ዜና፡ #ሶማሊያ የ #ኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ፈጸመዋል ስትል ባቀረበችው ክስ ኢትዮጵያ ማዘኗንና "ሀሰት" መሆኑን ገለጸች
ሶማሊያ በዶሎው የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ባቀረበችው ክስ ኢትዮጵያ ማዘኗን በመግለጽ ክሱን "ሀሰተኛ" ስትል ጠራች። ኢትዮጵያ ክሱ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ግንኙነትን ለማደስ የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታሰበ ነው ብላለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱ "የአፍሪካን ቀንድ ለማተራመስ የሚሹ" እና "በቀጠናው ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ" አካላት ተግባር መሆኑን ገልጿል።
ኢትዮጵያ ይህን ምላሽ የሰጠችው ሶማሊያ ዶሎው በተባለው የድንበር ከተማ በኢትዮጵያ ኃይሎች "በግልጽ ጸብ አጫሪነት ድርጊት" ፈጸመዋል ስትል መክሰሷን ተከትሎ ነው። ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር፣ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ እና በሶማሊያ የፖሊስ ኃይል ቤዝ ላይ "ያልተጠበቀ ጥቃት" መፈጸማቸውን በመግለጽ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ተናግራለች።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6262