የራሱን አላዋቂነት ማን ያውቃል?!
▪️"ከማንም በላይ እኔ አውቃለሁ" ከማለት የበለጠ አላዋቂነት የለም።
ዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ዘንግተህ የሰዎች ዓይን ውስጥ ያለን ስንጥር ከማየት የበለጠ እውርነትም የለም።
كَدَعواكِ كُلٌّ يَدَّعي صِحَّةَ العَقلِ-
وَمَن ذا الَّذي يَدري بِما فيهِ مِن جَهل.
"ልክ እንዳንቺ ሙጉት ሁሉም ሰው የዓቅሉንና የአስተሳሰቡን ትክክለኛነት ይሞግታል፣ እራሱ ዘንድ ያለን አላዋቂነትና ሞኝነት ማን ያውቃል?!"ላለውና በ354 ዓ.ሂ ለሞተው የገጣሚዎች አሚር "አል-ሙተነቢ-አላህ ይዘንለት- ልክ ብሏልና።
▪️እራሳችን ዘንድ ትልቅ ሰው፣ አላህ ዘንድ ግን ትንሽና ወራዳ ሰው ከመሆን አላህ እራሱ ይጠብቀን
።የግንባር ዓይን እንደሰጠን ሁሉ የልብም ዓይን ይስጠን።
▪️የሰው ልጅ ከቁርኣንና ሐዲሥ የተጨለፈ የእውቀቱ መጠን አናሳ በሆነና ዲንና ኢማኑ በሳሳ ቁጠር በሆነ ባልሆነው አፉን ይከፍታል፣ የመሰለውንና የመጣለትንም ሁሉ ያወራል።የምላስንና የንግግርን አደገኛነት ጠንቅቆ ያወቀ ሰው ግን አፉን ከመክፈቱና ምንም ነገር ከመናገሩ በፊት ልብና አዕምሮውን ተጠቅሞ በሚገባ ያስባል፣ ንግግሩ አላህን የሚያስደስት፣ ለሰው ልጆች የሚጠቅምና ፍትሃዊ ንግግር መሆኑን አረጋግጦ እንጂ አይናገርም።
🔅("በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካምን ይናገር፣ ካልሆነ ዝምምም ይበል") አርዓያችን ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ በሌላም ሐዲሣቸውም የሚከተለውን ብለዋል፣
(إِنَّ الْعَبْدَ لَيَتَكَلَّمُ بِالْكَلِمَةِ مَا يَتَبَيَّنُ فِيهَا يَنْزِلُ بِهَا فِي النَّارِ أَبْعَدَ مِمَّا بَيْنَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ")
"አንድ ሰው ያላረጋገጣትን/እርግጠኛ ያልሆነበትን አንዲትን (አላህን የምታስቆጣ) ቃል በመናገሩ ምክንያት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሚበልጥን ርቀት የጀሀነም እሳት ላይ ወደ ታች ይወርዳል/ይጣላል" ብለዋል።
📚ሐዲሡንም ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል።
▪️ሙስሊም ሆይ ኢማንህ እንዲስተካከል ከፈለግክ ቀድመህ ልብህን አስተካክል፣ አንድ ሰው ምላሱን እስካላስተካከለና እስካልተቆጣጠረ ድረስ ደግሞ መቼም ልቡ ሊስተካከል አይችልም።ልብ ሳይስተካከል ደግሞ መቼም ኢማን አይስተካከልም።
✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ
17/6/1442ዓ.ሂ
https://t.me/+xBNi3Or3YoI4N2Y0