ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል ሀያ
14.የአባቶቻችን መንገድ
አብዛኛዎቹ ህዝቦች መልክተኞች ምን ይዘውላቸው እንደመጡ ገብቷቸዋል።ሆኖም ግን መልክቱን ላለመቀበል ካዳገዳቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የአባቶቻቸውን ውርስ ለመተው አለመፍቀዳቸው ነው ።አላህ እንዲህ ይላል፦
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ ٱللَّهَ وَحْدَهُۥ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا ۖ فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
«አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን ከውነተኞች ከኾንክ የምታስፈራብንን (ቅጣት) አምጣብን» አሉ፡፡ [አል-አዕራፍ :70]
አባቶቻችንን ተምሳሌት ልናደርግ የሚገባው በተውሒድ፣በሱንና በሐቅ ላይ ሲሆን ብቻ ነው።የአላህ ነብይ ዩሱፍ ምን እንዳሉ አላህ እንዲህ ይላል፦
وَٱتَّبَعْتُ مِلَّةَ ءَابَآءِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ ۚ مَا كَانَ لَنَآ أَن نُّشْرِكَ بِٱللَّهِ مِن شَىْءٍۢ ۚ ذَٰلِكَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ عَلَيْنَا وَعَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
«የአባቶቼንም የኢብራሂምንና የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፡፡ ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም ያ (አለማጋራት) በእኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡❨ዩሱፍ 38)
የታዘዝነው ከሽርክ እና ከቢዳዓ የፀዱትን የቀደምቶቹን የነብዩ ﷺ ፣ሰሃቦቻቸው ፣እና ሰለፉነ ሷሊሁንን መንገድ እንድከተል ነው።
15.አማኞቹ ጂኖች በአላህ ላይ አናጋራም ማለታቸው።
አማኝ ጂኖች በነብዩ ሙሐመድ ﷺ ላይ የወረደውን የአላህ ቃል ቁርአን ከሰሙ ቦኋላ በጌታችን አላህ ላይ አናጋራም በማለት እንዲህ ሲሉ መመስከራቸውን ጌታችን አላህ ይነግረናል ፦
قُلْ أُوحِىَ إِلَىَّ أَنَّهُ ٱسْتَمَعَ نَفَرٌۭ مِّنَ ٱلْجِنِّ فَقَالُوٓا۟ إِنَّا سَمِعْنَا قُرْءَانًا عَجَبًۭا
(ሙሐመድ ሆይ!) በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡
يَهْدِىٓ إِلَى ٱلرُّشْدِ فَـَٔامَنَّا بِهِۦ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَآ أَحَدًۭا
‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡› [አል-ጂን:1-2]
ቀደም ብለን እንዳሳለፍነው ጂኖችም ልክ እንደ ሰው ልጅ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ ነው የተፈጠሩት።ልክ ከሰው ልጅ አማኝ፣ከሃዲ፣አመፀኛ እንዳለ ሁሉ ከነሱም ውስጥ እንዲሁ አማኝ፣ከሃዲ፣ እና አመፀኞች አሉ። አማኞቹ ጂኖች ይኸው “በጌታችን ላይ አናጋራም” ማለታቸውን አላህ ነገረን።በሌላ ቦታ ላይ አማኝ ጂኖች ለህዝቦቻቸው ነብዩን ﷺ እንዲከተሉ እንዲህ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን አላህ እንደሚከተለው ይነግረናል፦
يَٰقَوْمَنَآ أَجِيبُوا۟ دَاعِىَ ٱللَّهِ وَءَامِنُوا۟ بِهِۦ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍۢ
ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና፡፡
وَمَن لَّا يُجِبْ دَاعِىَ ٱللَّهِ فَلَيْسَ بِمُعْجِزٍۢ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَيْسَ لَهُۥ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءُ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ
የአላህንም ጠሪ (ነብዩ ሙሐመድ ﷺ)የማይቀበል ሰው በምድር ውስጥ የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ከእርሱም ሌላ ለእርሱ ረዳቶች የሉትም፡፡ እነዚያ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ናቸው» (አሉ)፡፡ [አል አሕቃፍ :31-32]
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 40-42)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide