የሚባለው ሜየር ሮዝቻይልድ አምስት ወንድና አምስት ሴት ልጆች ነበሩት። ሀብቱን ማንም እንዳይወስደው በማለት ብቻ ወንዶቹን ልጆች ከሴቶቹ አጋብቷል። ከዚህ በኋላ አንዱ ወንድም የኢንግሊዝ ንጉስን ሲይዝ አንዱ በፈረንሳይ ናፖሊይንን እያታለለ ይይዝ ነበር። ቤተሰባቸውም እያደገ ሄዶ የተለያዩ ቅርጫፎች ቢመሠርትም አሁንም እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ናቸው። ምናልባትም የንጉስ ሰሎሞን ሀብት በእጃቸው ያሉት የመጨረሻው እነሱ ናቸው።


የሰሎሞን ሀብት ወዴት ገባ?

ንጉስ ሰሎሞን በዓለማችን ከነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ሀብታም እንደነበረ ይታወቃል። እግዚአብሔር በገባለት ቃልኪዳን መሠረት ከዛን ጀምሮ እስከ ዓለም ፍፃሜ ከርሱ በላይ ሀብታም እንደማይኖር ቃል ገብቶለታል። ስለዚህ እግዚአብሔር ደግሞ ቃልኪዳኑን የሚጠብቅና ፈጽሞ የማይረሳ፣ ለዘለዓለምም የሚገጠብቅ በመሆኑ ንጉስ ሰሎሞን እስከዛሬ ድረስ ከተነሱ፣ ወደፊትም ከሚነሱ መንግስታትና ባለሀብቶች በላይ ሀብት ነበረው ማለት ነው። ስለዚህ ያ ሁሉ ሀብት ዛሬ የት ደረሰ? ብዙ ሰዎች ስለ ታቦተ ጽዮን፣ ወይም ስለ ቅዱሱ ጽዋ ወይም ስለ ንጉሱ ቀለበት አበክረው ይጠይቃሉ። ስለ ሀብቱ ግን የሚጠይቅ ብዙም ሰው የለም።

ከሰሎሞን በኋላ በነበሩት የእስራኤል ነገስታት ወቅት የእስራኤል መንግስት እየተዳከመ እንደሄደ ከታሪኩ እንረዳለን። የሰሎሞን ልጅ ሮብአም የሽማግሌዎችን ምክር ንቆ የጓደኞቹን ክፉ ምክር በመቀበሉ መንግስቱ ላይ ትልቅ ጉዳት አድርሷል። ከሱ በኋላ የነበሩ እንደ ህዝቅያስ የነበሩትም የአሶርን መንግስት መቋቋም አቅቷቸው በእግዚአብሔር እርዳታ የተረፉበት አለ። በኋላም በባሊሎን መንግስት ሁለት ጊዜ ተወርረው ለስደት ተዳርገዋል። የሰሎሞን ቤተመቅደስም የመፍረስ አደጋ ደርሶበታል። ምናልባት ሰሎሞን ሀብቱን በቤተመቅደሱ ሰውሮት ይሆን? ያ ከሆነ ሀብቱን በከፊልም ቢሆን ባቢሎናውያን ወስደውት ይሆን? ያ ከሆነ ቀጥሎ የተነሳው የፋርስ መንግስትም ያንን የተወሰነውን ሀብት ይዞ አስቀጥሎ ይሆናል።

በዚህ መሃልም ንጉስ ሰሎሞን ከንግስት ማክዳ የወለደው ልጅ አባቱን ሊጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ታቦተ ጽዮንን እና ከ12ቱም የእስራኤል ነገድ ወንዶችና ሴቶችን አድርጎ ሸኝቶታል። በዚህም ጋር አብሮ ከሀብቱ የተወሰነውን ሰጥቶት ይሆን?

አንድ ሰው ከዚህ በፊት ባጠናው ጥናት የሮዝቻይልድ ቤተሰቦች ከኢንግሊዝ የንጉሳውያን ቤተሰቦች ጋር በመሆን በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ወርቅና ሌሎችም ሀብት ከፋርስ ኢምፓየር እንደዘረፉ ጠቅሷል። የሮዝቻይልድ ቤተሰብ የሀብታቸው ምንጭ ከዚህ ይሆን? ይህኛውን ነጥብ እንመለስበታለን።

ከዚህ በኋላ የሮም መንግስትም ኢየሩሳሌምን በ70 ዓም አይሁዶች ባመጹበት ወቅት አፍርሷታል። ሁለተኛው የሰሎሞን ቤተመቅደስም በዚህ ጊዜ ፈርሷል። ሮማውያን በቤተመቅደሱ ከነበረው የሰሎሞን ሀብት የተወሰነውን ወስደው ይሆናል። በኋላ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ሮም ፈርሳ ወደ ትናንሽ የከተማ ግዛቶች በተቀየረች ጊዜ ከነዚህ ግዛቶች በአንዷ በፍሎረንስ ገዢ የነበሩት የ ሜዲቺ ቤተሰቦች ባንከሮች እና እጅግ ባለሀብት ነበሩ። ከነዚህ ዳይናስቲ ውስጥም እነ ኮስሞ ዲ ሜዲቺ እና ሎሬንዞ ዲ ሜዲቺ ይጠቀሳሉ። ሎሬንዞ ሜዲቺ ከሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ ጋር በአንድ ዘመን የነበረ ነው። አሁን ላይ የወጡ መረጃዎች የሚያሳዩት እነዚህ የሜዲቺ ቤተሰቦች የሚገኙት ከሮማውያን ጋር ከተቀላቀሉ አይሁዳውያን ዘር ነው። ምናልባት የነዚህ ቤተሰቦች ሀብት ከዚያ የሰሎሞን ሀብት በሆነ መልኩ ያለፈ ይሆን?

ከዳቪንቺ ዘመን ትንሽ ወደኋላ መለስ ስንል ደግሞ የመስቀል ጦርነት ዘመንን እናገኛለን። ይህ ጦርነት በሙስሊሞች እና በካቶሊኮች መካከል የተረጉ ተከታታይ ጦርነቶችን የሚመለከት ነው። ዓላማውም ቅድስቲቱን ምድር ከሙስሊሞች መጠበቅ የሚል ነበር። በተለይ ኢየሩሳሌም በሁለቱም ወገን እጅግ የምትፈለግና በሷም ምክንያት ብዙ ጦርነት የተካሄደባት ነው። ሙስሊሞቹ ያችን ከተማ ለምን ፈለጓት? ከሃይማኖታዊ ዓላማው ውጪ ማለት ነው። ከመካና መዲና እኩል ዋጋ ለምን ሊሰጧት ፈለጉ? የሰሎሞን ቤተመቅደስ ላይ ትልቅ መስጊድ መስራትስ ለምን ያን ያህል አጓጓቸው? የሀብቱ ነገር አሳስቧቸው ይሆን?

በዚሁ ጦርነት ወቅት ደግሞ ናይትስ ቴምፕላር የሚባሉትንም እናገኛለን። በካቶሊኮቹ ወገን ሊዋጉ የመጡት የፈረንሳይ ወታደሮች ውጊያውን ትተው ነበር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት። በዚያም ኢየሩሳሌምን ሊጎበኙ የሚመጡ ሰዎችን ከተለያዩ ሽፍታዎችና ዘራፊዎች እንጠብቃለን ብለው ነበር ለንጉሱ ሀሳብ ያቀረቡት። ከዚያም ጊዜያቸውን በሙሉ የሰሎሞንን ቤተመቅደስ በማሰስ ነበር የሚያሳልፉት። ከጊዜ በኋላ የባንክ ስርአትን አስጀምረው ከአውሮፓ የሚመጡ ተጓዦችን ኮሚሽን እየተቀበሉ ገንዘባቸውን በመያዝ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ይመልሱ ነበር። ይህም በአውሮፓ ታዋቂ አደረጋቸው። ነገር ግን ሀብታቸው እጅግ የተጋነነ ነበር። በመላው አውሮፓ የነሱን ያህል ሀብት ያለው ጠፋ። እነሱን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ሰዎች የትየለሌ ሆኑ። ሀብታም ከመሆናቸው የተነሳ በአንድ ወቅት የፓሪስን አንድ ሶስተኛ የሚቆጣጠሩት እነሱ ሆኑ።

ታዲያ እነዚህ ቴምፕላሮች አይሁድ እንደነበሩ አሁን ተደርሶበታል። በጊዜው በፈረንሳይና ስፔን የተበተኑ አይሁዳውያን በብዛት ነበሩ። ስለዚህ ቴምፕላሮቹም ከዚያ የመጡ ይሆናሉ። ደግሞም ለቤተመቅደሱ እጅግ ትልቅ ቦታ የነበራቸው መሆኑ በትውፊት የሚያውቁት ሊሆን እንደሚችል ያሳያል። ከሁሉም በላይ ግን የሚያደርጓቸው ድርጊቶች አይሁድነታቸውን ያሳብቁ ነበር። እነሱን መቀላቀል የሚፈልግ ሰው መስፈርቱ ክርስቶስን መካድ እና በመስቀሉ ላይ መትፋት ነበር። በዚያ ሃይማኖት በገነነበት ዘመን ክርስትናን በዚህ ልክ የሚጠላ ከአይሁድ በላይ ማን አለ? ሙስሊሞች እንዳንል ሙስሊሞች ክርስቶስንና እናቱን ጭምር ያከብራሉ። ለሱም ትልቅ ቦታ አላቸው። ያው አምላክ መሆኑን ባይቀበሉም እንኳ። አይሁድ ግን ፍጹም የክርስቶስ ጥላቻ ነው ያላቸው።

ታዲያ ይህ የቴምፕላሮች ድርጊት ለፍጻሜያቸው ያደረሳቸው ሲሆን፣ የሰሎሞን ሀብት ወዴት ደረሰ ለሚለው ጥያቄም ሌላ ፍንጭ ይሰጣል። የካቶሊኩ ጳጳስ ቴምፕላሮችን የፈረንሳዩ ንጉስ ዘንድ ይከሳቸዋል። ከፍተኛ መረጃም ለንጉሱ ይቀርባል። ንጉሱም በአንድ ጀምበር ቴምፕላሮችን በሙሉ ልቅምቅም አድርጎ ይጨርሳቸዋል። መሪዎቹንም ይዞ ለወራት የፈጀ የችሎት ሂደት ካካሄደ በኋላ በመጨረሻም ዋናው መሪያቸው ሂዩስ ደ-ፔይንስ ከነነፍሱ ተቃጥሎ እንዲሞት ያደርገዋል። የተወሰኑ ቴምፕላሮች ግን ወደ እስኮትላንድ ይሸሹና ሲንክሌር የሚባል ካቴድራል ውስጥ ይሸሸጋሉ። ይህ ካቴድራል በኋላ ላይ እነ አይዛክ ኒውተንን ጨምሮ የብዙ ፍሪሜሰኖች መነኻርያ ሆኗል።

ታዲያ እነዚህ ቴምፕላሮች በዚሁ ሳሉ ውስጥ ለውስጥ ፍሪሜሰንሪን ፈጠሩ። የራሱን ሚስጥራዊ መዋቅርም ሰሩለት። በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን አዳም ዋይስሆፕት ሰርጎ በመግባት መዋቅሩን እስኪቀይረው ድረስም በዚያ መዋቅር ቀጠሉ። በኋላም ኢሉሚናቲን ከመሠረቱ በኋላ የፈረንሳይ አብዮትን ያስነሱና ንጉሱን አንገቱን ይቆርጡታል። ከዚያም የንጉሱን አንገት ከፍ አድርገው ከያዙ በኋላ ለቴምፕላሩ ሂዩስ ዴ-ፔይንስ ደም መልሰናል እንዳሉ ይነገራል።

ታዲያ አዳም ዋይስሆፕት የፍሪሜሰንን መዋቅር ገብቶ የቀየረውና ኢሉሚናቲንም የመሠረተው በሮዝቻይል ቤተሰብ ቀጥታ ትዕዛዝ ነው። የቴምፕላሮች ሀብትም የወደቀው ከሮዝቻይልዶች እጅ ነው። በዚህም ሀብት የተነሳ እስካሁን በዓለም የነሱን ያህል ሀብት ያለው የለም። አንዳንዶች ሀብታቸው እስከ 500 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ እስካሁን ከሚታወቁት ወይም ከተመዘገቡት ክስተቶች ብቻ በመነሳት ሀብታቸውን እስከ 1-2 ትሪሊዮን ይገምታሉ። ለንጽጽር ያህል አጠቃላይ የአሜሪካ ሀብት 12 ትሪሊዮን ነው። እነዚህ ሰዎች ከኢንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች ጋር ተዋልደዋል። ከነሱም ጋር ከፍተኛ ሀብትና ስልጣን ተካፍለዋል።


ከሰሞኑ በከተማው ነጮች እየበዙ መጥተዋል። ከድሮ በተለየ መልኩ በየቦታው ይታያሉ። በዛ ማለት ከጀመሩ ሰንብተዋል። ከነሱ መምጣት ቀድሞ ደግሞ ሀገራችን ደምቃለች አሸብርቃለች የሚለው ሀሳብ እንዲዳረስ የተደረገበት መንገድ አለ። ልክ አንድ ሰው ትልቅ እንግዳ ሲኖርበት ቤቱን አፅድቶ አሳምሮ፣ አሽሞንሙኖ እንደሚጠብቀው ማለት ነው።

ከዚህ በፊት እንዳነሳነው ሀገራችን ለዘመናት ያልለመደባትን ለውጩው ዓለም ክፍት ሆናለች፤ በኒዮ ሊበራሊዝም እሳቤ መሠረት። ነጮች ዓለም አቀፍ ኢምፓየራቸውን የሚገዙበትን የኒዮ ሊበራሊዝም እሳቤ በየቦታው ተግብረውታል። ሁሉም የዓለም ሀገራት ለነሱ ጥቅማቸው መዝናኛ የሚያደርጉባቸው፣ ለቫኬሽን የሚሄዱባቸው፣ በተለያዩ የወሲብ ንግድና እፅ ወዘተ ተግባራት ተሳትፈው ፈታ ካሉ በኋላ ወደቀደመ ኑሯቸው የሚመለሱበት ነው። ይህንንም ለመተግበር ደግሞ ቀጣይዋ ሀገር ሀገራችን ናት።

ለዚህ ነው አሁን ሲመጡ ደና ነገር ይዘው አይመጡም። የወሲብ ንግድ፣ የዕፅ ዝውውር፣ ፖርን ጭምር በሀገራችን የሚስፋፋበት ጊዜ ይመጣል። በምላሹ ደግሞ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት፣ ማዕድን፣ ገንዘብ፣ ዕፅዋት ሁሉ ጠራርገው ይዘው ይሄዳሉ።

ነጮች በኢትዮጵያ ለመኖር ካለሙና ካቀዱ ዘመናት ተቆጥረዋል። እኛ ሳናውቀው ቀስ በቀስ የሀገራችንን ስነ ምህዳር ለነሱ በሚመቻቸው መልኩ እየቀየሩ ነበር። በአበባ፣ በችግኝ እየተሳበበ እንግዳ ዕፅዋትን ይገቡ ነበር። የቤት እንስሳት ሳይቀር የፈረንጅ ውሻ እየተባለ ቀስ በቀስ በሀገር ውስጥ ያሉ ዝርያዎች እየጠፉ፣ ላሞች የተሻለ ወተት አላቸው በሚል የፈረንጅ ላም እየተራባ እና ከሀበሻም ጋር እየተዳቀለ፣ ዶሮም በተመሳሳይ በGMO እየተቀየረ መጥቷል። ኢትዮጵያ ያላትን እጅግ ድንቅ የሆነ የዘረመል (genetics) ሀብት ሙልጭ አድርገው ወስደው የቀረውን ዘርፈው የራሳቸው ሊያደርጉ ይሻሉ። ይህንን ዝርፊያ ከሚፈጽሙበት መንገድ አንዱ ደግሞ ፓተንት የሚባለው ነው። ለምሳሌ አንዱ የኔዘርላንድ ድርጅት ጤፍን የራሱ ፓተንት አድርጎ ሊወስድ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ይህንን ጉዳይ ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ "ራማቶሐራ" በተሰኘው መጽሐፉ በደምብ ገልፆታል።

ታዲያ እንደነሱ እቅድ ከሆነ የሀገራችንን ሀብት ጠራርገው ወስደው ስለማይበቃቸው የኢትዮጵያ የጄኔቲክስም ሆነ የስነ ምህዳር ሀብት ተዝቆ ስለማያልቅ፣ ወስደው ከሚጨርሱ ይልቅ እዚሁ መጥተው ሊጠቀሙበትም ይሻሉ። ለዚህም ነው እዚህ በብዛት መጥተው ለመኖር የሚፈልጉት። እኛን በተለያየ ሰበብ አጣልተው አጫርሰው፣ ከኛ የተረፉትም የነሱ ባርያ እንዲሆኑ አድርገው ሊኖሩ ይሻሉ። በፍጹም አትጠራጠሩ እኛ መካከል ከሚደረገው ማለቂያ የሌለው ጦርነት ጀርባ የነሱ እጅ አለበት። ይህንን የሚያደርጉበት ብዙ በመርህና በፍልስፍና ደረጃ የተቀመጡ እሳቤዎች ላይ ተመሥርተው ነው። ለአንዳንዶች eugenics ወይም እንደነሱ ምርጥ ዘር ያልሆነው ሁሉ እንዲያልቅ ስለሚመኙ ነው። (ይህ ውሸት ከመሰላችሁ፣ DNAን ያገኘው ሳይንቲስት ጭምር በዚህ ያምናል)። ሌሎቹ ደግሞ የdepopulation ፖሊሲ ስለሚፈጸም ነው። ነጮች ሌላውን conspiracy theory ቢቃወሙ እንኳ ይሄኛው ግን ነጭ ባልሆኑ ህዝቦች ላይ እስከደረሰ ድረስ ችግር የለባቸውም። ሌላው ቀርቶ abortion እና የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ነጮች እንኳ በጥቁሮች ላይ እስከሆነ ድረስ ችግር የለውም የሚሉ ናቸው። ለኛ ያላቸው ቦታ ይህ ነው። እዚህም የሚመጡት ይህን አስተሳሰብ እና ርዕዮተ-ዓለም አዝለው ነው።'


4-3-3 World News dan repost
በተለምዶ korbe ኦሮምያ ክልል ውስጥ የሚገኝ ቦታ ላይ በድጋሜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

በዚ የመሬት መንቀጥቀጥ 4.6 rector scale አስመዝግቧል

@Ethionews433 @Ethionews433


4-3-3 World News dan repost
የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል

ዛሬ ጠዋት ከሰዓታት በፊት 1:38 በአዋሽ ከተማ ባለፈው ሳምንት ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጨመር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የተነገረ ሲሆን

ከዚህ በተጨማሪ በአደስ አበባ በአዳማ ከተማም ተመሳሳይ ንዝረት መሰማቱን በርካታ ሰዎች እየገለፁ ይገኛል።

#ዳጉ_ጆርናል

@Ethionews433 @Ethionews433


ሰባተኛው ፊደል

ይህ ሆሄ በቀመር ሲቆጠር አስረኛ ነው።
"ቶ" በመልካ ፊደሉ ሰው መሳይ ነው። ባለ ስድስት መቶ ገቢር ፈዋሽ ዕፅም"ዕፀ ልባዊትም" ቅርጿ መሳይ ናት።
'ቶ' ቃል ሥጋ ሆነ የሚለውን ምስጢር ይዟል።

"ቃል" የሚለው ፊደል በቀመር ሲተነተን
ቀ= 8 ነው።
ለ=2 ነው።
ድምር=10 ይሆናል።
10 ደግሞ የ "ቶ" ፊደል መነሻ የ'ተ' ቀመር ነው።
'ቶ' በፈጣሪ መንፈስ ነፀብራቅነት ለሙሴ ተሰጥታ ባህርን የከፈለች ዘንግ ናት።
ይህ ለመግቢያ የተፃፈ የ'ቶ' ፊደል ትርጉም ነው። ሙሉ ታሪኩን እናንተ አንብቡት።
ዋና ምንጭ፦የወርቅ ዘንግ መፅሐፍ በመስፍን ሰሎሞን  MESFIN SELOMON(የስነ_ፊደል_ተመራማሪ)

"የጥንት ኢትዮጵያውያን ድንቅ ምርምሮች"
"የጥንት ኢትዮጵያውያን ድንቅ ምርምሮች"


የማንን ሃሳብ፣ በማን ጭንቅላት እያሰባችሁ ነው?

( ብዙ ጭንቅላቶች ቢኖሩም፣ ብዙ ሀሳበች የሉም)
የሰው ልጅ አሳቢ ፍጡር ነው ቢባልም አብዛኛው ግን አይደለም፡፡ ብዙሃኑ ታስቦ ያለቀ አሳብ እራሱ ላይ ጭኖ የሚሄድ መንገደኛ ነው፡፡ ግቡ መሄዱ እንጂ መድረሱ አይደለም፡፡ “ለምን” የሚባል ጥያቄ ጠላቱ ነው፡፡ በሰዎች ምላስ ጣዕምን ይለካል እንጂ፣ የራሱ ምላስ(የጣዕም ልኬት) የለውም፡፡ ኬክ ጣፋጭ ነው! አዎ ነው!! እንትን ነውር ነው! አዎ ነውር ነው!! የእንትና መፅሐፍ አሪፍ ነው! አዎ በጣም ብዙ ሰው ይወደዋል አሪፍ ነው! እንዲህ ነው ብዙሀኑ-ገደል ማሚቱ!
የያዛችሁትን ሀሳብ ለምን ያዛችሁ ? ብዙሀን ስለተከተሉት? ብዙሃን ስለተከተሉት በቡዝሀን ሀሳብ ብቻ ትክክል ሆኖ የሚያውቅ ሀሳብ አለ፡፡ ትክክል በመሆኑ ብዙዎች የተከተሉት ሀሳብ ይኖር ይሆናል፣ ብዙሃን ስለተከተሉት እውነት የሆነ ሀሳብ ግን በፍፁም! የያዝከውን ሀሳብ ትጠይቃላችሁ? ለምን እንዲህ አመንኩ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ ወይስ ለምን ከሚባል ጥያቄ እስከ አለም ጥግ ትሸሻላችሁ፡፡

ሃሳባችሁ ማን ሰራሽ ነው? ሃይማኖት ሰራሽ? ማህበረሰብ ሰራሽ? ቤተሰብ ሰራሽ? ነው ቅልቅል? ግርር ብሎ ማሰብ ትልልቅ ሰዎችን ፈጥሮ አያውቅም- ባለህበት እርገጥ እንጂ፣ ወደ ፊት! የለውም፡፡ ታላቅነት “ለምን” በምትል ጥያቄ ውስጥ ነው የሚወለደው፡፡ ነፃ መሆን፣ ወይም የብዙሃኑ ቡችላ መሆን የግለሰቡ ምርጫ ነው፡፡ እንደተመረጠልህ መኖር ወይስ እንደመረጥከው መጓዝ፡፡

ትልቁ ጥያቄ- የያዝከውን አቋም የመፈተሸ ድፍረት አለህ ወይ? ለሃይማኖትህ መልስ የምትሰጠው ከሰባኪያን ከለቀምከው ቃል ነው ወይስ የሀይማኖት መፃሕፍትህን መርምረህ ከደረስክበት? መፀሐፍቱን ስታነብስ አራት ነጥብ እያደረክ ነው የምታነበው ወይስ ጥያቄ ምልክት ታስቀምጣለህ በመሃል? ያለመጠየቅ ሙቀት ይሻልሀል፣ የመጠየቅ ገነት? ሳይጠየቁ የኖሩ አዲስ እውነት አፍጦ በመጣባቸው ጊዜ ያብዳሉ፡፡

“ ያልተመረመረ ህይወት ዋጋ ቢስ ነው” ይላል ጋሽ ሶቅራጥስ፡፡ የኛው ሌሊሳ ደግሞ፣
“ ሕይወትን ሂስ ማድረግ የማይችል ዘመን የፈጠራ መንፈስ አይኖረውም” ይላል ፡፡ ዘመን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን ሂስ የማያዳረግ ሰውም እንደዛው ነው፡፡ እርግጥ በመመርመር የሚመጡብህ ቅጣቶች አሉ፡፡ አንደኛው የለውጥ ስቃይ ነው፡፡ የቀደመ አስተሳሰብን መለወጥ ለብዙዎች ስቃይ ነው፡፡ አንዳንዱ እዚህ ድረስ መጥቼ እንዴት እመለሳለው ብሎ፣ በጀመረው የስህተት መንገድ መንገድ ይመርጣል( አዲሱ መንገድ ትክክል እንደሆነ ቢያውቅም፣ የኖረበትን መንገድ መልቀቅ ሞቱ ነው)፣ ሌላኛው በስቃይም ቢሆን አዲሱን እውነት ይቀበላል፡፡

እናንተ የየትኛው ዘመን ሃሳብ ባሪያዎች ናችሁ? ለየትኛው ሰው? ለየትኛው ድርጅት?….
መንግድህ እያሳየህ ያለው ከሌሎች ባትሪ የሚወጣው ብርሀን ነው ወይስ የራስህ ባትሪ አለህ? ስንት ሃይማኖት መርምረህ ያንተ ሃይማኖት ልክ መሆኑን አወክ? ስንት ማህበረሰብ አይተህ አንተ ያለህበት ማህበረሰብ አስተሳሰብ ልክ መሆኑን አመንክ? የስንት ህዝብ ባህል ፈትሸህ፣ የባህልህ ተገዢ ሆንክ? “ባህላችን” ስትል ምን ማለትህ ነው? ሙሉ ለሙሉ እንከን የማይወጣለት ባህል አለኝ ነው የምትል ወይስ ባህሉ “የአንተ ስለሆነ” ብቻ ልክ ነው? የትኛው ባህልስ ነው ልክ? ባህል እንደሚሻሻል እንደሚለወጥ ታምናለህ ወይስ ለአያቶችህ መንፈስ የመታመን እዳ በላይህ ላይ ጭነሃል?

"የማን ሆናችኋል? ማን እየሾፈራችሁ፣ ማን እየዘወረን ነው? “

ጥያቄው የማንን ጭነት ተሸክማችኋል ነው፡፡ የራሳችሁን ሸክም ነው የሌላውን የተሸከማችሁት? ……ሸክማችሁ የከበደ እናንተ ሸክማችሁን ጣሉ….! የራሳችሁን ሸክም ብቻ ተሸከሙ፡፡ ማንነታችሁንና ዘመናችሁን በማይመጥን ሸክም ትከሻችሁን አታጉብጡ፡፡

“ ብዙ ያማሩ ጭንቅላቶችን፣ ብዙ ያማሩ ቡድኖች ውስጥ ገድለን ቀበርን! ብዙ ሃሳብ ያላቸው ጥቂት ሰዎች እንጂ፣ ጥቂት ሃሳብ ያላቸው ብዙ ሰዎች ምን ይረቡናል? በቡድን ውስጥ የሚጨፈለቀው እኔ ለራሱም ለሌላውም የሚፈይደው የለውም፡፡ እንዲያ ማለት አብዝተህ እራስህን ውደድ አይደለም፣ የሌሎችን ህልውና ጨፍልቅ አይደለም! – የራህን ጫማ አድርግ ማለት ነው፡፡ ያባትህ ጫማ ያንተ አይደለም- ላንተም አይደለም! መንገድ ላይ ከርፈፍ ከርፈፍ እያልክ ከመሄድ ውጪ የሚያተርፍልህ የለም፡፡ አንቺም የእናትሽን ጫማ አውልቀሽ ጣዪ፡፡ ማን እንደሰራው ከማታውቂው፣ ከሚያወለካክፍሽ ጫማም እራስሽን ጠብቂ፡፡

በመጨረሻም፣ እራሳቸውን ችለው የሚያስቡ ጭንቅላቶች ያብዛልን!!


'ብላ ፣ ጠጣ ፣ ተደሰት ነገ ሟች ነህና!>

                                         ሄዶኒዝም

ምንጭ ፦ ከፈላስፎች ዓለም
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ

የህይወት ተቀዳሚ አላማ ደስታን አግኝቶ ስቃይን ማስወገድ ነው። እያንዳንዱ እንቅስቃሴና ድርጊት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከዚህ ውስጣዊ ፍላጎት ይመነጫል።

በሄዶኒዝም ፍልስፍና መሰረት የሰው ልጅ የሞራል ግዴታ አንድና አንድ ነው ደስታን አግኝቶ ስቃይን ማስወገድ በሌላ አገላለጽ ደስታ ለማግኘት ያለውን ጥልቅ ጉጉት ማሟላትና በተቻለው አቅም ስቃይን ማጥፋት፡ ካልሆነም መቀነስ።

በሄዶኒዝም ፍልስፍና ውስጥ የተለያዩ ፈርጆች አሉ። አንዳንዶቹ ቅጽበታዊ ለሆኑ ስሜታዊ ፈንጠዝያዎች ትኩረት ሲሰጡ አንዳንዶቹ ደግሞ ለመንፈሳዊ የደስታ ምንጮች ቅድሚያ ይሰጣሉ።

አሪስቲፐስን የመሳሰሉ ሄዶኒስቶች አካላዊ ደስታ የህይወት ተቀዳሚ ግብ እንደሆነ ይሰብካሉ። በአሪስቲፐስ ፍልስፍና መሰረት ደስታ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት እንደመሆኑ ሰዎች ህይወት የቸረቻቸውን አጋጣሚ አሟጠው መጠቀም አለባቸው።

አካላዊና መንፈሳዊ ተብሎ የሚፈረጅ የደስታ ምንጭ የለም። መሰረታዊው ነገር በተገኘው አጋጣሚ መደሰት፣ በተቻለን አቅም ስቃይን ማስወገድ እስከሆነ ድረስ ማንኛውም አይነት የደስታ ቅጽበት መባከን የለበትም። ምክንያቱም እያንዳንዱ የደስታ ቅጽበት ተመልሶ አይገኝም። በመሆኑም የህይወት መርህ ቀላልና ፍጹም የማያወላዳ ነው - "ብላ፣ ጠጣ ተደሰት - ነገ ሟች ነህና››

የዚህ ፍልስፍና አራማጆች ከዛሬ ደስታቸው ባሻገር ስላለው ነገ አይጨነቁም። ደስታ ብቸኛው የህይወት ግብ በመሆኑ እያንዳንዱ ሰው የደስታ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ምቹ አጋጣሚዎችን ሳይሰስት መጠቀም አለበት።

ከጥንታዊ የሄዶኒዝም ፍልስፍና አራማጆች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው ኢፒካረስ ይህን አይነቱን ክፉን ከደግ ሳይለዩ ደስታን የማሳደድ መርህ ይቃወማል። ደስታ የሀይወት ታላቁ ገጸ በረከት ቢሆንም አንዳንድ የደስታ ምንጮች ጎጂ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ።

'ብላ ጠጣ፣ ተደሰት ነገ ሟች ነህና' በሚል መርህ የሚመሩ ግለሰቦች የማታ ማታ ለጉዳት መዳረጋቸው አይቀርም። ሞት በቀላሉ የሚከሰት ባለመሆኑ ሁሉም ሰው የአፍራሽ ድርጊቱን ምንዳ ለመቀበል ይገደዳል። ነገራትን ግራ ቀኝ ሳያጤኑ ባልተገራ የደስታ አሳዳጅነት ስሜት መነዳት ደስታን ሊያመናምን፣ ሊያጠፋ ወይም ከነአካቴው ደስታን ወደ ስቃይ ሊቀይር ይችላል።

ከዚህ በመነሳት ጥንታዊው ፈላስፋ ኤፒካረስ 'ደስታን የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተመሳሳይ ዋጋ የለውምና ሰዎች የደስታ ምንጮቻቸውን ለያይተው ማጤን ይኖርባቸዋል› ይለናል። የተሻለ መጻኢ ጊዜን ለመፍጠር አንዳንድ የደስታ ምንጮች መወገድ ሲኖርባቸው አንዳንድ ስቃይን ሊያስከትሉ የሚችሉ ተሞክሮዎች በጽናት ሊታለፉ ይገባል። አንድ የታመመ ሰው ጤናማ መሆን ይችል ዘንድ ጎምዛዛ መድሀኒቶችን መውሰድ ብሎም አሰቃቂ ቀዶ ጥገናዎችን ማካሄድ ይጠበቅበታል።

ለኤፒካረስ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት አስተውሎ ነው። በርግጥ ተገቢ ካልሆኑ የደስታ ምንጮች ታድጎ መልካም ወደሆኑት የሚመራን አስተዋይነት በመሆኑ መልካም የሆኑ የደስታ ምንጮችን መለያ ሚዛን ይሆናል። ለዘላቂ ስኬትና ደስታ ጊዜያዊ የስቃይ ስሜቶችን በጽናት መቋቋም ይችል ዘንድ ሰው አስተዋይ ልቡና ያስፈልገዋል።

የኤፒካረስ ፍልስፍና ደስታን ከመሻት ይልቅ ስቃይን ስለማስወገድ አጽንኦት ይሰጣል። ምክንያቱም ህይወት ራሷ ከሁሉ የላቀች ሀብት እንደመሇኗ ከስቃይ፣ ህመም፣ ፍርሀትና ሞት ጋር አብራ የምትሄድ አይደለችም።

በኤፒካረስ አገላለጽ ‹‹ደስታ የህይወት ታላቁ ገጸ በረከት ቢሆንም ይህ ደስታ ከአካላዊና ስሜታዊ ብኩንነት የሚመነጭ አይደለም" ይህ አይነቱ ደስታ በስካርና ዝሙት ህሊናን በማወር የሚገኘው ከንቱነት አይደለም። ይህ አይነቱ ደስታ ከአካላዊ ህመምና ከአእምሯዊ ስቃይ ነጻ ከመውጣት የሚገኘው እፎይታ ነው። የአእምሮ ህመም ከአካላዊው የከፋ ሲሆን ለክፋትም ሁሉ ስር ነው። አካላዊ ህመም በጽናት ሊታለፍ ይችላል። ካልታለፈም ፍጻሜው ሞት ይሆናል። ሞት ደግሞ የከፋ ውስጣዊ ውጥረትን የሚፈጥር መሆን የለበትም። ምክንያቱም በህይወት እስካለን ሞት ከእኛ ዘንድ የለም። ሞት ሲመጣ ደግሞ እኛ በሀይወት የለንም››

ኤፒካረስ ፍርሀት፣ በተለይም ፍርሀተ ሞት ለደስታ ማጣት ስረ መሰረት ነው ብሎ ያስባል። በመሆኑም ፍርሀተ ሞትን ማሸነፍ ህይወትን አስደሳች እንደሚያደርጋት ይገልጻል።

ከዚህ በመነሳት ሰዎች ሞትን እንዳይፈሩ ለማሳመን ሞጋች የሆነ ምክንያታዊ እሳቤ ያቀርባል። እንደ ኤፒካረስ አመለካከት ሞትን መፍራት አያስፈልግም።ምክንያቱም በህይወት እስካለን ድረስ ሞት የሚባል ነገር የለም። ስንሞት ደግሞ አንድም ሙሉ ለሙሉ እንጠፋለን፤ ካልሆነም ከሞት በኋላ ህይወት ይኖረናል። ከሞት በኋላ ህይወት ካለ በህይወት እያለን ስለ ሞት ልንጨነቅ አይገባም። ከሌለም ወደ ኦናነት መቀየር ነውና ከህይወት በኋላ ላለው ልንፈራና ልንጨነቅ አይገባም። በመሆኑም በማንኛውም መልኩ ሞትን መፍራት አላስፈላጊ ነው።


Remote IT ሪሞት አይቲ dan repost
ሙሉ በሙሉ ያለ አሽከርካሪ በራሱ የሚንቀሳቀስ #ሳይበርካፕ የተባለ ቴስላ ይፋ ያደረገው መኪና 💡

አዲሱ መኪና መሪም ሆነ የነዳጅ መስጫ እና የፍጥነት መቆጣጠርያ ፔዳል የለውም ተብሏል


4-3-3 Crypto dan repost
ዘጠኝ ኪሎ ግራም ወርቅ ከሴቶቹ ብልት ተገኘ።

በስድስት ሴቶች ብልት ውስጥ ተሰፍቶ ሊያልፍ የነበረ ከ9 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ በኡዝቤክ ተወላጆች ወደ ቱርክ በድብቅ ሊገባ ሲል ተያዘ።

ሙሉ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም አዳዲስ እና ትኩስ ሀገራዊ እና ዓለምአቀፍ መረጃዎች ማግኘት ከፈለጉ ይቀላቀሉን።
👇👇👇👇👇

t.me/ethionews433

@Ethionews433 @Ethionews433


#እያለህ_ካልሆነ_ከሌለህ_የለህም!

👌 ማንም ሰው ያልሰራኸውን፣ ያልጣርክበትን ነገር አምጥቶ አይሰጥህም!
ማንም ሰው በልፋት ስላመጣኸው ነገር ግድ አይሰጠውም። ብታወድመው ተው የሚልህ ማንም አይኖርም።

👌ማንም ሰው በመገለል ላሳለፍከው የስቃይ ህይወት ጉዳዩ አይደለም። ስትወድ ለተሰበርከው የሚታመምልህ ማንም የለም። ስለዚህ ያን የስቃይ ጊዜ እያሰብክ በእልህ መጣር የበለጠ የተሻለ ምርጥ ውጤት ለራስህ መሸለም ያለብህ አንተው ነህ።

ያሳለፍከውን ከባድ ህይወት ብትጽፈው፣ ብትናገረው፣ ብታለቃቅሰው አንድም ሰው እውነቱን አያውቅልህም። ስለዚህ በየተገኘህበት ምሬትህን በማሰማት ፈንታ ያንን ጊዜ በስራ፣ በማግኘት ተበቀለው።

ና ራስህን አበርታ
ና ለራስህ አመስግን
ና ራስህን አድንቅ
ና ራስህን
በማግኘት
በማሳካት
በመቀጠል
ሸልም

☑️ ህይወት ስለሌሎች አይደለም። ስለራስ የሚቆስሉት የሚታመሙት የሚድኑት ትግል ነው።


════❥━━━❥═════
     🌾ነገ መልካም ይሆናል !  🌾
💫
https://t.me/sabawitube💫#ሼር
         


All CRYPTO ET dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Cats on bitget


በድጋሚ ሊከሰት ይችላል...ግን ያን ያህል አስጊ አይደለም

በሬክታር ስኬል በ4.9 ተመዝግቧል።

ይህ በቁጥር ስታዩት ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን ከባድ ቁጥር ነው አዲስ አበባም ሆነ ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢ የምትኖሩ ሰዎች ነቅታችሁ ተጠባበቁ!

የመንግሥት ኮምኒኬሽን ማብራሪያ ስለዛሬው መሬት መንቀጥቀጥ

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሷል።በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል። በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝረቱ ከመሰማት  በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም። በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ የታየውም ንዝረቱ ነው። ክስተቱ ከሰሞኑ ጀምሮ በፈንታሌ ተራራ እና አዋሽ አካባቢዎች የነበረ ስሜት ነው። 
Play Store & App store My Earthqwake alert የሚባል አፕ አውርዳችሁ አካባቢያችሁ ላይ ሊከሰት የሚችል ማንኛውም የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ካለ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣችሁ ይችላል።
የመሬንት መንቀጥቀጡ ያጋጠማችሁ ቦታ በተለምዶ Aftershock የሚሉት ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ የሚከሰት አነስተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊኖር ስለሚችል ተጠንቀቅቃችሁ ነቅታችሁ ጠብቁ።

Aftershock ከዋናው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙም ባልቆየ ሰዓት ውስጥ ነው የሚከሰተው
ድጋሚ ከተከሰተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ያሉት መድረግ ያለበት ጥንቃቄ

➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።

➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።

➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።

ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "


ከ4.5 እስከ 4.9 ይሆናል በተባለ መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቷል

በበርካታ የከተማው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በስጋት ላይ እንደሚገኙ ተረድተናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን እናደርሳለን...


ውሻ ተከተሉ !

ውሾች 8ተኛ የስሜት ህዋስ አለቸው የዚ ህዋስ ሚናም ከሰው ቀድሞ የመሬት መንቀጥቀጥ ካለ እዛ አከባቢ ውሾች አይኖሮም እና የውሻ ድምፆች ይበርክታሉ


ሰበር

አዲስ አበባ እና አከባቢዋ ላይ 1.5-1.8 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ እንደነር ታውቋል።

ተጨማሪ መረጃዎች እንዲሁም አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ጆይን ይበሉ።


😄ንጉሡ በከተማው የሚገኝ ከሁሉ የሚበልጠውን ሊቅ እንዲያመጡለት ባለሟሎቹን አዘዘ። ባለሟሎቹን በጥበቡ፣በበማስተዋሉም እጅግ የላቀ የሚሉትን ጠቢብ አመጡለት።ንጉሡም ወደ ጠቢቡ እየተመለከተ "ሶስት ጥያቄዎች እጠይቅሃለሁ የመጀመሪያው ጥያቄዬ እግዚአብሔር የት ነው የሚኖረው?"

⭐ጠቢቡም እጅ ነስቶ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ትኩስ ወተት እና ስኳር ያስፈልገኛል አለ።ንጉሡም እንዲመጣለት አደረገ። ጠቢቡም ስኳሩን ወተት ውስጥ ጨምሮ አማስሎ ለንጉስ ሰጠው እንዲቀምሰው
"ግርማዊነቶ ወተቱ እንዴት ያለ ጣዕም አለው?" አለው
ንጉሱም"ይጣፍጣል"አለው
ጠቢቡም መልሶ"ከወተቱ ውስጥስኳሩን ማየትይቻላል? "ብሎ ጠየቀው
ንጉሱም"አይቻልም ስኳሩ ሟምቷል።"አለው
ጠቢቡም "ልክ እንደሟሟው ስኳር እግዚአብሔር ሁሉም የአለም ስፍራ ላይ አለ አናየውም እንጂ"አለው

⭐ንጉሡ በመልሱ ረክቶ ሁለተኛው ጥያቄ ጠየቀው"ፈጣሪን እንዴት ልናገኘው እንችላለን?"

🟡**ጠቢብም ግርማዊነቶ ይህንን ለመመለስ የወተት ክሬም ያስፈልገኛል አለ። ንጉሡም እንዲያመጡለት አዘዘ።
ጠቢቡም እጅ ነስቶ"ግርማዊነቶ በክሬሙ ላይ በቅቤ ይታያል?"ብሎ ጠየቀው**
ንጉሡም"ክሬሙን ብንናነሳው ቅቤ ከስር እናገኛለን ከላይ ግን አይታይም "አለው
ጠቢቡም"የሁለተኛ ጥያቄዎም መልስ እንዲህ ነው ፈጣሪም በእውነተኛ ማንነታችንን ወደ ልባችንን ስንመለስ እናገኘዋለን"አለው።

🟡ንጉሡም በጠቢቡ ተደንቆ ወደ መጨረሻው ጥያቄ አለፈ"እግዚአብሔር ምን ማድረግ ይቻለዋል? "አለው

ጠቢቡም ከንጉሡ ሎሌዎች አንዱ እንዲቀርብለት ጠየቀ። ንጉሡም አስጠራለት። ጠቢቡም"ይህ ጠባቂዎ ንጉሠ ነገሥት ነው እንበል እናም ግርማዊነቶ ለንጉሥ ዙፋን ይገባዋል እና እርሶ ከእኔ ለጎን ይቆማሉ ጠባቂዎ ደሞ በዙፋኖ ይቀመጣል "አለ
ንጉሱም በመስማማት ዙፋኑን ለሎሌው ለቀቀ።
ጠቢቡ ወደ ንጉሡ እያየ" ፈጣሪ ሎሌን ጌታ፤ጌታን ሎሌ ማረግ ይችላል"አለው።
***

https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_5896210150


Cherry game Task ለሚሰሩ ሰዎችና እና Invite ለሚያደርጉ ሰዎች በአጠቃላይ 70 ሺ ዶላር የሚያስገኝ ሽልማት አዘጋጅቷል ።

ይሄ ኤርድሮፕ ሚጠናቀቀውም በ13 ቀናት ውስጥ ሲሆን ብርም ለማግኘትም ብዙ ጊዜያትን አይወስድም ።

እናንተም 3 ሰው Invite አርጋቹ Task ሰርታቹ የውድድሩ ተካፋይ መሆን እንዳትዘነጉ

➩ 13 Days left .....

ለመጀመር 👇
https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_5896210150


DV 2026 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
DV-2026 Program Instructions

↘️እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

➡️ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ /ያጠናቀቀች። ወይም
➡️ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።

↘️የ DV አሞላል ሂደቶች:-

➡️ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት።

↘️ፎርም አሞላል‼️
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት - የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
➡️ በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።

8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

↘️በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2026 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2026 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ
🏃🏃🏃🏃🏃🏃🏃🏃
መልካም ዕድል ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ማረግ አይርሱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+9Uk5umy2wo00MDk0


ውድ ቤተሰቦች X Empire አዲሱ chill phase ጀምሯል አሁኑኑ ጀምሩ ከዚህ በፊት ያልጀመራችሁ በዚህ ሊንክ ስትጀምሩ ቦነስ ይሰጣችኋል። ፍጠኑ በደንብ ስሩ።http://t.me/empirebot/game?startapp=hero5896210150

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.