🔖 አንድ ጥያቄና አስር መልሶቹ ይድረስ ለአብዱ'ላሂ አል-ሀረሪ ተማሪዎች እና ተከታዮች፤ የመጀመሪያ ክፍል፧
🗞 በመጀመሪያ ስለ ትምህርቱ አንዳንድ ነገር ላሳዉቃችሁ። ይህንን ፅሁፍ ያገኘሁት ከነሲሃ ቲቪ ድረገፅ ሲሆን በሸኽ ኢልያስ አህመድ የተፃፈ ፅሁፍ ነዉ። እናም እኔ ከፅሁፉ ላይ ምንም ነገር ሳልጨምር ሳልቀንስ ወደናንተ አደርሳለሁ፤ በአላህ ፍቃድ ይህን ትምህርት እንዲትከታተሉ እጋብዛችኋለሁ። ሼር አድርጉት።
#⃣ «በቁርኣን ውስጥ አላህ ከፍጥረታቱ በላይ እንዳለ
የሚያመለክቱ አንድ ሺህ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ
መረጃዎች አሉ! »
📚 ከአንጋፋዎቹ የሻፊዒያህ መዝሀብ ሊቃውንት የአንዱ
ንግግር ነው።[1]
[1] “መጅሙዑ’ል-ፈታዋ” ጥራዝ 5 ገፅ 121
ይመልከቱ
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ፦
#⃣ የዚህ ፅሑፍ አላማ የአላህን የበላይነት የሚያረጋግጡ መረጃዎችን መዘርዘር አይደለም።
ነገር ግን ይህንን እውነታ የማይቀበሉ ወገኖች የሚያነሱትን አንድ “ዝነኛ” ብዥታ ጠራርገው የሚያፀዱ"ሸሪዓዊና አእምሯዊ ምላሾችን መጠቆም ነው። እንዲያውም የጥያቄያቸው ትክክለኛ ምላሽ የበላይነቱን የሚያፀና መሆኑን በስተመጨረሻ እናያለን! በትዕግስት ያንብቡት!
#ጥያቄ
« “አላህ በዐርሹ ላይ ነው!” ካላችሁ ዐርሽን ከመፍጠሩ
በፊት የት ነበር?!»
በርግጥ አላህ ከዐርሽ በላይ የመሆኑን ብሩህ እውነታ
በእንዲህ ያለ ጥያቄ መጋፈጥ እንደሚቻል የሚገምቱ
ወገኖች ይህንን ጥያቄ የሚቀምሩት እንደሚከተለው
ነው፦
«አላህ ዐርሽም ሆነ ሌላ ቦታ ሳይፈጠር የነበረ ጌታ
ነው፤ እርሱ የማይቀያየር ጌታ በመሆኑ ዛሬም እንደያኔው
ያለ ቦታ ነው ያለው! » ይላሉ።
[ይህ በተለያየ አገላለፅ የሚደጋግሙት ሀተታ “ዋነኛ
መጋፈጫቸው” ነው፤ እንደ ምሳሌ፦ “አሽ-ሸርሑ’ል-
ቀዊም” የተሰኘውን የዐብዱ’ላሂ አል-ሀረሪ መፅሐፍ ገፅ
212 (በአምስተኛው እትም መሰረት) መጥቀስ
ይቻላል።]
#መልስ
ይህን ድፍን ሙግት ከነመንደርደሪያው አንኮታኩተው
የሚጥሉ ምላሾችን በሁለት መንገዶች ማቅረብ
ይቻላል።
የመጀመሪያው መንገድ የጥያቄውን ስልት በጥቅሉ
የተመለከቱ መሰረታዊ ምላሾችን ያካተተ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሙግቱ አሰካክ ላይ የሚያነጣጥሩ ዝርዝር ምላሾችን ያቀፈ ነው።
አንደኛው መንገድ ስልቱን የተመለከቱ አምስት ጥቅል ምላሾችን ይዟል፤ እነሆ!
1.1 እውነታ በውዥንብር አይረታ!
የአላህ ከበላይ መሆን በሸሪዓዊና አእምሯዊ አስረጆች
የተረጋገጠ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪ በሰዎች ተፈጥሯዊ
ዝንባሌ ውስጥ ያሰረፀው አማራጭ የለሽ እምነት
በመሆኑ ምንም አይነት ጥያቄን የሚያስተናግድ አይደለም! ልብ ይበሉ! በፅኑ መረጃዎች የፀደቀ እምነትን በማጠራጠሪያ መጠይቆች መጋፈጥ አይቻልም! ሙግት ደግሞ ማስረጃ አይሆንም! ማስረጃም በመላምት አይፈርስም! እውነታም በውዥንብር አይረታም።
ይህ ሙግት አል-ኢማም አዝ-ዘሀቢይ እና ሌሎች በትክክለኛ ሰነድ የዘገቡትን አንድ ተያያዥ ክስተት ያስታውሰናል፦
🌟 ﻗﺎﻝ ﺃَﺑُﻮ ﺟَﻌْﻔَﺮ ﺑﻦ ﺃﺑﻲ ﻋَﻠﻲّ ﺍﻟْﺤَﺎﻓِﻆ: ﺳَﻤِﻌﺖ ﺃَﺑَﺎ ﺍﻟْﻤَﻌَﺎﻟِﻲ
ﺍﻟْﺠُﻮَﻳْﻨِﻲّ ﻭَﻗﺪ ﺳُﺌِﻞَ ﻋَﻦ ﻗَﻮْﻟﻪ }ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦ ﻋﻠﻰ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵ
ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ { ﻓَﻘَﺎﻝَ : ﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﻠﻪ ﻭَﻟَﺎ ﻋﺮﺵ ﻭَﺟﻌﻞ ﻳﺘﺨﺒﻂ ﻓِﻲ
ﺍﻟْﻜَﻠَﺎﻡ ﻓَﻘﻠﺖ ﻗﺪ ﻋﻠﻤﻨَﺎ ﻣَﺎ ﺃَﺷﺮﺕ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﻓَﻬَﻞ ﻋﻨْﺪﻙ ﻟﻠﻀﺮﻭﺭﺍﺕ
ﻣﻦ ﺣِﻴﻠَﺔ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻣَﺎ ﺗُﺮِﻳﺪُ ﺑِﻬَﺬَﺍ ﺍﻟﻘَﻮْﻝ ﻭَﻣَﺎ ﺗَﻌْﻨِﻲ ﺑِﻬَﺬِﻩِ ﺍﻟْﺈِﺷَﺎﺭَﺓ
ﻓَﻘﻠﺖ ﻣَﺎ ﻗَﺎﻝَ ﻋَﺎﺭِﻑ ﻗﻂّ ﻳَﺎ ﺭﺑﺎﻩ ﺇِﻟَّﺎ ﻗﺒﻞ ﺃَﻥ ﻳَﺘَﺤَﺮَّﻙ ﻟِﺴَﺎﻧﻪ
ﻗَﺎﻡَ ﻣﻦ ﺑَﺎﻃِﻨﻪ ﻗﺼﺪ ﻟَﺎ ﻳﻠْﺘَﻔﺖ ﻳﻤﻨﺔ ﻭَﻟَﺎ ﻳﺴﺮﺓ ﻳﻘْﺼﺪ ﺍﻟﻔﻮﻕ
ﻓَﻬَﻞ ﻟﻬَﺬَﺍ ﺍﻟْﻘَﺼْﺪ ﺍﻟﻀَّﺮُﻭﺭِﻱّ ﻋﻨْﺪﻙ ﻣﻦ ﺣِﻴﻠَﺔ ﻓﻨﺒﺌﻨﺎ ﻧﺘﺨﻠﺺ
ﻣﻦ ﺍﻟﻔﻮﻕ ﻭﺍﻟﺘﺤﺖ ﻭﺑﻜﻴﺖ ﻭَﺑﻜﻰ ﺍﻟْﺨﻠﻖ ﻓَﻀﺮﺏ ﺍﻟْﺄُﺳْﺘَﺎﺫ
ﺑﻜﻤﻪ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺴﺮﻳﺮ ﻭَﺻَﺎﺡ ﻳﺎﻟﻠﺤﻴﺮﺓ ﻭﺧﺮﻕ ﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻋَﻠَﻴْﻪِ
ﻭﺍﻧﺨﻠﻊ ﻭَﺻَﺎﺭَﺕ ﻗِﻴَﺎﻣَﺔ ﻓِﻲ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪ ﻭَﻧﺰﻝ ﻭَﻟﻢ ﻳﺠﺒﻨﻲ ﺇِﻟَّﺎ
ﻳَﺎ ﺣَﺒِﻴﺒِﻲ ﺍﻟْﺤﻴﺮَﺓ ﺍﻟْﺤﻴﺮَﺓ ﻭﺍﻟﺪﻫﺸﺔ ﺍﻟﺪﻫﺸﺔ ﻓَﺴﻤِﻌﺖ ﺑﻌﺪ
ﺫَﻟِﻚ ﺃَﺻْﺤَﺎﺑﻪ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺳﻤﻌﻨﺎﻩ ﻳَﻘُﻮﻝ ﺣﻴﺮﻧﻲ ﺍﻟْﻬَﻤﺪَﺍﻧِﻲ
አል-ሓፊዝ አቡ ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ዐሊይ አል-ሀመዛኒ
(በ531 ዓመተ-ሂጅራ ያረፉ) እንዲህ ይላሉ፦ «አቡ’ል-
መዓሊ አል-ጁወይኒ (478 ዓ.ሂ) “አር-ረሕማን ከዐርሹ
በላይ ከፍ አለ” ስለሚለው የአላህ ንግግር ተጠይቆ
“አላህ ዐርሽ ሳይኖር የነበረ ነው…” እያለ በንግግሩ
ሲዘላብድ ሰማሁት! ከዚያም “ያመላከትከውን ነገር
አውቀናል፤ ታዲያ ስለ “ዶሩሪያት” (እንድናረጋግጠው
የግድ ስለሚለን ፅኑ እውነታ) መላ ቢጤ አለህን?”
