Taha Ahmed


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው።
(ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው።) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እረሶም በዚህ ሰዎችን ወደ ኸይር በማመላከት እና ለሌሎች በማስተላለፍ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል።
(إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


*_ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ_*
*የመጨረሻው ክፍል*

√ *_ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ ተምኖ መክፈል_*

ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ መክፈል አይፈቀድም። ምክንያቱም በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ሲገልፁ ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለታቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡
አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዲህ ብለዋል:-
“የአላህ መልዕክተኛ በነበሩበት ዘመን ዘካተል ፊጥር የምናወጣው ከምግብ አንድ ሷዕ ነበር” ብለዋል።
ዘካተል ፊጥርን ከተገደበለት ጊዜ ማስቀደም ወይም ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ የአወጣጡን አይነትም መቀየር አይቻልም። ዒባዳ ሁልጊዜ በአላህ የሚደነገግ እንጂ በአስተያየት ምንፈፅመው አይደለም። ማንኛዉም ሙስሊም ዒባዳው እንዳይበላሽበት ሊጠነቀቅ ይገባዋል። በገንዘብ መተመን በቀደምት ሰለፎች አልተፈፀመም። ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃዉንት በገንዘብ ማዉጣትን ይቃወማሉ። አል-ኢማም ማሊክ፣ አል-ኢማም አሻፊዒይ እና አል-ኢማም አህመድ ይህ መዝሀባቸው ነው። ስለዚህም በተባለው መልኩ በእህል ያወጣ ሰው በሁሉም ስምምነት ትክክለኛ ዒባዳ ፈፅሟል

√ *_ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ መላክ_*

በመሰረቱ እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ዘካተል ፊጥርን ማዉጣቱ ቢሆን
ም የሚገባው ነገር ግን ምግብ የሚቀበል ሚስኪን ሰው የሌለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቤተሰቦቻቸዉ ወይም ጓደኞቻቸው አማካኝነት ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይችላሉ።
በጥቅሉ ማንኛዉም ሰው ዒባዳውን በዒልም ላይ የተመሰረተ በማድረግ ኢስላምን በሚገባ ለመተግበር መሞከር ይገባዋል።

*ተፈፀመ*

**تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال**
✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ *
ክፍል 3

√ *_ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶች_*
ዘካተል ፊጥር ሙስሊሞች ከሚመገቡዋቸው እንደ እሩዝ፤ በቆሎ፤ ጤፍ…. ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው። መልእተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲስ የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች (እንደ ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) የመሳሰሉት ሲሆኑ፤ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የሻፊዒያ እና የማሊኪያ መዝሀብ ዑለማዎች ሲስማሙበት ሸይኹል ኢስላምም የመረጡት አቋም ነው፡፡
የአላህ መልአክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› እንዲወጣ ማዘዛቸውን በተመለከተም እነዚህ ዑለማዎች የሚሰጡት ምላሽ ‹‹መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) እነዚህን የምግብ አይነቶች የጠቀሱት የመዲና ሰዎች በምግብነት ይጠቀሟቸው የነበሩ ከመሆናቸው አንፃር ነው፡፡ ስለሆነም የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) አነሱ የሚያገኙትንና የሚመገቡትን የምግብ አይነት ነው እንዲያወጡ ያዘዟቸው›› የሚል ነው፡፡
በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን መልዕክተኛው ሲጠቀሙበት በነበረው መስፈርያ መጠን ማውጣት ይችላል፡፡

√ *_ዘካተል ፊጥር መሰጠት የሚገባው ለማን ነው? *
በዚህ ጉዳይ ላይ ዑለማዎች ሁለት አይነት አመለካከት ያለቸው ሲሆን ሚዛን የሚደፋው ሀሳብ ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ከመግለፃቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል…

✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!


t.me/tahaahmed9


*ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ*
*ክፍል 2*

√ *_የዘካተል ፊጥር መጠን_*
ኢብኑ ዑመር ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል መልዕክት ተላልፎል:- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡››(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በድሮ ጊዜ የነበረ የእህል መስፈሪያ ነው። በዘመናዊ መለኪያ አንድ ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ 1ሷዕ = 4 የሁለት ዕጅ እፍኞች ነው።

√ *_ዘካተል ፊጥር በማን ላይ ግዴታ ይሆናል?_*
ዘካተል ፊጥር ግዴታ የሚሆነው ሁለት መስፈርቶችን ባሟላ ሰው ላይ ብቻ ነው። እነርሱም:- 1ኛ\ ሙስሊም በሆነ 2ኛ\ ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ በሚሆንበት ቀን እና ሌሊት፤ ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ የሚበቃ መብል ኖሮት የተረፈው እና ተጨማሪ ነገር ያለው ነው፡፡

√ *_ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው መቼ ነው?_*
ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ሲሆን፤ ማውጣቱ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት የሚጀምረው ከረመዳን የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ ነው፡፡ ነገር ግን ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች ያደርጉት እንነበረው ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ይፈቅዳል፡፡

ክፍል 3 ይቀጥላል…
✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ*

ዘካተል ፊጥር ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ግዴታ የሚሆን የዘካ አይነት ነው፡፡ ዘካተል ፊጥርን መስጠት እያንዳንዱ ሙስሊም ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ሲሆን፤ እያንዳንዱም አባወራ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር ስላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ኢብኑል ሙንዚር ‘አል-ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው ዑለማዎች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን ተስማምተውበታል›› በማለት የጉዳዩን ግዴታነት ከሚያመለክቱት ነብያዊ ሀዲሶች በተጨማሪም የኡለማዎችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

√ *_የተደነገገበት ጥበብ_*

ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው፡፡
ይህን አስመልክቶ ዐብደላህ ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ:- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ ለ ‘ለግዉ’ (ጥቅም ለሌላቸው ውድቅ የቀልድ ንግግሮችና ተግባሮች) እና ለ ‘ረፈስ’ (ፆታዊ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮች) ማፅጃ፤ ለምስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል፡፡ ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከኢድ ሰላት በኋላ ዘካውን የሰጠ ከሌላ ግዴታ ያልሆነ ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል፡፡›› (አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል) ""
ክፍል 2 ይቀጥላል…
✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*አላህ ዘንድ ከሰዎች ተወዳጁ ማነው? ከስራዎችስ ይበልጥ ተወዳጁ የትኛው ነው?*

ዓብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት አንድ ግለሰብ ወደ መልእክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጣና አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ ዘንድ ተወዳጁ ሰው ማነው? ከስራዎችስ የበለጠ ተወዳጁ የትኛው ነው? አላቸው:: እሳቸውም:- “አላህ ዘንድ ተወዳጁ ሰው ለሰዎች የተሻለ ጥቅም የሚሰጥ ሰው ነው:: አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሆነው ስራ ደግሞ ሙስሊምን ማስደሰት ወይም ጭንቀቱን ማስወገድ አልያም እዳውን መክፈል ወይም ከሱ ላይ ረሀብን ማባረር ነው:: ” አሉ:: በማስከተልም “በዚህ መስጂድ ውስጥ ( መስጂድ-አነበዊ ለማለት ነው) አንድ ወር በኢዕቲካፍ ከማሳልፍ የወንድሜን አንዳች ጉዳይ ለማስፈፀም መንቀሳቀሴን እመርጣለሁ:: ቁጣውን የተቆጣጠረ አላህ ገመናውን (ዓውረቱን) ይደብቅለታል:: ቁጭቱን መወጣት እየቻለ ከመወጣት የተቆጠበ አላህ የቂያማ እለት ልቡን በተስፋ ይሞላለታል:: የወንድሙ ጉዳይ እስኪመቻችለት (እስኪፈፀም) ከወንድሙ ጋር የተንቀሳቀሰ እግሮች በሲራጥ ላይ በሚንሸራተቱበት (የቂያማ እለት) አላህ እግሮቹን እንዲፀኑ ያደርግለታል:: ኮምጣጤ ማርን እንደሚያበላሸው ሁሉ መጥፎ ስነ-ምግባርም ስራን ያበላሻል::” አሉ:: ጠበራኒ ዘግበውታል:: አልባኒ ሲልሲለቱ አል-አሀዲስ አሰሂሃ ላይ ሰሂህ ብለውታል::
✍ ጣሀ አህመድ - ረመዳን 1441

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*ደካማ ሰው ዱዓእ ከማድረግ የደከመ ነው!*

አቡ ሁረይራ - ረዲየ አላሁ ዓንሁ- :- “ ደካማ ሰው ዱዓእ ከማድረግ የደከመ ነው:: ስስታም ሰው ደግሞ ከሰላምታ የሚሰስት ነው::” ብለዋል:: (አቡ ያዕላ እና ኢብኑ ሂባን ዘግበውታል) አልባኒ ሲልሲለቱ አል-አሀዲስ አሰሂሃ ላይ ሀዲሱ ሰሂህ ነው ብለዋል::
✍ጣሀ አህመድ - ረመዳን 1441

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*_ባሪያው ወደ እሱ እጆቹን አንስቶ ባዶ አድርጎ ሊመልስበት ያፍራል_*

ሰልማን አል-ፋሪሲይ -ረዲየ አላሁ ዓንሁ- እንዳስተላለፉት:- ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ የተባረከው እና የላቀው ጌታችሁ እጅግ የሚያፍር እና ቸር ነው:: ባሪያው ወደ እሱ እጆቹን አንስቶ ባዶ አድርጎ ሊመልስበት ያፍራል::” (አቡ ዳውድ፣ኢብኑ ማጃህ እና ኢብኑ ሂባን ዘግበውታል) አልባኒ ሰሂሁ አቡ ዳውድ ላይ ሀዲሱ ሰሂህ ነው ብለዋል::
✍ጣሀ አህመድ - ረመዳን 1441

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


*_ አላህ ዘንድ እጅግ የተከበረ አምልኮ የትኛው ነው? _*

አቡ ሁረይራ - ረዲየ አላሁ ዓንሁ- እንዳስተላለፉት:- ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ እንደ ዱዓእ (ከአምልኮ) አላህ ዘንድ የተከበረ የለም::” (ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ እና ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል) አልባኒ ሰሂሁ አቲርሚዚይ ላይ ሀዲሱ ሀሰን ነው ብለዋል::
✍ ጣሀ አህመድ ረመዳን 1441

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!

t.me/tahaahmed9


የትኛው ዒባዳ ነው በላጭ?
ከዓብዱላህ ኢብኑ ዓባስ - ረዲየ አላሁ ዓንሁ - እንደተላለፈው:- “ በላጭ የሆነው ዒባዳ ዱዓእ ነው ” ብለዋል:: (አል-ሃኪም ዘግበውታል) ሰሂሁል አል-ጃሚዕ ላይ አልባኒ ሀዲሱ ሰሂህ ነው ብለዋል::
✍ ጣሀ አህመድ ረመዳን 1441

👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!


t.me/tahaahmed9


*ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ?*

እናታችን ዓኢሻ -ረዲየ አላሁ ዓንሀ- እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት ለይለተል-ቀድር መሆኖን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም:- " አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ" ( አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) በይ አሉኝ:: (ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል::) አልባኒም ሀዲሱን ሰሂህ ከማለታቸውም ባሻገር በአንዳንድ የቲርሚዚይ ኪታብ ህትመቶች ላይ የሚታየው *ከሪሙን* ስለሚለው ጭማሪ ከአንዳንድ ፀሀፊዎች ወይም አታሚዎች ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል:: (ሲልሲለቱ አል-አሀዲስ አሰሂሃ)

✍ ጣሀ አህመድ ረመዳን 1441

👇የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!


t.me/tahaahmed9

10 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

331

obunachilar
Kanal statistikasi