✨✨✨✨ ገምሃልያ ✨✨✨✨
✨✨✨✨ ክፍል 1 ; ✨✨✨✨
ፀሃፊ : ረምሃይ
እንደወትሮዬ ሁልግዜ ቅዳሜ ወይ እሁድ ከሰአት እምሰራው ስራ ከሌለኝ ከመፅሃፍ መደርደሪያዬ ላይ ውድ ጓደኞቼ በስጦታ መልክ ከሰጡኝ መፅሃፎች አንዱን አነሳና ቦሌ ማተሚያ አከባቢ ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝ ደስ እሚል በዛፎች የተሞላ ፓርክ አለ። ብዙ ግዜ እዛ ሄጄ መፅሃፍ ማንበብ እወዳለው። ዛሬ እለቱ ቅዳሜ ነው እዛ ሄጄ ለማንበብ የመረጥኩት ብርቅርቃ እሚለውን መፅሃፍ ነበር አሜን እምትባል ጓደኛዬ የሰጠችኝ መፅሃፍ ነው እሚገርመው ብርቅርቅታን የመሰለ አሪፍ መፅሃፍ እስከዛሬ አላነበብኩትም ነበር ከመደርደሪያው ላይ ስቤ ጠቅለል አድርጌው ይዤ ወጣው። መንገዴን ከቦሌ ድልድይ ጫፍ ወደ ስታዲየምና ሚክሲኮ በሚወስደው መስመር ታክሲ ተሳፍሬ ወደ ማተሚያ ቤት ሄድኩ። ማተሚያ ቤት ጋር ስደርስ ወርጄ በእግር መንገድ ወደ ውስጥ ወደፓርኩ ገሰገስኩ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ ሳልወድ በግድ ያሯሩጠኛል። እዛ ሰፈር ያሉት ፍየሎች ሁሌም ሳያቸው ያስቁኛል በጣም ትልልቅ ጥጃ ነው እሚያክሉት ምን እንደሚቀልቧቸው እንጃላቸው። እነሱን በአይበሉባ እየታዘብኩ ፓርኩ ጋር ደረስኩ ለመቀመጥ ሁለት ብር ከከፈልኩ በኃላ ሁሌም ወደምቀመጥባት ሰላማዊ ቦታ አቀናው ቦታዋ ጥግ ላይ ሁና ከሁሉም እይታ ገንጠል ብላ ጀርባዋን ሰጥታ ያለች ቦታ ናት ከፊትለፊቷ እሚያምር፤ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኝ የሙዝ እና የበቆሎ እርሻ ማሳ ይታያል። እናም ወደቦታዬ እየሄድኩ በልቤ ሌላ ሰው እንዳይቀመጥባት እየቋጠርኩ ሄድኩ ቦታዬ ላይ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ ከጀርባ ከሚታዩት ክብ መቀመጫዎች ላይ አንዲት በግምት በእኔ እድሜ አከባቢ እምትሆን ሴት ሲጋራ እያጨሰች አየኃት ለሽራፊ ሰከንዶች ቆም ብዬ ካየኃት በኃላ ወደቦታዬ ሄድኩ ማንም አልተቀመጠባትም ደስ አለኝ። በሸክላ ጡብ እና በሲሚንቶ የተሰራችውን መቀመጫ በሶፍት ጠረግኩና ተቀመጥኩ ቦታዋ ደስ ትላለች ሙሽሮች ሲጋቡ ለመድረክነት የሚጠቀሙባት ባለግርማሞገስ የድንጋይ ዙፋን ትመስላለች መደገፊያዋ ረጅም ስለሆነ ካልቆምኩ በስተቀር ከኃላዬ ምን እንዳለ አይታይም ያውም በኔ መለሎ ቁመት።
ቦታዬ ላይ ተረጋግቼ ከተቀመጥኩ በኃላ መፅሃፌን ከፈትኩና ሀ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ.... ግን ቅድም ሲጋራ እያጨሰች የነበረችው ሴት በአእምሮዬ ተመላለሰች ፊቷ የተከፋ ይመስላል ሲጋራውን በብሽቀት እየማገች ጭሱን ሽቅብ ትለቀዋለች ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት አሰብኩና ምን አገባኝ ብዬ መልሼ ተውኩት መፅሃፌን ማንበብ ቀጠልኩ። ግን የልጅቷ ሁኔታ አእምሮዬ ውስጥ እየተመላለሰ ሰላም ነሳኝ በመጨረሻም ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት ወሰንኩና መፅሃፉን ከድኜ አስቀመጥኩት። ወደሷ ሄድኩ እሷ የተቀመጠችበት ቦታ ከኔ ጀርባ ሆኖ ቅርብ ርቀት ላይ ነው ሄጄ ሰላም አልኳት የደረቀ ሰላምታ ሰጠችኝ። ሲጋራ ማጨስ እችላለው አልኳት ገልመጥ እያለች በእጇ መሃል የሚጤሰውን ሲጋራ ሰጠችኝ ተቀበልኳትና በጣቶቼ መሃል አድርጌ ጭሱ ሲበን ትንሽ ተከዝ ብዬ አየሁት በጎን በኩል የሸክላው ጡብ ወንበር መደገፊያ ላይ ወጥቼ እግሬን ደግሞ መቀመጫው ላይ አድርጌ ተቀመጥኩ። እሷን ምንም ሳልናገራት ሲጋራውን ዝም ማየት ቀጠልኩ ውስጡ የሷን ጭንቀት ይሁን ሃሳብ ይነግረኝ ይመስል ከጭሱ ውስጥ መልስ ፍለጋ ገባው። ልጅቷ ከሁኔታዋ ማውራት እምትፈልግ አትመስልም እንዲያ ባይሆን ኖሮ እንደዚ አይነት በብቸኝነት ሰላም እሚሰጥ ቦታ ባልመጣች ነበር። እሷ ማውራት ባትፈልግም እኔ ግን ማውራት ነበረብኝ። ሲጋራውን ትንሽ ካየሁት በኃላ ወደታች ዘቀዘቅኩት እሳቱ ሲጋራውን በፍጥነት ወደላይ ይበላው ጀመር ጭሱ ወደላይ ይበናል አመዱ ደግሞ ወደመሬት ይወድቃል። ልጅቷ እማደርግውን ዝምብላ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ምን ይታይሻል አልኳት ሲጋራ አለችኝ። እኔ ግን ህይወት ይታየኛል ምስቅልቅሉ የወጣ ህይወት ከላይ ወደታች የተገለበጠች ህይወት አመድ እና ጭስ የሆነ ህይወት እሳት የሆነ ፈተና። ህይወት እንደሲጋራው ቀጥ ተደርጋ በምቾት ስትያዝ እኛ የህይወትን ትርጉም አናውቅም እሳቱ ቀስ እያለ ሲጋራውን ይጨርሰዋል ነገር ግን ሲጋራው ሲገለበጥ መከራ ሲበዛብን እሳቱ ቶሎ ሲጋራውን ይበላዋል በመከራ ውስጥ ሆነን የህይወት ትርጉም ይገባናል ህይወታችችንን አጣጥመን ቶሎ ቶሎ እንኖራታለን እዚች ምድር ላይ ያለን ግዜ ውስን ስለሆነ ሲጋራው ወደታች ቢዘቀዘቅም ጭሱ ግን ወደላይ ነበር የሚጨሰው ፈተናውን የሚያልፍ ሰውም እንደዛ ነው ግን...... አልኳትና ዝም አልኩ ሲጋራውን ለልጅቷ መለስኩላት እና ተነስቼ ወደቦታዬ ለመመለስ ስዘጋጅ ግን ምን? አለችኝ ፈገግ ብዬ አየኃትና መልስ ሳልሰጣት ቦታዬ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ መፅሃፌን እንደነገሩ ከፍቼ ቁጭ አልኩ ልጅቷ እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ አንዳንዴ ሰው እንዴት እንደሚያስብ ስናውቅ ሰውን ማሞኘት ቀላል ይሆናል ልጅቷ መጀመሪያ ላይ ማውራት እንደማትፈልግና ብቻዋን መሆን እንደምትፈልግ ከሁኔታዋ ያስታውቃል ግን ደግሞ እኔ ምን እንደሆነች ማወቅ ፈልጊያለው ምን ሆነሽ ነው ብላት ቀጥታ እንደማትነግረኝ አውቃለው ማንያውቃል ምን አባህ አገባህ ብላ ታባረኝም ይሆናል ስለዚ የጭንቅላት ጨዋታ መጫወት ነበረብኝ ግን ብዬ የጀመርኩትን ሳልጨርስላት ተመለሼ ቦታዬ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ ስለዚህ አሁን ውሳኔው የሷ ይሆናል ማውራት ከፈለገች ትመጣለች ካልፈለገችም ሙከራዬ ከሸፈ እኔም ማውራት እማይፈልግን ሰው መጨቅጨቅ አልፈልግም።
እንዳቀድኩትም ልጅቷ ትንሽ ቆይታ ከተቀመጥኩበት ቦታ መጥታ ፊትለፊቴ ቆማ ግን ምን? አለችኝ እንደቅድሙ ፈገግ እያልኩ መፅሃፌን ዘግቼ ሲጋራውን ተቀበልኳትና እንድትቀመጥ ጋበዝኳት ከአጠገቤ ትንሽ ፈቀቅ ብላ ተቀመጠች። ሲጋራውን መሬት ላይ ጣልኩትና በእግሬ ጨፈለቅኩት ልጅቷ እንደመቆጣት እያለች ለምን አጠፋኀው አለችኝ በአንዴ ሁለት ጥያቄ መጠየቅ አይቻልም አሁን ከጠየቅሽኝ አንዱን ምረጭ አልኳት ከንዴቷ በረድ እያለች እሺ ግን ምን? አለችኝ። ሌላ ሲጋራ ይዘሻል ብዬ ጠየቅኳት አው ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገብታ ከፓኮው ውስጥ አንድ ፍሬ ሲጋራ አውጥታ ሰጠችኝ። ሙሉ ፓኮውን ስጪኝ አልኳት ምንም ሳትል አውጥታ ከነካርቶኑ አስረከበችኝ። ግን ምን? የሚለውን መልስ እየጠበቅች ነው። ግን ምን አለ መሰለሽ እኛ እንደጭሱ ጠንካራ ሆነን የተመሰቃቀለ የተገለባበጠ ህይወታችንን ተቋቁመን ወደላይ ስንወጣ ደካማ አመድ የሆነው ደግሞ ወደታች ይወድቃል ትቢያ ይበላል። ህይወት እንደዚ ናት ህይወት ብትገለባበጥ ብትመሰቃቀል አንቺ ጭሱን ወይ አመዱን ትሆኛለሽ ከሁለቱ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም! ስለዚ አንቺ ከየትኛው ወገን ነሽ አመድ ወይስ ጭስ አልኳት እንደማዘን እያለች አመድ አለችኝ ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ታዲያ ለአመድ ጭስ ምን ይሰራለታል አልኳትና በፓኮ ያለውን ሲጋራ አንድ ፍሬ አስቀርቼ የተቀረውን አርቄ ወረወርኩት የሲጋራው ካርቶን የፓርኩን የዛፎች አጥር አልፎ ወደ ውጪ ወደቀ እንዴ ለምን ወረወርከው አለችኝ እየተናደደች። እዛው እንደቆምኩ ወደሷ እያየው አመድ ከሆንሽ ጭስ ምንም አያደርግልሽም አይደል ሁለቱ በምንም እማይገናኙ እሚቃረኑ ተፈጥሮዎች ናቸው በከሰለ አመድ ውስጥ ጭስ የለም አልኳት እየተናደደች እሺ ጭስ ብልህስ ኖሮ አለችኝ።
አብሮነታችሁ አይለየን ቀጣይ ክፍል እንዲቀጥል 👍👍👍👍👍
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት
@DagiiHaile