አልኩት። “በዚህ ንግግርህ ምን ፈልገህ ነው? በዚህ
ጥቆማህስ ምን ወጥነህ ነው?” አለኝ። እኔም፦
“ማንኛውም አዋቂ ‘ጌታዬ ሆይ…!’ ካለ ገና ምላሱ
ከመንቀሳቀሱ በፊት በውስጡ ፅኑ ስሜት ማደሩ አይቀሬ
ነው፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ሳይዞር እላይን ያስባል!
ለዚህ ፅኑ እውነታ መላ አለህን? አሳውቀንና ከ ‘ላይ’
እና ከ ‘ታች’ እንገላገል!” አልኩትና አለቀስኩ! ሁሉም
አለቀሱ! መምህሩም (አል-ጁወይኒ) በእጅጌው
አግዳሚ ቆጡን መታና “ወይ ግራ መጋባት!” ሲል ጮኸ! ልብሱንም ቀዶ ጣለ! በመስጂዱም ቂያማ ቆመ (ተረበሸ)! ከዚያም ወርዶ “ወዳጄ ሆይ! ኧረ ግራ መጋባት…! ኧረ መርበትበት…!” ከማለት ሌላ መልስ አልሰጠኝም። ከዚያም በኋላ ተማሪዎቹ “‘አል-ሀመዛኒ ግራ አጋባኝ!’ ብሎ ሲናገር ሰማነው!” ሲሉ ሰማኋቸው።» [2]
በጥቅሉ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ማስረጃዎች የፀደቀውን የአላህ የበላይነት በመሰል ፀጉር ስንጠቃ
መጋፋት ለአላህና ለመልዕክተኛው ንግግር ተገቢውን ቦታ ከመስጠት ጋር የሚጣረስ ነው!
1.2 ልዩነቱ ብርቱ!
ሌሎች ሙስሊሞች የአላህን የበላይነት ሲያፀድቁ እጅግ
ብዙ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ቁርኣናዊና ነብያዊ አስተምህሮቶችን እያጣቀሱ ነው! እነዚያ ሙግተኞች ግን “አላህ ቦታ ሳይፈጠር የነበረ ነው፤ ዛሬም ያለ ቦታ ነው ያለው…» የሚለውን የዘወትር መፈክር የሚያትቱት
በየትኛውም የቁርኣን ወይም የሐዲሥ መረጃ ወይም
የሰሓቦች ንግግር ላይ አግኝተውት አይደለም! ይህን ማወቅ ብቻ ሙግታቸው ውድቅ መሆኑን ያረጋግጣል። በርግጥ ይህንን ሙግት እንዲጠግን የተቀጠፈ መሰረተ ቢስ “ዘገባ” አይጠፋም!
ለምሳሌ፦ ታዋቂው የሐዲሥ ጠቢብ አል-ሓፊዝ ኢብኑ
ሐጀር (852 ዓ.ሂ) «አላህ – ከርሱ ውጭ ምንም ነገር ሳይኖር ነበረ…» የሚለውን አል-ቡኻሪይ ዘንድ በቁጥር 3191 ላይ የሚገኘውን ሐዲሥ ባብራሩበት አጋጣሚ እንዲህ ብለዋል፦
⏩ ክፍል 2 ይቀጥላል፤ ቻናሉን ሼር ማድረግ አትርሱ፤ በቴሌግራም ይቀላቀሉን፡
✅