የአነስ ኢብኑ ማሊክ እንባ
=======================
አለቀሰ ያውም ስቅስቅ ብሎ የእንባ ዘለላዎች በጉንጮቹ ላይ እየፈሰሱ ለረዥም ሰዓት ቆየ። አነስ ቢን ማሊክ ነው። ሙስሊሞች ቱስቱር ከተማን ድል አድርገው የከፈቱበት ዘመቻ በተወሳ ቁጥር አንገቱን ሰበር አድርጎ ያነባል። ስለቱስቱር ምን አሳወቃችሁ እሷ የፋርስ ከተማ አልነበረችምን? ሙስሊሞች ለአንድ ዓመት ሙሉ የከበቧት። ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከተማይቱ በሙስሊሞች እጅ ወደቀች። ግልፅ የሆነ ድልን ተጎናፅፈው ከፈቷት። ታዲያ አነስ ቢን ማሊክ የቱስቱርን ዘመቻ ሲያስታውስ ለምን ያለቅሳል?! ገና ጎህ ሳይቀድ ነበር የኢስላም ሠራዊት ወደ ቱስቱር ምሽግ የዘለቀው። ሰላሳ ሺህ ሙጃሂዶች ከአንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የመስቀል ሠራዊቶች ጋር ገጠሙ። መራር ውጊያ ተካሄደ። ከባድ ጦርነት ተከናወነ። ሙስሊሞች ደማቸውን እያንጠባጠቡ ሰውነታቸውን በጨርቅ እያሰሩ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አደረጉ። እጅግ በጣም አስቸጋሪ እጅግ ከበዛ እልቂት በኋላ ለአላህ ምስጋና ይግባውና ሙስሊሞች ድል ተጎናፅፈው በጠላታቸው ላይ ድልን ተቀዳጁ ይህ ድል ፀሓይ ከወጣች ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነበር። ሙጃሂዶቹ በእጃቸው የያዙትን ሠይፍ ወደሰገባው ሲመልሱ የሱብሒ ሰላት እንዳመለጣቸው አወቁ። ጎህ ከመቅደዱ በፊት ሰዓቱን ጠብቀው የሱብሒን ሰላት መስገድ አልተቻላቸውም ነበር። እጅግ አዘኑ ምክንያታዊ ሆነው ዑዝር ኖሯቸው እንኳ አቅልለው አላለፉትም። አነስ ቢን ማሊክ በሕይወቱ አንድ ጊዜ የሱብሒን ሰላት ባለመስገዱ ተንሰቅስቆ አነባ። አቀርቅሮ አለቀሰ። የሙስሊሙ ጦር በእስልምና ሻኛ በአላህ መንገድ በጂሃድ ተጠምዶ አላህ ዑዝር ሰጥቷቸው እነሱ ግን አነቡ። አነስ እንዲህ ይላል፡- “ቱስቱር ምንድነው?! የሱብሂ ሰላት አምልጣኛለች ዓለም ሁሉ በዚህ ሰላት ልዋጭ ትሁንህ ብባል እንኳ አልቀበልም”
አሁንስ ለምን አላህ ድልን እንደተጎናፀፋቸው ገባህ? እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸውን ሙሉ ለአላህ ሰዉ። እኛስ ስለኢማናችን እንቅልፋችንን መስዋዕት ማድረግ ችለናልን? ካልቻልን...የምን ድል የምን ከፍታን እንመኛለን? በልባችንና በሕይወታችን ውስጥ የሰላት ዋጋ ተገፎ ኃያልነታችንንና ክብራችንን አጥተናል። ዱንያ ጠባ አጣብቃናለች። ጠላቶቻችን ወረው ከዚህም ከዚያም ይቦጫጭቁናል። የእውነት ኢስላምን እንኑር “ምእመናን እንደሆናችሁ የበላይ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ” ተብሎ በአላህ ቃል ተገብቶልን ሳለ ለምን የበታች የሆንን ይመስላችኋል ራሳችሁ መልሱት ጣትህን ወደሌላው ከመቀሰርህ በፊት ወደራስህ አቅጣጫት!!
https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk