የስብሃት ሰይጣን፣ የእኛ መነፅር?
የስብሃት ገብረ እግዚአብሔር ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ንባብ
*
መተዋወቂያ
***
በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ የራሳቸውን የተለየ አሻራ
አስቀምጠው ካለፉ ደራሲያን አንዱ የሆነውን የስብሃት ገብረ
እግዚአብሔርን ያህል ሲያወዛግበን የኖረ ደራሲ ያለን
አይመስለኝም፡፡ በተመሳሳይ ዘመን የተወገዘም የተመለከም
ደራሲ ነው፡፡ ይኽ ሁለት ጽንፍ የያዘ ልዩነት የመነጨው
ከሰውየው የድርሰት ብቃት አንጻር ሳይሆን ከሚነሳበት የሥነ-
ምግባር ጥያቄ አንጻር ነው፡፡ የአደራረስ ችሎታው ለጥያቄ
ሲቀርብም አይስተዋልም፡፡ የስብሃት ድርሰቶች አንባቢያቸውን
ከራሳቸው ጋር የሚያዛምዱባቸው ምትሃት አላቸው፡፡ “ሰባተኛው
መልአክ”ን ባነበብኩት ቁጥር የአየለን ፍርሃቶች፣ ሽንፈቱን
ለቀናት ከላዬ ላይ ማንሳት የሚያቅተኝ ስብሃት ስላዛመደኝ ነው፤
‹ሌቱም አይነጋልኝ›ን እያነበብኩ በዚያ ሁሉ የቡና ቤት ሁካታ፣
የወሲብ ጨዋታ መሃል የነማሚት ፍርሃት፣ የወጣቶቹ ተስፋ
መቁረጥ፣ ‹ከአድማስ ባሻገር› ላይ በዓሉ ጀምሮ የተወው የዚያ
ዘመን ወጣቶች የሰብዕና ሙጠት የሚጋባብኝ ከስብሃት ብዕር
የተነሳ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የአንባቢውን ስሜት ተቆጣጥረው
የመሰንበት ሥልጣን ያላቸው ደራሲዎቻችን፣ በጣት የሚቆጠሩ
ናቸው፡፡
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በ1992 ዓ.ም. ባሳተመው ‹ሰባተኛው
መልአክ› ውስጥ ሦስት የተለያዩ ታሪኮች ይገኛሉ፡፡
ከመጀመሪያውና ‹ሰባተኛው መልአክ› ከተባለው ተረክ ውጭ
ያሉት ሁለቱ አጫጭር ልቦለዶች፣ ‹አጋፋሪ እንደሻው› እና
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የፋንታሲ ልቦለድ ባሕርያት ያሏቸው
ድርሰቶች ናቸው፡፡ እንዲያውም ስብሃት የፋንታሲ ሥነ-ጽሑፍ
ለአማርኛ ስነጽሑፍ ያስተዋወቀባቸው ናቸው ለማለት
እደፍራለሁ፡፡ እነዚህ ድርሰቶች ወደ ተረትነት የሚያደሉ፣ ምናባዊ
ነጻነታቸው እና ጉዳዮቻቸው ደግሞ ከተረትም የረቀቁ የፋንታሲ
ድርሰቶች የሚያደርጓቸው ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልቡና፣ እምነቱ፣
ፖለቲካው፣ ባህሉ፤ ሥጋዊው እና መንፈሳዊው ዓለሙ ሁሉ
ይጠየቁባቸዋል፤ ይመዘኑባቸዋል፣ ይተቹባቸዋል፡፡
“አጋፋሪ እንደሻው” ሞትን የሚሸሹት አጋፋሪ እንደሻው የተባሉ
ሽማግሌ የሽሽት ተረክ ነው፤ ተረኩ ሕልማዊውን ከእውናዊው
ጋር ይቀላቅላል፤ በትንታ አማካይነት የሞትን እና የሕይወትን
ድንበር አፍርሶ አጋፋሪን መንፈሣዊ ዓለም ውስጥ ይተርካቸዋል፤
እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ይኽንን የእሳቸውን ገድል የሚተርከውን
ደራሲ ሳይቀር በዚያ መንፈሳዊ ዓለም ነዋሪ ያደርገዋል፡፡ አቡነ
ተክለ ሃይማኖትን እና ቆሪጥን በፍልሚያ መድረክ ያገናኛል፤
ሞትን ሥጋ አልብሶ ከአጋፋሪ ጋር ያፋልማል፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የአጋፋሪ እንደሻው ልጅ የሆኑትን የአቶ
አልአዛርን መዋዕለ ዕብደት የሚተርክ፣ አንባቢውን በ“ሕልም
ዓለም” እና በእውን ዓለም መሃል የሚያዋልል ተረት ነው፡፡ ይኼ
አጭር ድርሰት የስብሃትን የበቃ ተራችነት፣ ጨዋታ አዋቂነት፣
በፋንታሲያዊ ተረኮች መመሰጡንም ይመሰክራል፡፡ ስብሃት በዚህ
ድርሰት እንደነ ሩድያርድ ኪፕሊንግ (The Jungle Book) እና
ሎፍቲንግ (Doctor Dolittle) እንሰሳን ከሰዎች ጋር በቋንቋ
ማግባባትን፣ እንደነ ጎጎል (The Nose) እና ጊ ደ ሞፓሳ
(The Hand) አንድን አካል ባለሚና ባለድርጊት አድርጎ ልቦለድ
ድርሰት ውስጥ የማጫወትን ብልሃት፣ እንደነሉዊስ ካሮል
ገፀባሕርያቱን የምንኖርበት ዓለም የማይፈቅድላቸውን ውላጤ
(transformation) የ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ዓለም
በሚፈቅድላቸው መጠን እንዲያካሒዱ ሲፈቅድ እናያለን፡፡
ይኽን ድርሰት የፋንታሲ ድርሰት ነው ለማለት ያስደፈሩኝም
እነዚህ ስብሃት ወደ ኢትዮጵያ ጽሑፋዊ ሥነ-ጽሑፍ የጋበዛቸው
የተረኩ ባሕርያት ናቸው፤ እነኚህ በላይኛው አንቀጽ ያሰፈርኳቸው
የ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ገፅታዎች፣ የሥነ-ጽሑፍ ዘውግ
አጥኚዎች ለፋንታሲ ዘውግ በመለዮነት ከሚያስቀምጧቸው
ባህርያት ጋር ይሰምራሉ፡፡ የራሱ የፋንታሲ ልቦለድ ዋነኛ
መለዮዎች ከሚባሉት ባሕርያት አንዱ በድርሰቱ ውስጥ
የምንኖርበት ዓለም ውስጥ ሊኖሩ/ሊደረጉ የማይችሉ ፍጡራንን፣
አካባቢዎችን፣ ድርጊቶችን/ክስተቶችን ... እንደሚቻሉ አድርጎ
ማቅረብ ነው፤ ይኽ ደግሞ እንግዳ ፍጡራንን (ለምሳሌ ቀንድ
እና ጭራ ያላቸውን ሰዎች፣ በራሪ ፈረሶችን)፣ ወይም ለዚህ
ዓለም እንግዳ የሆኑ ክስተቶችን (ከእንቅልፍ ሲነቁ ራስን ወደ
ነፍሳትነት ተለውጦ እንደማግኘት ያለ) በታሪኩ ውስጥ አሳማኝ
አድርጎ በማቅረብ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ስብሃት በ“ስምንተኛው
ጋጋታ” ለዚህ ዓለም አይቻሌ የሚመስሉ ውሻን ከሰው ጋር
እንደማግባባት፣ በተደገመበት ዕፅ ምክንያት ከአንድ ሰብዕና ወደ
ሌላ ሰብዕና እንደመለወጥ፣ ምንነቱ በግልፅ ያልተነገረውን
(ነገር ግን በምርመራ የሚደረስበትን) “እንትን” የተባለን አካል
የሰው ባሕርያት እንደማላበስ ያሉ ለምንኖርበት ዓለም እንግዳነት
(strangeness) ያላቸውን ነገሮች ለድርሰቱ አውሏል፡፡ ድርሰቱ
ውስጥ የተተረኩት ክስተቶች እና የተፈጸሙት ድርጊቶች፣
በትውፊታዊው/ሃይማኖታዊው የስምንተኛው ሺሕ ዋዜማ እና
የዕለቱ ዕለት መሆኑ፣ እንደ ስምንት ኪሎ መግደላዊት ያሉ
ሥፍራዎቹም የድርሰቱን ፋንታሲያዊነት ያጠናክራሉ፡፡
በ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ውስጥ ስብሃት ትላልቅ ጥያቄዎችን
አንስቷል፣ ወይም ነባር እውነታችንን እና እምነታችንን
እንድንጠይቅ ገፋፍቶናል እላለሁ፡፡ ከመደበኛው ልቦለድ ይልቅ፣
ተረት መናገር የሚፈልጉትን ያላሉ በማስመሰል ተናግሮ ከጥያቄ
ለማምለጥ ይረዳል፤ ከተረት ተግባራት አንዱ እንዲያውም ይኼ
ለማምለጫነት ማገልገሉ ነው፡፡ ስብሃት ማምለጥ ይፈልግም
አይፈልግ በሌሎች ድርሰቶቹ ውስጥ በቀጥታ ያላስቀመጣቸውን
(አስቀምጧቸውም ከሆነ ጎልተው ያልተሰሙኝን) ሞጋች
ሐሳቦቹን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ባቀናበረው
በ‹ስምንተኛው ጋጋታ› በኩል አቀብሎናል፡-
ለምሳሌ ከታማኝ ዘብነቱ በቀር በአወንታ ስሙን
የማናዘወትርለትን ውሻን በሰው ላይ የምግባር ልዕልና አጎናፅፎ
ያመጣዋል፡፡ አቶ አልአዛር ኮምቡጠር የተባለ ውሻ አላቸው፤
በስምንተኛው ሺሕ ዋዜማ በቋንቋ ከባለቤቱ ጋር መግባባት
የሚጀምር ውሻ ነው፡፡ ይኽ ውሻ አድነን እንብላ የሚል ሐሳብ
ለጌታው ሲያቀርብ እሳቸው ግን “እንቀላውጥ” ይሉታል፡፡ ውሻን
በልክስክስነት የሚነቅፈው የሰው ልጅ ከውሻ በምግባር አንሶ
ቅልውጥን ለውሻ ሲያስተምር እናገኘዋለን፡፡ አቶ አልአዛር
ቅልውጥን “ረቂቅ ጥበብ አለው” ብለው አደን ያባት ነው
ያለውን እንሰሳ፣ የሰው ልጅ የሚፀየፈውን (የሚፀየፈው
የሚያስመስለውን) ምግባር ሲያሞካሹት እናያለን፡፡ ለወትሮውማ
ውሻ እንጂ ሰውማ በምግባር የከበረ ነው ባዮች ነን፤ በምፅዋት
እስትንፋሳቸውን ለማቆየት ከሰው በታች የዋሉ የኔብጤዎች
እንኳን በልመና ግጥሞቻቸው ይህንኑ ነው የሚያፀድቁልን፡-
ስጡኝ አንድ እንጀራ ውሻ የለከፈው፣
በምን ዐይኔ አይቼ እንዳልተጠየፈው፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የሕፃናቱን ልጅነት የሚነጥቀውን፣ ርህራሄ
አልባውን፣ ገንዘብ ጆሮውን የደፈነውን፣ መተሳሰብ ያጠጠበትን
ማኅበረሰብ አፍ አውጥቶ “ወዮልህ!” ሲለው እንሰማለን፤
“ወዮልሽ አዲሳባ!” ብሎ በባሕታዊ አንደበት አድማጭ
የሌለውን የበረሃ አዋጁን ሲጮህም እንሰማዋለን፡፡ ከፊቱ
በወደቀው ላይ ተረማምዶ ብቻውን የፅድቅን ሜዳሊያ
ለማጥለቅ የሚሽቀዳደመውን ሕዝብ እያሳየም ከራሳችን ጋር
ያስተዛዝበናል፡፡
የስብሃት ገብረ እግዚአብሔር ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ንባብ
*
መተዋወቂያ
***
በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ የራሳቸውን የተለየ አሻራ
አስቀምጠው ካለፉ ደራሲያን አንዱ የሆነውን የስብሃት ገብረ
እግዚአብሔርን ያህል ሲያወዛግበን የኖረ ደራሲ ያለን
አይመስለኝም፡፡ በተመሳሳይ ዘመን የተወገዘም የተመለከም
ደራሲ ነው፡፡ ይኽ ሁለት ጽንፍ የያዘ ልዩነት የመነጨው
ከሰውየው የድርሰት ብቃት አንጻር ሳይሆን ከሚነሳበት የሥነ-
ምግባር ጥያቄ አንጻር ነው፡፡ የአደራረስ ችሎታው ለጥያቄ
ሲቀርብም አይስተዋልም፡፡ የስብሃት ድርሰቶች አንባቢያቸውን
ከራሳቸው ጋር የሚያዛምዱባቸው ምትሃት አላቸው፡፡ “ሰባተኛው
መልአክ”ን ባነበብኩት ቁጥር የአየለን ፍርሃቶች፣ ሽንፈቱን
ለቀናት ከላዬ ላይ ማንሳት የሚያቅተኝ ስብሃት ስላዛመደኝ ነው፤
‹ሌቱም አይነጋልኝ›ን እያነበብኩ በዚያ ሁሉ የቡና ቤት ሁካታ፣
የወሲብ ጨዋታ መሃል የነማሚት ፍርሃት፣ የወጣቶቹ ተስፋ
መቁረጥ፣ ‹ከአድማስ ባሻገር› ላይ በዓሉ ጀምሮ የተወው የዚያ
ዘመን ወጣቶች የሰብዕና ሙጠት የሚጋባብኝ ከስብሃት ብዕር
የተነሳ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የአንባቢውን ስሜት ተቆጣጥረው
የመሰንበት ሥልጣን ያላቸው ደራሲዎቻችን፣ በጣት የሚቆጠሩ
ናቸው፡፡
ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በ1992 ዓ.ም. ባሳተመው ‹ሰባተኛው
መልአክ› ውስጥ ሦስት የተለያዩ ታሪኮች ይገኛሉ፡፡
ከመጀመሪያውና ‹ሰባተኛው መልአክ› ከተባለው ተረክ ውጭ
ያሉት ሁለቱ አጫጭር ልቦለዶች፣ ‹አጋፋሪ እንደሻው› እና
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የፋንታሲ ልቦለድ ባሕርያት ያሏቸው
ድርሰቶች ናቸው፡፡ እንዲያውም ስብሃት የፋንታሲ ሥነ-ጽሑፍ
ለአማርኛ ስነጽሑፍ ያስተዋወቀባቸው ናቸው ለማለት
እደፍራለሁ፡፡ እነዚህ ድርሰቶች ወደ ተረትነት የሚያደሉ፣ ምናባዊ
ነጻነታቸው እና ጉዳዮቻቸው ደግሞ ከተረትም የረቀቁ የፋንታሲ
ድርሰቶች የሚያደርጓቸው ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልቡና፣ እምነቱ፣
ፖለቲካው፣ ባህሉ፤ ሥጋዊው እና መንፈሳዊው ዓለሙ ሁሉ
ይጠየቁባቸዋል፤ ይመዘኑባቸዋል፣ ይተቹባቸዋል፡፡
“አጋፋሪ እንደሻው” ሞትን የሚሸሹት አጋፋሪ እንደሻው የተባሉ
ሽማግሌ የሽሽት ተረክ ነው፤ ተረኩ ሕልማዊውን ከእውናዊው
ጋር ይቀላቅላል፤ በትንታ አማካይነት የሞትን እና የሕይወትን
ድንበር አፍርሶ አጋፋሪን መንፈሣዊ ዓለም ውስጥ ይተርካቸዋል፤
እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ይኽንን የእሳቸውን ገድል የሚተርከውን
ደራሲ ሳይቀር በዚያ መንፈሳዊ ዓለም ነዋሪ ያደርገዋል፡፡ አቡነ
ተክለ ሃይማኖትን እና ቆሪጥን በፍልሚያ መድረክ ያገናኛል፤
ሞትን ሥጋ አልብሶ ከአጋፋሪ ጋር ያፋልማል፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የአጋፋሪ እንደሻው ልጅ የሆኑትን የአቶ
አልአዛርን መዋዕለ ዕብደት የሚተርክ፣ አንባቢውን በ“ሕልም
ዓለም” እና በእውን ዓለም መሃል የሚያዋልል ተረት ነው፡፡ ይኼ
አጭር ድርሰት የስብሃትን የበቃ ተራችነት፣ ጨዋታ አዋቂነት፣
በፋንታሲያዊ ተረኮች መመሰጡንም ይመሰክራል፡፡ ስብሃት በዚህ
ድርሰት እንደነ ሩድያርድ ኪፕሊንግ (The Jungle Book) እና
ሎፍቲንግ (Doctor Dolittle) እንሰሳን ከሰዎች ጋር በቋንቋ
ማግባባትን፣ እንደነ ጎጎል (The Nose) እና ጊ ደ ሞፓሳ
(The Hand) አንድን አካል ባለሚና ባለድርጊት አድርጎ ልቦለድ
ድርሰት ውስጥ የማጫወትን ብልሃት፣ እንደነሉዊስ ካሮል
ገፀባሕርያቱን የምንኖርበት ዓለም የማይፈቅድላቸውን ውላጤ
(transformation) የ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ዓለም
በሚፈቅድላቸው መጠን እንዲያካሒዱ ሲፈቅድ እናያለን፡፡
ይኽን ድርሰት የፋንታሲ ድርሰት ነው ለማለት ያስደፈሩኝም
እነዚህ ስብሃት ወደ ኢትዮጵያ ጽሑፋዊ ሥነ-ጽሑፍ የጋበዛቸው
የተረኩ ባሕርያት ናቸው፤ እነኚህ በላይኛው አንቀጽ ያሰፈርኳቸው
የ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ገፅታዎች፣ የሥነ-ጽሑፍ ዘውግ
አጥኚዎች ለፋንታሲ ዘውግ በመለዮነት ከሚያስቀምጧቸው
ባህርያት ጋር ይሰምራሉ፡፡ የራሱ የፋንታሲ ልቦለድ ዋነኛ
መለዮዎች ከሚባሉት ባሕርያት አንዱ በድርሰቱ ውስጥ
የምንኖርበት ዓለም ውስጥ ሊኖሩ/ሊደረጉ የማይችሉ ፍጡራንን፣
አካባቢዎችን፣ ድርጊቶችን/ክስተቶችን ... እንደሚቻሉ አድርጎ
ማቅረብ ነው፤ ይኽ ደግሞ እንግዳ ፍጡራንን (ለምሳሌ ቀንድ
እና ጭራ ያላቸውን ሰዎች፣ በራሪ ፈረሶችን)፣ ወይም ለዚህ
ዓለም እንግዳ የሆኑ ክስተቶችን (ከእንቅልፍ ሲነቁ ራስን ወደ
ነፍሳትነት ተለውጦ እንደማግኘት ያለ) በታሪኩ ውስጥ አሳማኝ
አድርጎ በማቅረብ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ስብሃት በ“ስምንተኛው
ጋጋታ” ለዚህ ዓለም አይቻሌ የሚመስሉ ውሻን ከሰው ጋር
እንደማግባባት፣ በተደገመበት ዕፅ ምክንያት ከአንድ ሰብዕና ወደ
ሌላ ሰብዕና እንደመለወጥ፣ ምንነቱ በግልፅ ያልተነገረውን
(ነገር ግን በምርመራ የሚደረስበትን) “እንትን” የተባለን አካል
የሰው ባሕርያት እንደማላበስ ያሉ ለምንኖርበት ዓለም እንግዳነት
(strangeness) ያላቸውን ነገሮች ለድርሰቱ አውሏል፡፡ ድርሰቱ
ውስጥ የተተረኩት ክስተቶች እና የተፈጸሙት ድርጊቶች፣
በትውፊታዊው/ሃይማኖታዊው የስምንተኛው ሺሕ ዋዜማ እና
የዕለቱ ዕለት መሆኑ፣ እንደ ስምንት ኪሎ መግደላዊት ያሉ
ሥፍራዎቹም የድርሰቱን ፋንታሲያዊነት ያጠናክራሉ፡፡
በ‹ስምንተኛው ጋጋታ› ውስጥ ስብሃት ትላልቅ ጥያቄዎችን
አንስቷል፣ ወይም ነባር እውነታችንን እና እምነታችንን
እንድንጠይቅ ገፋፍቶናል እላለሁ፡፡ ከመደበኛው ልቦለድ ይልቅ፣
ተረት መናገር የሚፈልጉትን ያላሉ በማስመሰል ተናግሮ ከጥያቄ
ለማምለጥ ይረዳል፤ ከተረት ተግባራት አንዱ እንዲያውም ይኼ
ለማምለጫነት ማገልገሉ ነው፡፡ ስብሃት ማምለጥ ይፈልግም
አይፈልግ በሌሎች ድርሰቶቹ ውስጥ በቀጥታ ያላስቀመጣቸውን
(አስቀምጧቸውም ከሆነ ጎልተው ያልተሰሙኝን) ሞጋች
ሐሳቦቹን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ባቀናበረው
በ‹ስምንተኛው ጋጋታ› በኩል አቀብሎናል፡-
ለምሳሌ ከታማኝ ዘብነቱ በቀር በአወንታ ስሙን
የማናዘወትርለትን ውሻን በሰው ላይ የምግባር ልዕልና አጎናፅፎ
ያመጣዋል፡፡ አቶ አልአዛር ኮምቡጠር የተባለ ውሻ አላቸው፤
በስምንተኛው ሺሕ ዋዜማ በቋንቋ ከባለቤቱ ጋር መግባባት
የሚጀምር ውሻ ነው፡፡ ይኽ ውሻ አድነን እንብላ የሚል ሐሳብ
ለጌታው ሲያቀርብ እሳቸው ግን “እንቀላውጥ” ይሉታል፡፡ ውሻን
በልክስክስነት የሚነቅፈው የሰው ልጅ ከውሻ በምግባር አንሶ
ቅልውጥን ለውሻ ሲያስተምር እናገኘዋለን፡፡ አቶ አልአዛር
ቅልውጥን “ረቂቅ ጥበብ አለው” ብለው አደን ያባት ነው
ያለውን እንሰሳ፣ የሰው ልጅ የሚፀየፈውን (የሚፀየፈው
የሚያስመስለውን) ምግባር ሲያሞካሹት እናያለን፡፡ ለወትሮውማ
ውሻ እንጂ ሰውማ በምግባር የከበረ ነው ባዮች ነን፤ በምፅዋት
እስትንፋሳቸውን ለማቆየት ከሰው በታች የዋሉ የኔብጤዎች
እንኳን በልመና ግጥሞቻቸው ይህንኑ ነው የሚያፀድቁልን፡-
ስጡኝ አንድ እንጀራ ውሻ የለከፈው፣
በምን ዐይኔ አይቼ እንዳልተጠየፈው፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› የሕፃናቱን ልጅነት የሚነጥቀውን፣ ርህራሄ
አልባውን፣ ገንዘብ ጆሮውን የደፈነውን፣ መተሳሰብ ያጠጠበትን
ማኅበረሰብ አፍ አውጥቶ “ወዮልህ!” ሲለው እንሰማለን፤
“ወዮልሽ አዲሳባ!” ብሎ በባሕታዊ አንደበት አድማጭ
የሌለውን የበረሃ አዋጁን ሲጮህም እንሰማዋለን፡፡ ከፊቱ
በወደቀው ላይ ተረማምዶ ብቻውን የፅድቅን ሜዳሊያ
ለማጥለቅ የሚሽቀዳደመውን ሕዝብ እያሳየም ከራሳችን ጋር
ያስተዛዝበናል፡፡