ዜና፡ በ #አማራ ክልል "በ #ፋኖ ታጣቂዎች" ተጣለ በተባለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋረጠ
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በሚገኙ አንዳንድ አከባቢዎች የ"ፋኖ ታጣቂዎች" በጣሉት ገደብ ምክንያት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከሁለት ቀናት በላይ መቋረጡን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
የትራንስፖርት እንቅስቃሴው የተቋረጠው "የመንግሥት የጸጥታ አካላት ላይ ተጽዕኖ እናደርጋለን በሚል ከፋኖ ታጣቂዎች በተላለፈ መመሪያ” መሆኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በደብረ ማርቆስ ነዋሪ ተናግረዋል።
“በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፤ በጽኑ የታመሙ ሰዎች ሪፈር ታዞላቸው መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት የሰዎች ህይወት የሚያልፍበት ሁኔታዎች አሉ። መንገድ ጀምረህም ከሆነ ያሰብክበት መድረስ ሳትችል እዛው ልትቀር ትችላለህ።” በማለት አገዳው እያስከተለ ያለው ተጽዕኖ አስረድተዋል።
ተጨማሪ ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6172