የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
🔹እውቀት ማለት አሏህን መፍራት ነው
የመጽሐፍ ብዛት ፣ የእውቀት ብዛት ፣ ለሚፈለገው የሸሪዓ እውቀት መለኪያ ሊሆን አይችልም።
እውቀት ማለት ራስን ጠቅሞ ሌላውን የጠቀመ ነው - እውቀቱ አነስተኛ ፣ መጽሐፉ አነስተኛ ቢሆንም።
እውቀት ብሎ ማለት በአቂዳም ፣ በመንሐጅም ፣ በእርሱ የተጠቀመበትና የፈየደው ነው።
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል :-
"አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ፣ አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው።" (ፋጢር : 28)
ሰለፎች "እውቀት ማለት አላህን መፍራት ነው" ይላሉ።
አላህን ሳይፈራ ፣ ብዙ እውቀት ካየህበት ይህ ሰው ትክክለኛ አሊም አለመሆኑን እወቅ። እንዲህ አይነቱ ሰው ለእውቀቱ ግምት አይሰጠውም - እውቀቱ በእርሱ ላይ ጥፋት ይሆንበታልና።
ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ረሱል - ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል :-
"ቁርአን ለአንተ ማስረጃ ይሆናል ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ይሆንብሀል።"
ቁርአን ፣ ሱና ፣ ሸሪዓዊ እውቀት በእርሱ ላይ ማስረጃ የሆነበት ሰው ምን አስከፊ አደረገው!
እንዲህ አይነቱ ሰው መጽሐፎቹ ቢበዙ ፣ እርሱ ግን ጠማማ ነው። በቋንቋ ፣ በተፍሲር ፣ በሐዲስ ብዙ እውቀት ቢኖረውም ፣ እርሱ ግን ጠማማ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ብዙ ይናገራሉ ፣ ነገር ግን ከእነርሱ ዘንድ ተግባር የለም።
ትክክለኛ ሙስሊም እርሱ ተግብሮ ሰዎችን ወደ ተግባር የሚቀሰቅስ ነው። ሱናን አጥብቆ ይዞ ሰዎችን ወደ ሱና የሚጠራ፣ ቢድዓን የሚዋጋ ነው። "ጠቃሚ እውቀት" ማለት ይህ ነው።
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል:-
"እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን?"
(በቀራ :44)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?"
(ሶፍ :5)
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة