ሙመይዓዎችን ተጠንቀቋቸው!!
——————
ውድ የሆነች ገሳጭ ምክር!!
、、、、、、
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሓዲ ዑመይር አል-መድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“በሸይኽ አልባኒና በሌሎችም የሱንና ሊቃውንቶች መካከል አለመግባባቶች ይከሰቱ ነበር ብለን በተደጋጋሚ ከአንድ ጊዜ በላይ ነግረናችኋል፣ ነገር ግን ወላሂ በጠቅላላ በዓለም ደረጃ የሰለፊዮች ሶፍ (አንድነት) ላይ አንድም ተፅእኖ አልፈጠረም ነበር!!። አሁን ግን የፊትና ባለ ቤት የሆኑ ገና ትናንሽ ተማሪዎች ሆነው ፊትናን በመፍጠር በሱኒዮች መካከል ተፅእኖ ለማሳደር የሚፈልጉ በቀን እና ሌሌት ኢማም ሆነው ያነጋሉ (ብቅ) ይላሉ። ሁለት ቀን ለማቅራት ቁጭ ይልና በቃ እርሱ ኡስታዝ ነው፣ ለእርሱ የሚወግኑ ማንም የእርሱን ስህተት ሊያርም የሚነሳን አካል የትኛውንም እርምት የማይቀበሉ ቡድኖች ሆነው ብቅ ይላሉ። የሚታረምበት መንገድ ምንም ያህል ግልፅ በሆነ ማስረጃ የተሞላ ቢሆን (አይቀበሉም)። በቃ ልክ ዱኒያ ቁጭ ብድግ የምትል እስከሚመስል ይደርሳሉ፣ ምክንያቱም እነዚያ ለእርሱ ወግነው ቡድንተኛ ሆነዋል። ይህ ኡስታዝ ምናልባትም ገና ምስኪን የዲን ተማሪ ይሆናል፣ ምናልባትም ጥሩ ነገር ሊኖረው ይችላል፣ ነገር ግን ወገንተኝነቱ ምንድነው?!።
የሂዝቢዮች (ቡድንተኞች) ባህሪ (ስነ-ምግባር) ወደ ከፊል ሰለፊዮች ገብቷል። ወላሂ ይህቺ ስነ-ምግባር በመካከላችን አልነበረችም!፣ ወላሂ ፊት ለፊታችን ሸይኽ ኢብኑ ባዝና ሸይኽ አልባኒ ሌሎችም በጃሚዐተል ኢስላሚያ ተከራክረዋል፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ወላሂ ሰለፊዮች ላይ አንዳች ተፅእኖ አላሳደረም ነበር። ሸይኽ አልባኒ ኪታቦችን ፅፈዋል፣ ከፃፏቸው ኪታቦች ውስጥም ከሩኩዕ በኋላ እጆችን ደረት ላይ ማስቀመጥ ቢድዐ ነው ብሏል፣ ከመሆኑም ጋር ግን ወላሂ በሰለፊዮች አንድነት ለይ አንደም የፈጠረው ተፅእኖ አልነበረም። ሱፊዮችና ኩራፊዮች ወጣቱን አንዱን በአንዱ የሸይኽ ኢብኑ ባዝንና የሸይኽ አልባኒ የመስአላ ልዩነት ተጠቅመው ሊመቱት ፈለጉ ወላሂ ምንም መንገድ አላገኙም!።
ወንድሞቼ በእነዚህ ነገሮች ላይ ነቃ ልትሉ ይገባል!፣ ለአገሌና ለአገሌ ብላችሁ መወገንን ተውት!፣ ለአንድም ሰው አትወግኑ የሰለፊያን ደዕዋ ትለያያላችሁ፣ ይህን ተግባር በጭራሽ አንወድላችሁም!። አንዳችሁ በሌላው ላይ ይታገስ፣ ከፊላችሁ ሌላውን በጥበብ ይምከር፣ ለአገሌና ለአገሌ መወገን ቡድንተኛ መሆን ውስጥ አትግቡ!፣ በዚህ አካሄድ ሰለፊያ ተበጣጥሳለች፣ ይህቺ ቡድንተኞች (ሂዝቢዮች) ወደ እናንተ (ወደ ሰለፊዮች) ያስገቧት ተግባር ናት። እንዲህ ላሉ ነገሮችም ከእናንተ ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋልና ተውዋት ባረከላሁ ፊኩም!። ደጋግ ቀደምቶቻችሁ ወደነበሩበት ተደጋጋሚ የሆነ በጥበብና ገሳጭ በሆነ መልኩ የመመካከርና የላቀች በሆነችዋ ባህሪ የማጌጥ ታሪክ ተመለሱ!።
እንዲሁም ወደ ጀርህና ተዕዲል ኪታቦች ስትመጣ በግለሰቦች ጉዳይ ላይ አለመግባባቶችን ታገኛለህ፣ አንደኛው (በደረሰው ልክ) ትክክል ነው ይለዋል፣ ሌላኛው ደግሞ ተሳስቷል ብሎ ጀርህ ያደርገዋል፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ግን የሀዲስና የሱና ባለቤት በሆኑት ሰለፊዮች መካካል ክርክሮችንና ቡድንተኝነትን አታገኝም። ምክንያቱም እነሱ ነገሮችን ገርና ቀላል በሆነ መንገድ መረዳት ይችሉ ነበር፣ ባልተግባቡባቸው ነገሮችም እንዲህ አይነት ጥሩ ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው መመዘኛዎችና መርሆች አሉዋቸው፣ ከዚህ ውስጥም ጀርህ አል-ሙፈሰር አለ።
ከመሆኑም ጋር ከነርሱ ውስጥ "እርሱ ጀርህ ያደረገው ለእኔ አጥጋቢ አይደለም፣ አለያም ማድረጉን ወድጄ መቀበል እኔን አይዘኝም (አይመለከተኝም)።" የሚል አይገኝም ነበር፣ ሌሎችንም መሰል በመክሯሯትና በትቢት (በአፈንጋጭነት) ሀቅን የማይቀበሉባቸውን መንገዶችን አይጠቀሙም ነበር። በመካከላቸው በቢድዐ ባለቤቶች ጉዳይ ላይ አለመግባባቶች አይገኙም ነበር። የእውቀት ባለቤት የሆነ አካል አንድን የቢድዐ ሰው "ሙብተዲዕ ነው" ብሎ ብይን ከሰጠበት በኋላ ልዩነት አይኖራቸውም ነበር። ምንም ያህል ያ ሙብተዲዕ በውሸትና በማምታታት ጥግ ቢደርስ ሙብተዲዕ ለተባለው አካል የሚከላከል ሌላ ግንባር አይፈጠርም ነበር። ልክ በዚህ ጊዜ ሰለፊዮች ላይ እየተከሰተ እንዳለው ፊትና አይከሰትም ነበር። አህሉሱናዎች ከእንዲህ ያለው ፊትና እና ከባለቤቶቹም ጤነኞች (ሰላም) ነበሩ!። ምክንያቱ ደግሞ ሚዛናዊና ሀቅን ወዳድ መሆናቸውና (በዲናቸው ጉዳይ) ከዱኒያ ጥቅማጥቅምና ገንዘብ የራቁ በመሆናቸው ነው። የቅርብ ሰው በሆነውም በሩቁም፣ በወዳጅም በጠላትም ሀቁን ይናገራሉ፣ በሀቅ ላይ ፍትሃዊ ሆነው ያስተካክላሉ።
ለዚህም ነው ታሪካቸውን በተደጋጋሚ ስንቃኝ በሀቅ እርስ በርሳቸው በአንድነት የተጣበቁ (የተሳሰሩ) ሆነው በቢድዐና በጥመት ባለቤቶች ላይ አሸናፊና የባለይ ሆነው እንጂ አናገኛቸውም። አህሉሱናዎች በዚህ እርስበርሳቸው በመጣበቃቸውና በመተሳሰራቸው በተደጋጋሚ ታሪካቸው ሲቃኝ በቢድዐና በጥመት ባለቤቶች የበላይ ሆነው ነበር።
አሁን ላይ ግን የቢድዐ ሰዎች የበላይ ሆነውባቸዋል፣ ወንድሞቼ አሁን ላይ የቢድዐ ሰዎች የበላይ ሆነውባቸዋል፣ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ሰለፊያ የሚጠጉ ሰዎች በሚኖሩት የተበላሸ አኗኗር ነው!!። አላህ ለመልካም ነገር ይግጠማችሁ!!፣ ጉዟችሁንም በሀቅ ላይ ያፅናው!!።” [አዝ-ዘሪዓህ ኢላ በያኒ መቃሲዲ ኪታብ አሽ-ሸሪዓህ 2/589-590]
ትርጉም:- ✍🏻ኢብን ሽፋ: ሸዕባን 21/1442 ዓ.ሂ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa