ዜና: #በጁባላንድ አስተዳደር የጸጥታ አካላት እና #በሶማሊያ መንግስት ወታደሮች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ
በኬንያ አቅራቢያ በምትገኘው የሶማሊያ ጁባላንት ከተማ በመሆነችው ራስካምቦኒ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በግዛቷ አስተዳደር የጸጥታ ሀይሎች እና በአከባቢው በሰፈሩ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮች መካከል ውጊያ መካሄዱ ተገለጸ።
የሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ “ዛሬ ጠዋት በጁባላንድ የጸጥታ ሀይሎች የተሰነዘረብንን ጥቃት በሚገባ መክተናል” ሲል ገልጿል፤ ጥቃቱን የፈጸመው የጁባላንድ የጸጥታ ሀይል ነው ሲል መኮነኑን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል።
የአሜሪካ መንግስት ዛሬ ነሃሴ 2 ቀን በጁባላንድ ያለው ውጥረት አስጊ ነው የሚል ማስጠንቀቂያ ያወጣ ሲሆን ማስጠንቀቂያው ከወጣ ከሰዓታት በኋላ ከባድ ግጭቶች መከሰቱ ተጠቁሟል።
ሁኔታው ከቅርብ አመታት ወዲህ ግንኙነታቸው በእጅጉ እያሽቆለቆለ የመጣውን በሞቃዲሾ እና ኪስማዮ መካከል ሊኖር የሚችለውን የሰላም ድርድር የበለጠ ሊያደናቅፈው ይችላል ተብሏል።
የጁባላንድ የጸጥታ ባለስልጣናት በደርዘን የሚቆጠሩ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮች እጃቸውን እንደሰጡ እየገለጹ ቢገኝም የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት ሁኔታውን በገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አለመቻላቸውን ጠቁመዋል።
በጁባላንድ የተፈጠረው ውጥረት ወደ ለየለት ግጭት እየተቀየረ ባለበት ሁኔታ የሀገሪቱ የፌደራል መንግስት የግዛቷ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤን ከአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ሲል ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0333kL33LLySZBhQhZ5KA95MWjJ1KuRV2kfkSCu6CP5rCnKjpPB5xBqhzVGmFv3qv9l