ትናንት ለሰዓታት ኢትዮጵያ የቆዩት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ምን ጉዳዮችን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተወያይተው ሄዱ?
የ አርባ ሰባት አመቱ ማክሮን ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከአይኤም ኤፍ የፀደቀላትን ከሶስት ቢልየን በላይ ዩሮ ብድር ወደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገብቶ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ መንግስታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ማክሮን ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የተፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እና ