አቡ ዐብዲላህ ሰዕድ ዐብዱለጢፍ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


فلواحد كن واحدا في واحد
👇 👇 👇
«فلواحد» وهو الله عز وجل، وهذا هو توحيد المراد.
«كن واحدًا» في عزمك وصدقك وإرادتك، وهذا هو توحيد الإرادة.
«في واحد» وهو متابعة الرسول الذي هو طريق الحق والإيمان.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




Bahiru Teka dan repost
🚫   እውነትም እንቁ – ጣጣሽ

     እንቁ የሚለው ቃል እኔ የማውቀው የከበረ ማእድን መሆኑን ነው ። እኛ ሀገር ግን ዘመን መለወጫ ላይ የሚወጣን አበባ ለመግለፅ ይጠቀሙበታል ። በእነርሱ እይታ አበባዋና ጣጣዋ ምን እንደሆነ ባላውቅም በኔ እይታ ግን የዘመን መለወጫን ተክትላ የምትመጣው እንቁ ብዙ ጣጣ አላት ። በሌላ አባባል ዘመን መለወጫው ብዙ ጣጣ አለው ።
     ከሁሉም በፊት ይህ ባአል ከክርስትና እምነት ጋራ የተገናኘ ስለሆነ ሙስሊሞችን አይመለከትም ። ሙስሊሞች በአመት ሁለት ዒድ ( ባአል አላቸው) እነርሱም ዒደል አድሓና ዒደል ፊጥር ናቸው ። የዘመን አቆጣጠራቸውም የአላህ መልእክተኛ ወደ መዲና ሂጅራ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ በሂጅሪያ ነው የሚቆጥሩት ። በዚህ አቆጣጠር መሰረት አመቱ አልቆ አዲሱ የሚጀምርበት ወር ሙሐረም ይባላል ። ይሁን እንጂ ይህን የዘመን መለወጫ ቀን  እንደ ባአል አያከብሩትም ።
    እንቁጣጣሽ የሚባለው ግን ከክርስትና እምነት ጋር የተገናኘ ባአል ነው ። ዘመኑንም ዘመነ ዮሐንስ,  ማቲዮሰ,  ሉቃስና ዻውሎስ ብለው ይሰይሙታል ።‼ ታዲያ ይህንን እንዴት ሙስሊሞች ያከብሩታል ? በጣም የሚገርመው የኢኽዋን መሪዎች አብሮነት በሚል ይህን ባአል የጋራ ለማድረግ ሲታትሩ መታየቱ ነው ። አልፎም በዚህና በጥምቀት ባአል ላይ በክብር እንግድነት ሲሳተፉና መግለጫ ሲሰጡም ሊታይ ይችላል ። ይህ የዲናቸውን ክብር ማስነካትና ራሳቸውንም ከማዋረድ ውጪ ጥቅም የለውም ።
   የሀገረችን ሙስሊም በሱፍይ መሪዎች አማካይነት ታቦት ሲሸኝና ጥምቀት አብሮ እየጨፈረ ሲያከብር ይኖር ነበር ። ተራው የኢኽዋን ሆነና በተራቸው ጭራሽ እየሱስ ፍቅር ያስተማረ ጌታ ነው ‼ ብለው አረፉት ። ይህም ለሙስሊሙ ወላእና በራእ የሚለው የዐቂዳ ውድቀት ሰበብ ሆነ ። የአላህ መልእክተኛ ለኡመቴ የምፈራው አጥማሚ መሪዎችን ነው ያሉት ይህ ነው ።
       ወደ ርእሴ ስመለስ እንቁ – ጣጣሽ እውነትም ብዙ ነው ጣጣሽ እላለሁ ። በመርህ ላይ ያልተመሰረተ ዐቂዳ ሁሌም ኮተት አያጣውም ። ዘመን መለወጫ ሲመጣ ሰዎች ካለፈው አመት ድክመታቸውና ስህተታቸው ታርመው የበለጠ ለመስራት ከመዘጋጀት ይልቅ የህይወታቸውን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ መተትና ኮተት ያማትራሉ ። በመሆኑም ከምን ጊዜውም በላይ በዚህ የእንቁ–ጣጣሽ ባአል ላይ መተትና ድግምት ይሰራል ጠንቋዮች በጣም ቢዚ ይሆናሉ ። ይህ መተትና ድግምት የእነርሱ ህይወት ሊለውጥ የሌላው ህይወት ማጥፋት አለበት ብለው ነው የሚያስቡት ። በመሆኑም በአብዛኛው የሚሰሩ ድግምትና መተቶች በሰዎች ላይ ይሆናል ።
   አላህ ከፈቀደው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ። መጠንቀቁና ሰበብ ማስገኘቱ መልካም ነው ። በዘመን መለወጫው ማለዳ ( ጠዋት)  ላይ የተለያዩ ዶሮዎች በተለያየ መንገድ ተገለው በሰዎች መውጫና መግቢያ ላይ ወይም መንገድ ላይ ሊጣሉ ይችላሉ ። በሌላ መልኩ መሬት ተቆፍሮ ሊቀበሩም ይችላሉ  ። ሙስሊሞች በተለይ በዚህ ቀን ጠዋትም ሆነ ቀኑ ላይ ከቤታቸው ሲወጡ " ቢስሚላህ ተወከልቱ ዓለላሂ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ብለው መውጣት ይኖርባቸዋል ። ለልጆቻቸው ይህን ዚክር ማስተማርና መንገድ ላይ የሚያገኙትን ነገር እንዳይረግጡ ፣ እንዳያነሱና እንዳይጫወቱበት መንገር ይኖርባቸዋል ።
ይህን ዚክር አድርገው ሰበብ ካስገኙ በአላህ ይጠበቃሉ ። በእንቁጣጣሽ ጣጣ እንዳይገቡ ይረዳቸዋል ።
    በመጨረሻም ይህን ኮተት ተሸክሞ የሚመጣውን ዘመን መለወጫ የሁሉም ነው ከማለት መቆጠብና ይዞት ከሚመጣው ጣጣና ኮተት በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል ።
አላህ ሙስሊሞችን ከሸረኛች ተንኮል ይጠብቅልን ።

https://t.me/bahruteka


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
https://t.me/sead429


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
☝️ከታቢዒዮች ሁሉ በላጭ የሆነው የኡወይስ ኢብኑ ዓሚር ቂሶህ

✍️https://t.me/sead429


አንተ በዝንጋቴ ላይ ሁነህ 👇
                           አሏህ እንዳይዝህ ተጠንቀቅ❗️

ያ መዕሸረል-አሂበህ መድሃኒት የሌለውን ሞት የሚባለውን ማስታወስ አለብን መልካም ስራን እንድንሰራ ከመጥፎ ስራ እንድንርቅ
يقول النبي صلى الله عليه وسلم" كُنْ فِي الدُّنْيَا كَأَنَّكَ غَرِيبٌ أَوْ عَابِرُ سَبِيلٍ ".
በዱንያ ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገደኛ ሁነህ ኑር!

👌ዛሬ ልሞት እችላለሁ አሁን ልሞት እችላለሁ በል! እንጂ ገና ነኝ ገና ልጅ ነኝ ገና ወጣት ነኝ ስንት life ይጠብቀኛል አትበል።

ስንቱ ህጻን እና ስንቱ ወጣት ተጉዟል።

👇يقول ابو اسحاق الإلبيري في تائيته

ولا تقل الصبا فيه امتهال........وفكر كم صغير قد دفنتا

ህጻንነት ልጅነት በሱ ውስጥ መዘግየት አለ(ፊት ለፊቴ እድል አለኝ ብዙ ዘመን አለኝ ) አትበል!.....እስኪ ስንት ህጻንን እንደቀበርክ አስተንትን!

👉ስንቱን ሰው ቀበርነው! ስንቱን ሰው አፈር ደፋንበት! መመከራችን ግን አነሰ!

ويقول ايضا👇

وتشهد كل يوم دفن خل..... كأنك لا تراد لما شهدتا
ሁሌ የወዳጅን ቀብር ትጣዳለህ(ትገኛለህ)....ግን አንተ ለተገኘህበት ለሁነው(ለሞት ለቀብር) ሁኔታህ የማትፈለግ ትመስላለህ(እነሱ የሚሞቱ አንተ የማትሞት መሰለህ)


ግን ይሄ ምክር መጀመሪያ ለራሴ ነው የሚሆን ነፍሴን አላጸዳም።

ለማንኛውም ሞትን በማስታወስ ላይ ሁላችንን አሏህ ይገዘን🤲

✍️https://t.me/sead429
share share! بارك الله فيكم


ከትክክለኛ ዑለሞች እንማር❗️

https://t.me/sead429






[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
የባጢል ሰዎች ንግግራቸው ስላማረ አንደበታቸው ስለጣፈጠ እውነተኛ ሊሆኑ አይችሉም!!
—————
አንዳንድ ሰዎች ንግግራቸውንና አንደበታቸውን በማሰማመርና በማጋጌጥ ይዘውት የተነሱትን ባጢል እውነት ለማስመሰል ይሞክራሉ። ልክ እንደዚያው ንግግሩ አላማረለትም ብለው የሚያስቡት ሀቅ ተናጋሪ ውሸታም ሊሆን አይችልም!!

የሀቅ ሰዎች ዘንድ ደግሞ አልፎ አልፎም ቢሆን የሚናገሯቸው ጠንከር ያሉ ቃላቶች ካሉ እነሱን ለቅመው አውጥተው በማራገብ የሚናገሩትን ሁሉ እውነታ ለማበላሸት "ይሀው ተሳዳቢ ናቸው፣ ተራጋሚ ናቸው…" እያሉ ይዳክራሉ። ዳሩ ግን ሀቅ ሀቅ ናት! የገላጯ አንደበት አማረም አላማረም፣ ተጋጌጠም አልተጋጌጠም ሀቋን በማስረጃ ፈትሾ መቀበል ነው። ሀቅ የሚመዘነው በማስረጃና እውነትን በመከተል ብቻ ነው።

የሀቅ ሰዎች አንደበታቸው ባይጣፍጥም፣ ንግግራቸው ባይጋጌጥም የሚናገሩት ሀቅ እስከሆነ ድረስ ሀቅ ፈላጊ በሆነ ሰው ላይ የመቀበል ግዴታ አለበት!!

ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) የሚባሉ ታላቅ ሊቅ 157ኛ ዓ.ሂ ላይ ነው ወደ አኼራ የሄዱት፣ ከአትባዑ ታቢዒን ናቸው፣ እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ:-
“ሰዎች ቢጋጩህ አለያም ቢርቁህ እንኳ የደጋግ ቀደምቶችን ትውፊት በመከተል ላይ አደራ! (ንቃት ይኑርህ!)። ወዮልህ የሰዎችን (የተዛባ) አስተሳሰብ ተጠንቀቅ! በንግግር ቢያጋጌጡልህ እንኳን።” [ጃሚዕ በያኑል ዒልሚ ወፈድሊሂ 2/114]

ሸይኽ ሷሊህ አሉ ሸይኽ (ሀፊዘሁላህ) ይህን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ:- “አስተሳሰባቸውን ቢያጋጌጡልህም፣ አንደበታቸውን ቢያሳምሩም ወዮለት ወዮልህ ንግግራቸውን ስላሳመሩና ቃላቶችን ስላሳመሯቸው ከሱንና ዘወር አትበል። ሱንናን እና የሱና ባለቤቶችን አንደበታቸውና የሚጠቀሟቸው ቃላቶች ባያምሩ እንኳን አጥብቀህ ያዝ!። ምክንያቱም ሚዛኑ ሱናን በመከተል ላይ ነው፣ ሱናን የተከተለ ድኗል፣ አዲስ ነገር የፈጠረ እርሱ ጠፊ ነው፣ አላህ ከጥፋት ይጠብቀን!።” አሉ

ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) ይህን የኢማሙል አውዛዒን ንግግር ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል:-
“ደጋግ ቀደምቶችን በመከተልህ ሰዎች ቢጋጩህም፣ ደረቅ ነህ ቢሉህም ወደነሱ ዘወር አትበል። ለሚያወግዙህ ነገር ቦታ አትስጠው ምክንያቱም አንተ ሀቅ ላይ ነህ፣ ሀቅ ላይ እስከሆንክ ደግሞ ፅና!። አንተ የሰዎችን ውዴታና ሙገሳ አይደለም የምትፈልገው፣ የምትፈልገው አላህን ማስወደድ እና ሀቅን ነው፣ ሀቅ ደግሞ ጥርጥር የለውም የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተል ላይ ነው። በግብዝነት፣ በተቃርኖ ሀሳብ አራማጅነትና መሰል ቃላት የሚገልፅህም ስታገኝ በጭራሽ ወደሱ ዘወር አትበል!። ምክንያቱም አንተ ሀቅ ላይ ነህ እነሱ ግን ባጢል ላይ ናቸው!!።” አላህ ሀቁን አውቀን በመከተል ላይ የምንፀና ያድርገን!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
✍️ሶሀቦች እና የነሱን ፈለግ እስከቂያማ መቆም መቃረብ ድረስ ያሉት ናቸው ትክክለኛ የነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወዳጆች።

ሶሀቦች ባመኑበት ሁኔታ ማመን እንዳለብን አሏህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ሲያሳስብ እንዲህ ይላል👇

(فَإِنۡ ءَامَنُوا۟ بِمِثۡلِ مَاۤ ءَامَنتُم بِهِۦ فَقَدِ ٱهۡتَدَوا۟ۖ وَّإِن تَوَلَّوۡا۟ فَإِنَّمَا هُمۡ فِی شِقَاقࣲۖ فَسَیَكۡفِیكَهُمُ ٱللَّهُۚ وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡعَلِیمُ)
[Surah Al-Baqarah 137]

በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡

👌የዚህ ዲን መሰረቱ መከተል እንጂ መፍጠር አይደለም።

لو كان حبك صادقا لأطعته إن المحب لمن يحب مطيع
ውዴታህ ትክክል ቢሆን ኖሮ በታዘዝከው ነበር
ወዳጅ ለሚወደው አካል ታዛዥ ነውና።


اتبع ولا تبتدع❗️


✍️https://t.me/sead429


የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
🔹እውቀት ማለት አሏህን መፍራት ነው

የመጽሐፍ ብዛት ፣ የእውቀት ብዛት ፣ ለሚፈለገው የሸሪዓ እውቀት መለኪያ ሊሆን አይችልም።
እውቀት ማለት ራስን ጠቅሞ ሌላውን የጠቀመ ነው -  እውቀቱ አነስተኛ ፣ መጽሐፉ አነስተኛ ቢሆንም።
እውቀት ብሎ ማለት በአቂዳም ፣ በመንሐጅም ፣ በእርሱ የተጠቀመበትና የፈየደው ነው።

አላህ የሚከተለውን ተናግሯል :-

"አላህን  ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ፣ አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው።" (ፋጢር : 28)

ሰለፎች  "እውቀት ማለት አላህን መፍራት ነው" ይላሉ።
አላህን ሳይፈራ ፣ ብዙ እውቀት ካየህበት ይህ ሰው ትክክለኛ አሊም አለመሆኑን እወቅ። እንዲህ አይነቱ ሰው ለእውቀቱ ግምት አይሰጠውም - እውቀቱ በእርሱ ላይ ጥፋት ይሆንበታልና።

ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ረሱል - ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል :-

"ቁርአን ለአንተ ማስረጃ ይሆናል ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ይሆንብሀል።"

ቁርአን  ፣ ሱና ፣ ሸሪዓዊ እውቀት በእርሱ ላይ ማስረጃ የሆነበት ሰው ምን አስከፊ አደረገው!

እንዲህ አይነቱ ሰው መጽሐፎቹ ቢበዙ  ፣ እርሱ ግን ጠማማ ነው። በቋንቋ ፣ በተፍሲር ፣ በሐዲስ ብዙ እውቀት ቢኖረውም  ፣ እርሱ ግን ጠማማ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ብዙ ይናገራሉ ፣ ነገር ግን ከእነርሱ ዘንድ ተግባር የለም።
ትክክለኛ ሙስሊም  እርሱ ተግብሮ ሰዎችን ወደ ተግባር የሚቀሰቅስ ነው።  ሱናን አጥብቆ ይዞ ሰዎችን ወደ ሱና የሚጠራ፣ ቢድዓን የሚዋጋ  ነው። "ጠቃሚ እውቀት" ማለት ይህ ነው።

አላህ የሚከተለውን ተናግሯል:-

"እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን?"
(በቀራ :44)

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?"
(ሶፍ :5)


https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መውሊድን ማን ጀመረው❓☝️☝️

ኡስታዝ ባህሩ ተካ

✍️https://t.me/sead429






አጠር መጠን ያለች መልስ👇

አሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረህመቱሏሂ ዐለይሂ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ➠ሰለፍዮች ብዙ ጊዜ ስለጋብቻ የሚያወሱት እና የሚወዱት ለምንድንነው❓

🤌ምክንያቱም እነሱ ዝሙት የማይሰሩ ህዝቦች ስለሆኑ


✍️https://t.me/sead429




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የቢድዐ ባለቤት ሁሉ የተረገመ ነው።

የቢድዐ ክብደት እና ቅለት ቢኖረውም ቆንጆ ግን የለውም።

በዚህ ቡድን መልስ እሰጣለሁ በዚህኘው አልሰጥም የሚባል ነገር የለም በሁሉም ቡድን እንደየቦታው እና ሁኔታው መልስ ስጥ❗️

የዝንጀሮ ቆንጆ የለውም❗️

اللهم اجعلنا من أهل السنة وأمتنا على السنة!


✍️https://t.me/sead429


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
https://t.me/sead429


የእስልምና ሀይማኖት ሙሉ ነው።ከማንኛውም አቅጣጫዎች ወይም ቡድኖች አስተያየቶች እና አስተሳሰቦች አያስፈልገንም

አል-መጅሙዕ(ጥ1 ገጽ497)

☝️አል-ዐላመቱ ረቢዕ ኢብኑ ሃ'ዲ አል-መድኸሊዩ አሏህህ ይጠብቃቸው!

ቆይ ግን የቢድዐ ባለቤቶች እና የመውሊድ ባለቤቶች በዲን ውስጥ ያለውን ትዕዛዝ ሰርተው ጨርሰውት ነው መጨመር ያስፈለጋቸው ❓


https://t.me/sead429

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.