ሂጃብ(መሸፈን)ለመደንገጉ የወረዱ የቁርአን አንቀፆች ስንመለከት ይበልጥ ግልፅ ይሆናልና አንመልከታቸው። በቁርአን
ከመጡ አንቀፆቹ መካከል:
① የመጀመሪያው ማስረጃ
ﻗﻮﻟﻪ -ﺗﺒﺎﺭﻙ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ : ﴿ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞْ ﻟِﺄَﺯْﻭَﺍﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ
ﻭَﻧِﺴَﺎﺀِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦْ ﺟَﻼﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ﺫَﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰ ﺃَﻥْ
ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًﺍ ﺭَﺣِﻴﻤًﺎ﴾ [ ﺍﻷﺣﺰﺍﺏ 59: ]
ትርጉም:አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ፣ለሴት ልጆችህ፣ለምእመናን ሴቶችም ከላያቸው ላይ ጅልባባቸውን
(መከናነቢያቸውን) እንደለቁ ንገራቸው። ይህ እንዳይታወቁና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ በጣም የቀረበ ነውና፤ አላህም
መሃሪና አዛኝ ነው። (ቁርአን 33:59)
ኡሙ ሰለማህ
(የመልእክተኛውصلى الله عليه وسلم) ባልተቤት
አላህ ስራዋን ይውደድላትና
ይህንን አንቀፅ (ከላያቸው ላይ
መከናነቢያቸውን ይልቀቁ የሚለው) በወረደ ጊዜ የአንሷር ሴቶች ከላያቸው ቁራ ያረፈባቸው ይመስል ጥቁር በጥቁር
ለብሰው ወጡ። አቡ ዳውድ ዘግበውታል (ሶሂህ አቢ ዳውድ 4101)። ዑበይደተ ሰልማኒ እና ሌሎችም እንዲህ ሲሉ
ያወሳሉ:
አማኝ ሴቶች ከራሳቸው ላይ ጅልባባቸውን ይለቁ ነበር። መንገዱን ለማየት ሲባል አይናቸው ብቻ እስኪታይ
ይሸፈኑ ነበር።
"ጅልባብ" ኢብኑ መስዑድ እና ሌሎችም ኩታ ብለው የሚጠሩት፣ ተራው ማህበረሰብ ደግሞ ሽርጥ ብሎ የሚጠራው፤
ትልቅ የሆነ ሽርጥ ሲሆን እራሷንና ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ነው። አቡ ዑበይድ እና ሌሎች ደግሞ ከላይ ለቃው አንድ
አይኗ ሲቀር ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ልብስ ነው ብለዋል። (ኢብኑ ተይሚያ መጅሙዑል ፈታዋ 22/110–111)
② ሁለተኛው ማስረጃ
﴿ ﻭَﻗُﻞ ﻟِّﻠْﻤُﺆْﻣِﻨَﺎﺕِ ﻳَﻐْﻀُﻀْﻦَﻣِﻦْ ﺃَﺑْﺼَﺎﺭِﻫِﻦَّ
ﻭَﻳَﺤْﻔَﻈْﻦَ ﻓُﺮُﻭﺟَﻬُﻦَّﻭَﻟَﺎ ﻳُﺒْﺪِﻳﻦَﺯِﻳﻨَﺘَﻬُﻦَّ ﺇِﻟَّﺎﻣَﺎ
ﻇَﻬَﺮَ ﻣِﻨْﻬَﺎ ۖ ﻭَﻟْﻴَﻀْﺮِﺑْﻦَ ﺑِﺨُﻤُﺮِﻫِﻦَّ ﻋَﻠَﻰٰ
ﺟُﻴُﻮﺑِﻬِﻦَّ ۖ ﻭَﻟَﺎ ﻳُﺒْﺪِﻳﻦَ ﺯِﻳﻨَﺘَﻬُﻦَّ ﺇِﻟَّﺎ ﻟِﺒُﻌُﻮﻟَﺘِﻬِﻦَّ
ﺃَﻭْ ﺁﺑَﺎﺋِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْ ﺁﺑَﺎﺀِ ﺑُﻌُﻮﻟَﺘِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْ ﺃَﺑْﻨَﺎﺋِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْ
ﺃَﺑْﻨَﺎﺀِ ﺑُﻌُﻮﻟَﺘِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْﺇِﺧْﻮَﺍﻧِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْﺑَﻨِﻲﺇِﺧْﻮَﺍﻧِﻬِﻦَّ
ﺃَﻭْ ﺑَﻨِﻲ ﺃَﺧَﻮَﺍﺗِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْ ﻧِﺴَﺎﺋِﻬِﻦَّ ﺃَﻭْﻣَﺎ ﻣَﻠَﻜَﺖْ
ﺃَﻳْﻤَﺎﻧُﻬُﻦَّ ﺃَﻭِﺍﻟﺘَّﺎﺑِﻌِﻴﻦَ ﻏَﻴْﺮِ ﺃُﻭﻟِﻲ ﺍﻟْﺈِﺭْﺑَﺔِ ﻣِﻦَ
ﺍﻟﺮِّﺟَﺎﻝِ ﺃَﻭِ ﺍﻟﻄِّﻔْﻞِ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻟَﻢْ ﻳَﻈْﻬَﺮُﻭﺍﻋَﻠَﻰٰ
ﻋَﻮْﺭَﺍﺕِ ﺍﻟﻨِّﺴَﺎﺀِ ۖ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﻀْﺮِﺑْﻦَ ﺑِﺄَﺭْﺟُﻠِﻬِﻦَّ ﻟِﻴُﻌْﻠَﻢَ
ﻣَﺎ ﻳُﺨْﻔِﻴﻦَ ﻣِﻦ ﺯِﻳﻨَﺘِﻬِﻦَّ ۚ ﻭَﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺃَﻳُّﻪَ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ﴾
[ ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﻮﺭ31 : ]
ትርጉም፡"ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይስበሩ (ይከልክሉ) ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም
ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡የውስጥ ጌጣቸውንም
ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው
ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች
ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም
ለእነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ
ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ። በሱራ አል–
ኑር ምእራፍ 24፥አንቀፅ 31
ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፥ "ኒቃብ" ابَقِن ማለት "መሸፈኛ" ማለት ነው፦ ኢማም ቡኻርይ
መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759 ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንዳስተላለፈችው፦ "ዓኢሻህ"ዲአላሁ አንሀ." እንዲህ ትል ነበር፦
"ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች
በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"። (ሶሂህ ቡኻሪ
ገጽ፡4758)
"ጉፍታዎች" በሌላ አንቀጽ (ከላይ ባሳለፍነው አህዛብ 59) ላይ "መከናነቢያቸው" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል።
(ሪሳለቱ አ–ሂጃብ ኢብኑ ዑሰይሚን።)
🍇🍇🍇🍇🍇🌳🌳🌳🌳🌳
✍أم نياب
ሶሸል ሚዲያ ያገኛነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
👇👇👇👇👇
https://t.me/Aselefiyaa