Ethio Space (ኢትዮ ጠፈር)


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሰለ ሌሎች ዓለማላቶች እና አስትሮኖሚ ሳይንስ ስታስብ በሰዎች መካከል ያሉት የጎሳ ,የብሔር ,የሐይማኖት ልዩነቶች እንዲውም የአገር ልዩነቶች ለአንት ተራ ነገሮች ይሆናሉ ምክንያቱም እራስክን የምታነፃፅረው በሌሎች አለማት ላይ ይኖራሉ ተብለው ከሚታሰቡ ልዩ ፍጥሮች ጋር ይሆናል ሰለዚህ አንት ሰው ከሆነክ በቂ ነው ምክንያቱም ሰው መሆንክ በራሱ በቂ ማንነት.. @unverseand 👈ለcross

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አብዛኞቻችሁ ዩፎዎች በላሊበላ ላይ ታዩበት የተባለው ቪዲዮ በጠየቃችሁኝ መሰረት ያው 🙌🏿

📆 || ተቀረፀ የተባለው 2006 አ.ም ነው !

🎥 || ዩፎዎች በላሊበላ ላይ ታዩ የተበሉበት ቪዲዮ ! 👽

ሼር በማረግ ተባበሩን ቤተሰብ ! 🙏🏿❤️

ሙሉን ቪድዮ ለማየት 👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


👆ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአለማችን ትልቁ የሬድዮ ቴሌስኮፕ ሲሆን መገኛውም በደቡብ ምዕራብ ቻይና በፒንግታንግ ካውንቲ ይገኛል።
ይህ ቴሌስኮፕ አጠቃላይ 500 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን 4,450 ፓነሎች አሉት።

ይህም ለምድራችን ስለ ጋላክሲዎች፣ ፕላኔቶች፣ ጥቁር ጉድጓዶች፣ ኮከቦች፣ ከምድር ውጭ ስላሉ ነገሮች ብዙ መረጃዎችን ይሰበስባል።

Join and share

@Ethio_tefer0    @Ethio_tefer0

@Ethio_tefer0     @Ethio_tefer0


​▬▬ ስለ ጨረቃይህንን ያውቁ ኖሯል❓ ▬▬

📚ጨረቃ ከመሬት 384,399ኪ.ሜ ትርቃለች።

📚ሙሉ ጨረቃ ከግማሽ ጨረቃ 9 እጥፍ ትደምቃለች።

📚 ኒል አርምስትሮንግ(ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን የረገጠው ሳይንቲስት) ጊዜው በ1969 እ.አ.አ ነበር አስቀድሞ በግራ እግሩ ነበር ጨረቃን የረገጠው።

📚በመሬት ላይ 60 ኪ.ግ የሚመዝን ሰው ጨረቃ ላይ ሲወጣ ግን 10 ኪ.ግ ነው።

📚በምድር ላይ የተዘረጉ የባቡር ሀዲዶች ቢቀጣጠሉ ጨረቃ ላይ ደርሰው መመለስ ይችላሉ።

📚የጨረቃ ክብደት የመሬትን 0.0123 ነው።

📚 ጨረቃ በመሬት ዙርያ ለመዞር 27.321 ቀን ይፈጅባታል።

📚 መሬት ከጨረቃ 400 እጥፍ ትገዝፈለች።

📚 በታሪክ ውስጥ ሙሉበሙሉ ጨረቃ ያልታየበት ወር February ወር 1865 ነው።

ለሌሎች ያጋሩ👇👇👇👇

@Ethio_tefer0    @Ethio_tefer0 
@Ethio_tefer0     @Ethio_tefer0 


በዚህ ግዙፍ ዩንቨረስ ውስጥ ብቻችንን ነን ?

አንድ ትልቅ መሬት የምትባል ፔላኔት ላይ እንኖራለን በማታም እጅግ ብዙ ክዋክበት እንመለከታለን በቁጥር ምን አልባት ቢልዮን እና በትርልዮን ይቆጠራሉ እንዚህም ክዋክብት በዙሪያቸው በትንሹ አንድ የኛን አለም የሚመስል ፕላኔት ወይም ዓለም እየዞራቸው ነው ይሄ ማለት በማታ የምናያቸው እያንዳዷ ኮከብ ዙሪያ የኛን አለም የሚመስል ፕላኔት አለ ምን አልባትም ፉጡሮች እየኖሩባቸው ያሉ እንዚህ ዓለምም ሁሉ ነገራቸው ከኛ አለም ፍፁም የተለየ ይሆናል።

ዩንቨረስ ጥግ ብሎ ነገረ የለውም የፕላኔቶች ቁጥር ሆነ የክዋክብት ቁጥር ማለቂያ የለሽ ነው ብርሃን በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ እንኳን የማይደርስባቸው ለመቁጠር የሚታክቱ አለማት አሉ ምን አልባት የኛን መገኛ እንደ አንዲት ትንሽዬ አሳ ብንወስዳት ዩንቨርስን እንደ ትልቅ ውቂያኖስ ልንቆጥረው እንችላለን በዚህ ትልቅ ውቂያኖስ ውስጥም አንድ አሳ ብቻ ሊኖር አይችልም ሳይንቲስቶችም እንዲ ሲሉ ይጠይቃሉ በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ እኛ ብቻችንን ነን?

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ለአንድ ወር የሚቆይ የሕዋ ዘርፍ ሥልጠና ሊሰጥ ነው።

ኢንስቲትዩቱ በሕዋ ዘርፍ ፍላጎትና ተሰጥኦ ያላቸውን 50 ተማሪዎች ሊያሰለጥን መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ለአራዳ ኤፍኤም ተናግረዋል።

ስልጠናው ከቡራዩ የተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በተሰጥኦዋቸው ለተለዩ 50 ተማሪዎች ከነሐሴ 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ በነጻ ይሰጣል ብለዋል።

ሥልጠናው በአስትሮኖሚና አስትሮ ፊዚክስ፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ኤሮስፔስ ኢንጅነሪንግ፣ ጂአይኤስና መሰል ዘርፎች እንደሚሰጥ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ከሥልጠናው በኋላ ሰልጣኞች ፕሮጀክት እንደሚሠሩና ወደ ምርት (prototype) እንዲቀየሩ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇
@ethio_tefer0 @ethio_tefer0
🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽
@Ethio_tefer @Ethio_tefer


#SHOCKING_FACT

በአንድ ሰው ውስጥ ብቻ ያለውን ጠቅላላ DNA ብንቀጣጥለው የሶላር ሲስተማችንን Radius 4 እጥፍ የሚያክል ወይም ጨረቃችንን 150,000 ጊዜ መጠምጠም የሚችል ርዝመት ይኖረዋል🤯

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


ናሳ ከምድር 20 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር ርቆ ጠፍቶበት የነበረውን መንኮራኩር መልሶ አገኘ

ናሳ ከምድራችን 20 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጠፍቶብኝ ነበር ያለውን መንኮረኩር መልሶ ማግኘቱን አስታወቀ የአሜሪካው ግዙፉ የጠፈር ምርምር ማዕከል ከእአአ 1977 ጀምሮ ጠፈርን ሲያስስ ከነበረው መንኮራኩር ጋር የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስታውቆ ነበር።

ባለፈው ወር ቮይጀር-2 ወደተባለው መንኮራኩር በስህተት የተላከ ትዕዛዝ መንኮራኩሩ ከምድራችን በሁለት ዲግሪ አንቴናውን እንዲያዞር በማድረጉ ግንኙነት ተቋርጦ ናሳ መልዕክት መቀበልም ሆነ መላክ ተስኖት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ናሳ ትናንት ማክሰኞ በአጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) ላይ የተለመደ ዳሰሳ እያደረገ ሳለ ከመንኮረኩሩ መልዕክት እንደደረሰው አስታውቋል ቮይጀር-2 አሁን ያለው የት ነው? ቮይጀር-2 አሁን ላይ ከምድራችን 19.9 ቢሊዮን ኪሎ ሜትሮች ርቆ በከዋክብት መገኛ አካባቢ በሰዓት 55 ሺህ ኪሎ ሜትር እየበረረ ይገኛል ከሐምሌ 14/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከናሳ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ የነበረው ቮይጀር-2 በአሁን ወቅት በናሳ ኔትወርክ ውስጥ መልሶ መግባቱ ዳግም ከመንኮራኮሩ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይቻላል የሚል ተስፋን ፈጥሯል።


መንኮራኮሩ ከምድራችን 20 ቢሊዮን ኪሎ ሜትሮችን ርቆ መገኘቱ ከመንኮራኮሩ የወጣው መልዕክት ወደ ምድር እስኪደርስ 18 ሰዓታት ሳይወስድ አይቅርም ተብሏል ናሳ መልዕክቱን መቀበሉ መንኮራኮሩ አሁንም መረጃ እያሰራጨ እና “በጥሩ ሁኔታ” ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው ብሏል።

ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇
@ethio_tefer0 @ethio_tefer0
🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽
@Ethio_tefer @Ethio_tefer


ጊዜ እና በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው

በአሁን ዘመን እንቆቅልሽ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጊዜ ሲሆን በየዘመኑ የሚመጡ ሳይንቲስቶች ብዙ ብለውለታል የሚገረመው ነገረ ጊዜን በተመለከት አሁንም ድረስ ደፍሮ ይሄ ነው ብሎ የሚናገረ ሰው አለመኖሩ ነው ጊዜ አንፃራዊ ነው ከማለት ውጭ።

ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ለምን ይሄዳል ? መቼ ጀመር ? መቼስ ያቆማል? ጊዜ ከስበት ጋር ያለው ግንኙነት ምንድነው ከፍጥነት ጋርስ ያለው ግንኙት ምንድነው በብርሃን ፍጥነት ብንጓዝ ጊዜ ይቆማል ወይስ ወደ ዋላ ይቆጥራል? ጊዜ ወደ ዋላ መመልስ ይችላል? በጊዜ ጉዳይ እንዚህ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ ሳይንሳዊ ማስረጃ መስጠት ያልተቻለባቸው ጥያቄዎች ናቸው።

በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው ?

በጊዜ መጓዝ ማለት አሁን ካለነበት ሰአት  ወደፊት ወይም ወደዋላ መሄድ ነው ወደፊት የምንሄደ ከሆነ የወደፊቱን ሂደን ማየት እንችላለን ወደ ትክክለኛው ቦታ በመመለስ የወደፊቱን በተንበይ ወይም መናገር እንችላን ወይም የሆንን ቴክኖሎጂ በማምጣት ሰዎች ሳይጠቀሙት መጠቅም እንችላለን ለዚህም ጥሩ ማሰረጃ የሚሆኑት ስልክ ባልተፈጠረበት ዘመን ስልክ ሲያወሩ የሚታዩ ሰዎች መኖራቸው ነው።

በጊዜ ወደ ዋላ መጓዝ ደግሞ አሁን ካለንበት ሰአት ወደ ዋላ በመሄድ ከዚህ በፊት የነበረውን ክስተት መመልከት መቻል ነው ምን አልባት ከዚህ በፊት የተበላሹብንን ነገረ ወደ ዋላ በመሄድ ማስተካክል እንችል ይሆናል።

በምን አይነት መንገድ ነው በጊዜ መጓዝ የሚቻለው?

በጊዜ ለመጓዝ ትልቅ ማሽን መሰራት አለበት ተብሎ ይታሰባል ይሄ ማሽን በእንግልዘኛው "time machine" ይባላል ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ዎርምኦልን መጠቀም ነው የሆነው ሁኖ ሳይንቲስቶች  እስከ 2100 ድረስ በጊዜ መጓዝን እውን ለማድረግ እየሰሩ ነው።

በርግጥ ይሄ በጊዜ በጓዝ በአሁኑ ዘመን በእሳቤ ደረጃ ብቻ የሚገኝ ነገረ ሲሆን በውስጡም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ አብዛኞቹ ባአሁኑ ዘመን የሚገኙ ሊቃዎንትም እብደት ወይም የማይቻል የሚሉት አይነት እሳቤ ነው።

ጥንት ጥንት የሰው ልጆች ኢንተርኔትን እና ሙባይል ስልክን የማይታሰብ ቴክኖሎጂ ብለውት ነበር በአሁኑ  ዘመን ግን ተሰርቷል የወደፊቱ የሰው ልጆች ይሄንን "time machine" ሰርተው በጊዜ ይጓዙ ይሆን የብዞች ጥያቄ ነው

በጊዜ ወደዋላ ወይም ወደፊት መሄድ ቢቻል ምን ታደርጉ ነበረ?

የዩቲውም ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


ጀምስ ዌብ የተሰኘው ቴሌስኮፕ ዛሬ ወደ ምድር የላከው ምስል ሲተነተን "ይሄ ምስል የጋላጊስዎች ስብሰብ ወይም አንድ ክላስተር ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ይሄ የጋላክሲዎች ሲብስብ ዩንቨረስ ከተፈጠር ከ6 ቢሊዮን ዓመት በህዋላ የተፈጠረ ነው ይሄ ምስል የሚያሳየው ደግሞ ከ7 ቢልዮን ዓመታት በፊት የነበረውን የጋላላክሲዎቹ ግፅታ ነው አሁን ላይ እንዚህ ጋላክሲዎች ምንም አልባትም ከዩንቨረስ ጠፍተው ይሆናል!!!

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


እጅግ አስፈሪ ስለሆነው #ቤርሙዳ #ትሪግል ምን ያሀሎቻቹ ታቃላቹ? ይህ አስፈሪ የሆነውን ስፍራ እንሆ በጥቂቱ

⏩ሊገለፅ የማይችል እጅግ አሰፈሪ ስፍራ ከ300 በላይ መርከቦች ገብተው የጠፉበት ከ75 በላይ አውሎፕራኖች ደብዛቸው የጠፋበት ቤርሙዳ ትሪያግል ይባላል::

⏩በርካቶች እሚስማሙበት ነገር ቢኖር የሴጣን ምድር ነው በማለት ነው የትኛውም ሳይንቲስት መርከቦቹና አውሎፕራኖቹ ሰምጠው እሚቀሩበትን ምክንያት ማወቅ አልቻለም::

⏩በአትላንቲክ ውቅያኖስ መሀል በአሜሪካዋ ግዛት ፍሎሪዳ አልባድሪ ይገኛል ይህ አከባቢ የ3 ማእዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን ስፋቱም  ወደ ሁለት መቶ 70 ሺ እስኩር ማይልስ ይጠጋል;;

⏩አንድ አንድ ሰወች ይህን ሚረጉት የባህር ለይ ጭራቆች ናቸው ሲሉ አንድ አንዶች ደሞ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ፍጥረታት ናቸው ይላሉ አንድ አንድ አጥኚዎች ግን በውሀ ውስጥ እሚፈጠር ከባድ አውሎ ንፋስ ነው ይላሉ::

⏩5 ቶፔዶ  ቦንብ ጣይ አውሎፕራኖችናአነስተኛ ጀቶች በ1945 የእቃ ማጓጓዣ መርከብ በ1943  al faro የተባለ የእቃ ማጓጓዣ መርከብ በ2015 እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር እነዚና ሌሎች በዚ ሶስማዘን በሚመስል በውሀ በተከበበ ክፍል ጠፍተዋል::

⏩ቦታው እንዳለው ዝና ግን በርካቶች ሊጉበኙት አልቻሉም ሆኖም ግን በየቀኑ ቁጥራቸው የበዛ የንግድ አውሎፕራኖች ሲበሩ ይውላሉ::

⏩ይህ በውሀ የተከበበ ስፍራ ውስጥ ብቻ የሚገኙ  እጅግ በጣም አስፈሪ የሆኑ ፍጥረታት ይገኛሉ ከነሱም ውስጥ ድራጎን ፊሽ  ባምፓዬር አስኮዴት ጎብልን ሻርክና ባምፓየር ሻርክ በጥቂቱ ናቸው::     ከዚ ቡሀላስ የቤርሙዳ ሚስጥር ይገኝለት ይሆን?


ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


🛑ፕላኔት ኤክስ (PLANET X )

በስርአተ ፀሀይ ውስጥ እጅግ በጣም ትልቁ ፕላኔት ነው በርግጥ ፕላኔቱ በሳይንስ ሙሉ በሙሉ እንዳለ አልተረጋገጠም planet x እንደማንኛውም ፕላኔት ፀሀይን ይዞራል ነገርግን ዑደቱ ወይም የሚዞርበት ርቀት በጣም ረጅምና በዝግታ ነው የሚሽከረከረው፡ ፀሀይን 1 ጊዜ ለመዞር በሺ የሚቆጠር አመት ይፈጅበታል ይህ ፕላኔት በሺ አመት አንዴ ብቅ ሲል ታድያ ብዙ ሺ መዘዝ ይዞ ነው የሚመጣው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


📿 #2050 ዓለማችን ምን ትመስላለች.........

#1. የዓለማችን የህዝብ ቁጥር ከ9 ቢሊዮን ይበልጣል።

#2. ከ 50 በመቶ በላይ የስራ ዕድሎች በሮቦቶች ይተካሉ። በዚህም የተነሳ ስራ አጥነት ያሻቅባል።

#3. ህንድ በህዝብ ቁጥሯ ቻይናን ትበልጣታለች።

#4. የህክምና ጥበብ እጅጉን ስለሚራቀቅ በአደጋ ካልሆነ በቀር የትኛውም የዓለም ህዝብ 80 ዓመት ሳይሞላው አይሞትም።

#5. ተማሪዎች ቦርሳ ሳይሆን ታብሌትና ላፕቶፕ ይዘው ነው ት/ቤት የሚሄዱት። ብላክ ቦርዶቹ ሁላ ተች ስክሪን ይሆናሉ።

#6. በዛ ጊዜ ለመዝናናት ላንጋኖ ወይም እንጦጦ ሳይሆን የሚሄዱት ጨረቃና ማርስ ላይ ነው።

#7. 75 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ በከተማ መኖር ይጀምራል።

#8. በዓለም ሙቀት መጨመር የተነሳ አንዳንድ #ደሴቶችና ከባህር ዳርቻ ያሉ ከተሞች በውሃ ይዋጣሉ።

#9. ቤንዚልን እንደ ነዳጅ መጠቀም የሚቀር ሲሆን በእሱ ምትክ #ሃይድሮጅን ጥቅም ላይ ይውላል።

#10. ቤት ለመስራት እንጨት መፍለጥ፣ ሚስማር መደብደብ፣ ብሎኬት መደርደር አይታሰብም።

📿 በ3D ፕሪንት ቴክኖሎጂ ቤትዎ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ተገንብቶ ያልቃል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


በናሳ ሕግ መሰረት ጠፈር ላይ ወይም በሌሎች ፕላኔቶች ላይ "sex" ማድረግ የተከለከለ ነው ይሁን እንጂ አሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ተደርጎ የተገኝ አውንታዊ ወይም አሉታዊ ግኝት የለም እንደ አንዳድ ሳይንቲስቶች ግምት ከሆነ ግን ጠፈር ላይ የሰው ልጅ የ"sex" ፍሎጎት በእጅጉን ይወርዳል።

ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


#Astronomical_event🤩🤩🤩

💥ውበቱን ተመልከቱ🥳🤩🤩
.
.
‼️ ለጓደኞቻችሁ ሼር እያረጋችሁ ቤተሰብ በቅርቡ በአዲስ አቀራረብ እንመጣለን!!!


Join and share

@Ethio_tefer0    @Ethio_tefer0

@Ethio_tefer0     @Ethio_tefer0


ልክ በዛሬዋ ቀን የዛሬ 45 ዓመት ናሳ የማይቻለው ነገረ ነገረ አደለገ የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የጨረቃን ምድር እረገጥ !!!

ከታሪክ ማህደር

Join and share

@Ethio_tefer0    @Ethio_tefer0

@Ethio_tefer0     @Ethio_tefer0


#ኒፍሊሞች

ኑፍሊሞች በግሪካውያን አፈታሪክ ውስጥ የሚነገርላቸው ግዙፋን ፍጥረታት ናቸው። ኒፍሊሞች አመጣጣቸውንና አፈጣጠራቸውን ቅዱስ ሔኖክ በመፀሀፉ ላይ አስቀምጦ ሚስጥሩን  በ ቅዱስ ሔኖክ መፀሀፍ ላይም አንደተገለፀው(የሰው ልጆች ከበዙ በኀላ እንዲህ ሆነ በእነዚያ ወራት መልከ መልካሞች ልጆች ሴት ልጆች ተወለዱላቸው መላእክትም እነርሱን አይተው ወደዷቸው እርስ በእርሳቸውም ኑ ለእኛ ከሰው ልጆች ሴቶችን እንምረጥ ለእኛም ልጆችን እንውሰድ አሉ ይላል።

ከዛንም ሰአት በሁአላ ልጆችን ወለዱ ለሰው ልጆችም እግዚብሔር እንዲገለጡ ያልፈለጋቸውን ሚስጥራት እና ጥበባት ሁሉ ማስተማር ጀመሩ እነዚህም ፍጥረታት ቁመታቸው 3ሺ ክንድ ሲሆን ማንንም የማይምረውን እና ማንም የማይችለውን ሀያል ፍጡር እንኳን በቀላሉ ይዘው ይመገቡ ነበር ኒፍሊሞች እርስ በራሳቸው ሳይቀር እንደተበላሉ የሚያስረዱ ማስረጃዎች እየተገኙ ይገኛሉ።


 እነደተገኙት ማስረጃዎችና እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ ኒፍሊሞች ከእኛለም ውጪ ያሉ ፍጥረታት መነሻናት ከምትባለው ኒብሩ(ፕላኔትx) የመጡናቸው ተብሎ ይታሰባል ኒብሩ የተለያዩ የረቀቁ ፍጥረታትና በድንቃድንቅ ነገሮች የተመላች እንደሆነች ይነገርላታል ኒፍሊሞችም ከዚያች ፕላኔት አንደመጡ ይታሰባለል ስለ ኒፍሊሞችን መረጃዎችን ሳሰባስብ ካገኝሁአቸው  አስገራሚ ነገሮች መካከል ቁመታቸው ከመርዘሙ የተነሳ በእናቶቻቸው እምብርት በኩል ሰንጥቀው ይወጡ አንደነበርና ዳመናን አየገፉ ይሔዱ እንደነበር አንብቤያለሁ ምናልባትም ኒፍሊሞች በተሰወረችው የሰብአዳት ከተማ ወይም በኒብሩ ሊኖሩ ይችላሉ።

Join and share

@Ethio_tefer0    @Ethio_tefer0

@Ethio_tefer0     @Ethio_tefer0


መሬት ላይ ሁንን በአይናችን የምናያቸው ፕላኔቶች ይኖሩ ይሆን?

በኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ መሬትን ጨምሮ ስምንት ፕላኔቶች ያሉ ሲሆን ከስምንቱ  5ቱን በምሽት መሬት ላይ ሁንን በአይናችን ማየት እንችላለን

መሬት ላይ ሁነን የምናያቸው ፕላኔቶች ሜርኩሪ,ቬኑስ,ማርስ,ጁፒተር እና ሳተርን ናቸው

እንዴት አድርጌ ማየት እችላለው?

ፕላኔቶቹ በማታ ሲታዩ ኮከብ ሰለሚመስሉ መለየት ይከብዳል ነገረ ግን ፕላኔት መሆናቸውን በሁለተ መንገድ መለየት ይቻላል አንደኛው ሲያበሩ እንደክዋክብት አይርገበገቡም በዚህ መሰረት ማታ ላይ የምታዮቸውን ፕላኔቶች ከክዋክብት መለየት ትችላላቹ ሁለተኛው ነገረ ደግሞ አብዛኞቹ ፕላኔቶች የሚገኙት ጨረቃ ወይም ፀሐይ በምትንቀሳቀስበት አቅጣጫ ወይም ቦታ ነው ።

ማየት የምትፈልጉ ካላቹ በማታ ፀሐይ ወታ በምትገባበት ወይም ጨረቃ በምትንቀሳቀስበት አቅጣጫ ቅኝት ብታረጉ ከነዚህ ካላይ ከጠቀስናቸው ፕላኔቶች መካከል አንዳቸውን ለማየት ትችሉ ይሆናል።

የቲኛውን ፕላኔት እያየው እንደሆነ እንዴት ላወቅ እችላለው?

የትኛውን ፕላኔት እያያቹ እንደሆነ ለማወቅ ከፈለገቹ ደግሞ እናተ በምታዩበት ወቅት የሚታዩ ፕላኔቶች የቲኞቹ እንደሆኑ ማጣራት ይኖርባቹዋል

እንዴት ላጣራ?

ጎግል ላይ "What planet is visible today?" ብላቹ ሰርች በማድረግ ማየት ትችላላቹ።

👆👆ከላይ ከትላንት እስከ ዛሬ እየታዩ ያሉ ፕላኔቶችን ዝርዝር አታች አድርገናል።

subscribe🙏🙏🙏👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


🌪በቤርሙዳ ትሪያንግል አካባቢ ገብተው ከመሰወራቸው በፊት ፓይለቶች እና ካፒቴኖች የመጨረሻ ቃላቸውን በዝርዝር እንመልከት

🌪አንዳንዶቹ የተናገሩት በጣም ሚያስደነግጥ ነው። በዛ ሰአት ምንድን ነው ያዩት ?

🌪ታህሳስ 15 1945 ከጠፉት 19 አውሮፕላኖች ውስጥ አብራሪዎቹ ለመጨረሻ ጊዜ ቃላቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው። እና እነዚ የመጨረሻ ቃላቶቻቸው record ተደርጎ ተቀምጧል።

🌪የመጀመሪያው ጥሪ

"ሄሎ ይሄ አስቸኳይ ጥሪ ነው። መሬት አይታየንም , ከበረራ መስመራችን የወጣን ይመስለኛል።"

🌪ሁለተኛው ጥሪ

"ያለንበት ቦታ የት እንደሆነ እርግጠኞች አይደለንም። መንገዱ የጠፋን ይመስላል።"

🌪ሶስተኛው ጥሪ

" ምእራብ በየትኛው አቅጣጫ እንደሆነ አናውቅም። ሁሉም ነገር ትክክል አይደለም ይገርማል።" ብሎ ተቋርጧል ጥሪው

🌪አራተኛው ጥሪ

"ውቅያኖሱ የተለመደ መልኩን አልያዘም።" ብሎ የዚኛውም ጥሪ ተቋርጧል።

🌪አምስተኛው ጥሪ

"እኔን ተከትላቹ አትምጡ። ከሌላ አለም የመጡ ይመስላሉ። ብሎ የዚኛውም ጥሪ ተቋርጣል።

🌪 ስድስተኛው ጥሪ

"ወደ ነጭ ውሀ እየገባን ነው , መንገድ ስተናል በጣም ሀይለኛ ንፋስ አለ።" ብሎ የዚም ተቋርጧል።

🌪ሰባተኛው ጥሪ

"ነገሮች እየተቀያየሩ ነው አቅጣጫ ጠቋሚው ኮምፓስ በፍጥነት ይሽከረከራል። እንደዚ ሆኖ አይቼው አላቅም። ሞተሩም ፣ electric system ሁሉም ነገር ቀጥ ብሏል። ሰማዩና ውቅያንሱ የተላጠፉ ይመስላሉ። ሰማዩ እና ውቅያንሱ የት እንደሚጀምሩ እና እንደሚያቁ አይታወቅም። ውቅያንስም ሆነ ሰማይ የሌለ አይነት ነገር ሆኖ ነው ሚታየው። ወደ ታች ስመለከት ወተት የመሰለ ጭጋግ ነገር ነው ሚታየኝ። መርከቡ በሁለት አቅጣጫ ሲጎተት አይነት እየተሰማን ነው።

🌪ከላይ የዘረዘርንላቹ የአውሮፕላን ፓይለቶች እና የመርከብ ካፒቴኖች የመጨረሻ ቃላቸው ነው። ከ Record ክፍል የተገኙ ናቸው። በዚ ቤርሙዳ አካባቢ ቁጥር ስፍር የሌላቸው መርከቦች እና ፓይለቶች ገብተው ተሰውረዋል። ሌላው ሳይቀር ተከስክሰው ነው ተብሎ እንኳን ቢታሰብ ስብርባሪያቸው እንኳን አይገኝም። ሳይንቲስቶች በዚህ አካባቢ ሚያልፉትን መርከቦች እና አውሮፕላኖች time traveler እያረጋቸው ነው ሚሰወሩት ይላሉ።

⛈ነገሩን አስደንጋጭ ሚያደርገው ቤርሙዳ ትሪያንግል ገብተው ያመለጡ ሰዎች ምን እንዳጋጠማቸው እና ምን እንዳዩ ተጠይቀው ምንም አናውቅም ማለታቸው ነው። አንዳንድ ያመለጡት ሰዎች ግን አሁን ላይ ትንሽ እየተናገሩ ነው። አንድ አውሮፕላን አብራሪ ከቤርሙዳ ገብቶ የተረፈ ደሞ የተናገረው " ምንም ነገር አይታየኝም ነበር። እጅግ ከፍተኛ ሚንቦገቦግ ብርሀን ነበር። ሁሉም ነገር ነጭ ሆኖ ነበር ሚታየኝ, ሞተሩም ሁሉም ነገር ለአምስት ደቂቃ ቀጥ ብሎ ነበር። ከዛ በሗላ ግን ወደ ቀድሞ ተመለስኩ እና በፍጥነት ከዚህ አካባቢ እያበረርኩ ወጣው" ብሏል።

🌪ሳይንቲስቶች እስካሁን የቤርሙዳ ሚስጥር ምን እንደሆነ ሊገባቸው አልቻለም። በተለይ ከላይ እንደፃፍነው አምስተኛው ጥሪ ላይ አንዱ ፓይለት እንዳለው "እኔን ተከትላቹ አትምጡ ከሌላ አለም የመጡ ይመስላሉ" ያለው, ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ይሄ አብራሪ በዛ ሰአት በእርግጠኝነት Aliens ወይም ባእድ ፍጡራን እየተከተሉት እንደነበር እና አግተው ወስደውትም እንደሆነ ደምድመዋል። እና እኛ የሰው ልጆች ከእነዚህ ባእድ ፍጡራን በእጅጉ በ technology ወደ ሗላ የቀረን እንደሆንን ይናገራሉ። እና ሳይንቲስቶች እንደሚሉት እነዚ Aliens ከኛ ከሰው ልጆች በ technology በብዙ እጥፍ የተራቀቁ እንደሉ።

©Mira Zh

ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


ከኛዋ መሬት ጋር የሚመሳለው ፕላኔት ወይም "kepler-22b"  ብለነ እንጠረዋለን

ይሄ ኤክሶ ፕላኔት ወይም በእንግልዘኛው "exoplanet" ወይም "extrasolar
planet" የሚባል አይነት ሲሆን
ይሄ ፕላኔት የሚዞረው ኮከብ "kepler-22" የሚባል ሲሆን ከኛዋ ኮከብ ፀሐይ እጅጉን ይመሳሰላል የኛ ፕላኔት ከኛ ፀሐይ 150ሚልዬን ኪሎ ሜትር የምትርቅ ሲሆን ይሄም እርቀተ ሕይወት ላላቸው ነገሮች ምቹ ያደርጋታል ይሄም "kepler-22b" የተሰኘ ፕላኔት ከራሱ ኮከበ(ፀሐይ) የሚርቀው ልክ እንደኛ ፕላኔት ነው ወይም ተመሳሳይ ነው ይሄም ሕይወት ያላቸው ነገሮች የሚኖሩበተ አከባቢ ነው ወይም በእንግልዘኛው "habitabel zone" ብለን የምንጠራው አከባቢ ነው

ይሄ ፕላኔት የተገኘው በ2011 ሲሆን "habitable zone" የሚባለው አከባቢ የተገኘ የመጀመሪያው ፕላኔት ነው
ውሃ በዚህ ፕላኔት የመገኘት እድሉ ሰፊ ነው ውሃ ደግሞ ሕይወት ላላቸው ነገሮች መሰረታዊ ነገረ ነው እናም ይሄ አለም ለሰው ልጆች ኦነ ለሌሎች ፍጡሮች ጥሩ መኖሪያ መሆን ይችላል

"kepler-22b" የተሰኘው ፕላኔት ከኛ ምድር የሚርቀው 600 የብርሃን አመተ ነው ወደዚህ ፕላኔት ለመሄድ አውን ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን "New Horizons" የሚባለውን እስፔስክራፍት ብንጠቀም እንኳን 26 ሚልዬን አመተ ያስፈልገናል ይሄ እስፔስ ክራፍት የሚጓዘው በሰሀተ 59,000km እንደሆነ ይታወቃል

ይሄ ፕላኔት ከኛ ፕላኔት የሚበልጥ ሲሆን የራሱን ኮከብ ዙሮ ለመጨረሰ 290 ቀን ይፈጅበታል አስተውሉ የኛ ምድር የኛን ፀሐይ ዙራ ለመጨረስ 365 ቀነ ነው የሚፈጅባት ይሄ ብቻ ሳይሆን የኛ ኮከበ(ፀሐይ) እና የፕላኔቱ ኮከብ አንድ አይነተ ወይም በእንግልዘኛው "G-type" ብለን የምንጠራቸው የኮከብ ዝርያዎች ውስጥ ይመደባሉ


የመስታወቱ አለም (the glass world)

በዚህ ግዙፍ ዩንቨረስ ውስጥ ብዙ አስደናቂ ፕላኔቶች ተገኝተዋል ከነዚህ ፕላኔቶች መካከል ደግሞ በመስታወት የተሰራው ፕላኔት ወይም ዓለም አንደኛው ነው ይሄ ፕላኔት ሙሉ ለሙሉ መስተዋት ሲሆን ሳይንቲስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌስኮፕ ሲመለከቱት እጅግ ውብ ነበረ በዋላም በተደረገ ጥናት ፕላኔቱ በኛ አለም ላይ ለአንዳድ ተግባራቶች በሚውለው መስታወት የተሰራ ሁኖ አግኝተውታል።

የፕላኔቱ ስም "HD 189733b" ይባላል እዚህ ዓለም ላይ ያለው ንፍስ የተሰባበሩ ጠርሙሶችን ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅስ ሲሆን ይሄም የተሰባበር መስታወት በዚህ አለም ላይ በሰአት እሰከ 7000km ይጓዛል እዚህ ዓለም ላይ የሚዘንበው ዝናብ ደግሞ ፈሳሽ መስታወት እንደሆነ ይነገራል ይሄ አይነቱ አለም ሕይወት ላላቸው ፍጡሮች ምቹ ነው ተብሎ አይታሰብም።

በቅርቡ ቶፕ አስር አስደናቂ ፕላኔቶች በሚል ቪድዮ ዩቲዩብ ላይ እንለቃለን እስከዛው "Subscribe" 🙏🙏👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

887

obunachilar
Kanal statistikasi