ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ ሶስት
የማይሞተው ህያው አላህን ትተው ሙታንን የሚያመልኩ ሰዎች “ከአላህ ውጭ ያለን ምንንም አትጥሩ፣አትለምኑ ይህ ተግባራችሁ ሽርክ ነው።አላህ ብቻ ነው በሃቅ ሊመለክ የሚገባው ”ሲባሉ አሻፈረን ይላሉ። ዘወትር በሰላታቸው፦ “አንተን ብቻ እናመልካለን።በአንተም ብቻ እንታገዛለን” ማለታቸውን ይዘነጋሉ። በዚህ መልኩ ሲገሰጹም “ለምንድን ነው ታድያ ወደ ዶክተር የምትሄዱት” ሲሉ የሚመልሱ አሉ። የእኛ መልስ ግን “ታድያ ለምንድን ነው ወደሞተ ዶክተር የማትሄዱት?የሚል ነው?
ሙታን አምላኪዎች ተውሒድን አልተረዱም።እንዲህ አይነት የማይገናኝ ጥያቄ እያነሱ ፈተና ውስጥ ይድቃሉ።እውነትም ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም መንገድ ከተውሒድ ያፈነገጠ ቂል ነው።
ሰዎችን ሺርክን በሚገባ እንዳይጠነቀቁት የሚያደርጋቸው ጉዳዩን አርቀው መመልከታቸው ነው። እውነታው ግን ከምናስበው የቀረበ ነው።እስኪ ይህን በርካታ ሙስሊሞች የሚያደምጡትን መንዙማ እንታዘብ ፦
“ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ፣
ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ
ሌላ የሺርክ አዋጅ በስፋት ከሚደመጡ መንዙማዎች ውስጥ
“ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል በህር ፣
በሁሉም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር፣
ከዛፍ ከቅጠሉ በዝትብኛል ነውር ፣
እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር ፣
መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር፣
አልሄድ ወደ ፊት ዘደ ኅላ አልበር ፣
በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር፣
አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር ፣
ረዳቴ ማን ነው ከናንተ በቀር።”
አሁንም ሌላኛው የሽርክ መንዙማ እንዲህ ይላል
“ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ ፣
መዲና ና ይበሉኝ።”
ይህን አደጋ ተመልከቱ ።የፍጡራን ሁሉ ረዳት አላህ ብቻ ነው።የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ አላህ ብቻ ነው።አለምን የሚያስተናብረው አላህ ብቻ ነው።አላህ እንዲህ ይላል፦
أَلَيْسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبْدَهُۥ ۖ وَيُخَوِّفُونَكَ بِٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦ ۚ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍۢ
አላህ ለባሪያውን በቂ አይደለምን? በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በኾኑትም (ጣዖታት) ያስፈራሩሃል፡፡ አላህ የሚያጠመውም ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡[አዝ-ዙመር:39]
አማኞች ሰላት ላይ ሆነው በተደጋጋሚ እንዲህ ሲሉ ቃል ይገባሉ ፦
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡[አል ፉርቃን:58]
በየትኛውም ዘመን ከአላህ ውጭ የሚመለኩት ሁሉ ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም።ሁሉም የአላህ ፍጡሮች ናቸው፣ሁሉም ሟቾች ናቸው፣ ሁሉም ጠፍተው የልቅናና የንግስና ባለቤት የሆነው የጌታ የአላህ ፊት ይቀራል።
አማኞች በአላህ ላይ ብቻ መመካት እንዳለባቸው አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦
إِن يَنصُرْكُمُ ٱللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمْ ۖ وَإِن يَخْذُلْكُمْ فَمَن ذَا ٱلَّذِى يَنصُرُكُم مِّنۢ بَعْدِهِۦ ۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ
አላህ ቢረዳችሁ ለእናንተ አሸናፊ የለም፡፡ ቢያዋርዳችሁም ያ ከርሱ (ማዋረድ) በኋላ የሚረዳችሁ ማነው በአላህም ላይ ብቻ ምእምናን ይመኩ፡፡[አል-ኢምራን:160]
ልክ እንዲሁ አላህ ብቻ ሊፈራ ሲገባው ከአላህ ውጭ ያሉ አካላትን መፍራት ለምሳሌ ፦ጂንን ይመታኛል፣ ሸሆቹ ልጄን ይቀሙኛል፣ ሃብቴን ያወድሙብኛል፣እንዲህ ያደርጉኛል ብሎ መፍራት ሺርክ ነው
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 25-27)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide