Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
አስተማሪው የሚቀበለውን (ስጦታ) በተመለከተ እነዚህን ቢድዐዎች፣ እነዚህን ነገሮች ስለሚያስፈፅም ከሆነ የሚሰጠው የሚቀበለው ነገር አስቀያሚ መሆኑ አይሰወርም። እነዚህን ነገሮች ምንም ሳይፈፅም እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚሰጠው ከሆነ ኢብኑ ሐቢብ ‘ለአስተማሪ በሙስሊሞች ዒድ ምንም አይወሰንለትም - ይህን መስራቱ የሚወደድ ቢሆን እንኳን’ ብለዋል። … ኢብኑ ሐቢብ ሸሪዐዊ በሆኑ በዓላት ላይ እንዲህ ካሉ ሸሪዐዊ ባልሆኑት ላይ እንዴት ሊሆን ነው?!” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዒ ወተሶውፍ፡ 128-129]
5. አልኢማም አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢ (790 ሂ.)፡-
መውሊድን ከተቃወሙ የስምንተኛው ክ/ዘመን ዑለማኦች ውስጥ አንዱ ሻጢቢ ናቸው። ሻጢቢ በቢድዐ ላይ የተሰላ ሰይፍ ነበሩ። “አልኢዕቲሷም” የተሰኘው ዳጎስ ያለ ስራቸው ቢድዐን እርቃኑን ያስቀረና ዛሬም ድረስ የቢድዐ አጋፊሪዎችን ምቾት እንደነሳ ነው። መውሊድን በተመለከተ ኢማሙ ሻጢቢ እውነትን ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ መልእክት ያዘለ ቅልብጭ ያለ ፈትዋ ሰጥተዋል። ይሄውና፡- “ሰዎች ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚከበረው መውሊድ መጤ የሆነ ቢድዐ መሆኑ የታወቀ ነው። ቢድዐ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። ስለሆነም ቢድዐን ለመፈፀም ገንዘብን መለገስ አይፈቀድም። በዚህ ላይ ኑዛዜ ከተላለፈም ተፈፃሚ አይደለም። እንዲያውም ቃዲው ሊያፈርሰው ይገባል።…” [ፈታዋ ሻጢቢ፡ 203-204]
በተጨማሪም ስለቢድዐ ምንነት ካብራሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አሁንም ከነሱ (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሚካተተው (በዒባዳ ውስጥ) ተለይተው የተወሰኑ አፈፃፀሞችንና ሁኔታዎችን በቋሚነት መያዝ ነው። ለምሳሌ በአንድ ድምፅ በመሰባሰብ የሚደረግ ዚክር፣ የነብዩን - ﷺ - ልደት ቀን በዓል አድርጎ መያዝና እነዚህን የመሳሰሉትን ያካትታል።” [አልኢዕቲሷም፡ 1/53]
6. አልኢማም ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.)፡-
ሸሪዐው ዒድ ተደርጎ እንዲያዝ ያዘዘበትን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ዒድ ሊይዙ አይፈቀድላቸውም። እነሱም (የታዘዙትም) ዒደል ፊጥር፣ ዒደል አድሓና የተሽሪቅ (ከዒደል አድሓ ቀጥሎ ያሉት ሶስቱ) ቀናት ናቸው። እነዚህ አመታዊ በዓላት ናቸው። የጁሙዐ ቀን ደግሞ ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለን በዓልና ዐውደ- አመት አድርጎ መያዝ በሸሪዐችን መሰረት የሌለው ቢድዐ ነው።‛ [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 118]
7. አቡ ዐብዲላህ አልሐፋር አልገርናጢ (811 ሂ.)፡-
“የመውሊድ ሌሊት መልካም ቀደምቶች ማለትም የአላህ መልእክተኛ- ﷺ - ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት አልነበሩም። ከአመቱ ሌሊቶች ተጨማሪ ስራም አይሰሩባትም ነበር። ምክንያቱም ነብዩ- ﷺ - እንዲከበሩ በተደነገገው መልኩ እንጂ አይከበሩምና። እሳቸውን ማላቅ ከትልልቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎች ነው። ነገር ግን ልቅናው ከፍ ወዳለው አላህ እሱ በደነገገው መልኩ እንጂ (በሌላ) መቃረብ አይፈቀድም። ሰለፎች ከሌሎች ሌሊቶች በተለየ ምንም የሚጨምሩ እንዳልነበሩ መረጃው በሷ (በተወለዱበት ቀን) ላይ መወዛገባቸው ነው። ለምሳሌ እሳቸው - ﷺ - የተወለዱት በረመዳን ነው ተብሏል፣ በረቢዕ ነውም ተብሏል። በዚህም ላይ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ አራት የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላጭ የሆኑት በመወለዳቸው ሳቢያ በማለዳዋ የተወለዱባት ሌሊት ዒባዳ የሚጠነሰስባት ብትሆን ኖሮ ውዝግብ ሳይከሰትባት በሰፊው በታወቀች ነበር። ነገር ግን ጭማሬ የሆነ ማላቅ አልተደነገገባትም።
የጁሙዐ ቀን ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጭ ቀን እንደሆነችና በበላጭ ቀን የሚፈፀመው በላጩ ነገር ፆም እንደሆነ አታውቅምን? ሆኖም ግን ነብዩ - ﷺ - ከትልቅ ልቅናው ጋር ከጁሙዐ ቀን ፆም ከልክለዋል። ይህም በየትኛውም ጊዜ ይሁን በየትኛውም ቦታ ካልተደነገገ በስተቀር አምልኮት መፍጠር እንደማይቻል ያመለክታል። ካልተደነገገ አይፈፀምም። ምክንያቱም የዚች ህዝብ ኋለኛው ክፍል ከቀዳሚው የተሻለ የተቀና ነገር አያመጣምና። ይሄ በር ቢከፈትማ የሆኑ ሰዎች መጥተው ወደ መዲና የተሰደዱበትም ቀን ‘አላህ በሱ ኢስላምን ያላቀበት ቀን ነው’ በማለት ሊሰባሰቡበትና ሊያመልኩበት ነው። ሌሎች ደግሞ ተነስተው ኢስራእ ያደረጉባት ሌሊት ‘ልኬታው የማይገመት የሆነ ልቅና የተጎናፀፉባት ሌሊት ነች’ በማለት አምልኮት ሊፈጠር ነው። እናም (እንዲህ ከተከፈተ) የሆነ ወሰን ላይ ሊቆም አይቻልም። መልካም ሁሉ ያለው አላህ ለሳቸው የመረጣቸውን መልካም ቀደምቶች በመከተል ነው። የሰሩትን እንሰራለን። የተውትን እንተዋለን። ይሄ ከተረጋገጠ በዚች ሌሊት ላይ መሰባሰቡ በሸሪዐው ተፈላጊ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል። እንዲያውም ይተው ዘንድ መታዘዝ አለበት። …
ይህቺ ሌሊት ደግሞ በሱፍዮች መንገድ ነው የምትዘጋጀው። በዚህ ዘመን የሱፍዮች መንገድ በዲን ውስጥ ከተፈጠሩ አስቀያሚ ነገሮች ውስጥ ነው። ምክንያቱም የጉባዔ ስርአታቸው ዘፈንና እንቶ ፈንቶ ነውና። ይሄ ነገር በነዚህ ጊዜያት ከሚፈፀሙ የላቁ መቃረቢያዎች እንደሆነና ይህ የወልዮች መንገድ እንደሆነ ለአላዋቂ ሙስሊሞች ያስተምራሉ። በሌሊትና በቀን ውስጥ ግዴታ የሆኑባቸውን ህግጋት በቅጡ የማያውቁ መሃይማን ሰዎች ናቸው። ይልቁንም አላዋቂ ሙስሊሞችን ለማጥመም ሸይጧን ምትኮች ካደረጋቸው ውስጥ ናቸው። ለሰዎች ከንቱ ነገሮችን ይሸላልማሉ። ወደ አላህ ዲንም ከሱ ያልሆነን ነገር ያስጠጋሉ። ምክንያቱም ዘፈንና እንቶ ፈንቶዎች ከዛዛታና ከጨዋታ ውስጥ ናቸውና። እነሱ ግን ወደ አላህ ወሊዮች ያስጠጉታል። እነሱም በዚህ ላይ ገንዘብን ያለ አግባብ ለመብላት ይዳረሱ ዘንድ እየዋሹባቸው ነው።…” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዕ ወተሶውፍ፡ 128]
8. ኢብኑ ነሐስ (814 ሂ.)፡-
“አውደ-አመታትና በዓላት ውስጥ ከተፈጠሩት ውስጥ በከፊል ማውሳት” በሚል ንኡስ ርእስ ስር “ከነዚህ ውስጥ በወርሃ ረቢዐል አወል ሰዎች የፈጠሩት የመውሊድ ተግባር ነው” ይላሉ። በውስጡ ካሉ ቢድዐዎችና ጥፋቶች እንኳን ቢፀዳ ከቢድዐነት እንደማያልፍ ካጣቀሱ በኋላ ሰዎች መውሊድን ለማዘጋጀት የሚያነሳሷቸው ምክንያቶች ብለው የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል። ከነዚህም ውስጥ፡-
- ከሚጠሯቸው ቃዲዎች፣ መሪዎች፣ መሻይኾችና ከመሳሰሉት ጋር ለመተዋወቅ በማለም የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንድ መሻይኾች ደግሞ ሰዎች በመውሊድ ምክንያት በእርዳታ መልክ ወይም በስጦታ መልክ ወይም ሃፍረት ይዞት ወይም ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር ለመፎካከር ሲል ከሚያመጡት ነገር የሚተርፈውን ለራሳቸው ለመጠቀም በማለም መውሊድን የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንዱ ክፉ ምላስ ያለውና ቁጡ ይሆንና ደካሞችን በመጥለፍና ምላሱንና ምግባሩን የሚፈሩ ሰዎችን በማጥመድ አላማውን የሚያሳካ አለ። … [ተንቢሁል ጋፊሊን ዐኒል አዕማሊል ጃሂሊን፡ 499]
9. ቃዱ ሺሃቡዲን ደውለት አባዲ አልሐነፊ (894 ሂ.)፡-
“በያመቱ መጀመሪያና በረቢዐል አወል ወር መሃይማን የሚሰሩት ተግባር ከምንም የሚቆጠር ነገር አይደለም። የሳቸው ﷺ ልደት ሲወሳ ይቆማሉ። ሩሐቸው ትመጣና ትካፈላለች ይላሉ። ይሄ ሙግታቸው ውድቅ ነው። ይሄ እምነት ሺርክ ነው።” [ፈታዋ ሸይኽ ሸምሲል ሐቅ አዚምአባዲ፡ 166]
እንግዲህ ተመልከቱ። እነዚህ በሙሉ በ1206 ሂ. ከሞቱት ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ - ረሒመሁላህ - ዘመን ቀድሞ መውሊድን ያወገዙ ዑለማዎች ናቸው። መሃይማን ሱፍዮች ግን መውሊድን የሚቃወሙት ከ200 አመት ወዲህ የመጡ “ወሃቢዮች” ናቸው ሲሉ የራሳቸውን ድንቁርና በራሳቸው አንደበትና ብእር እያጋለጡ ነው።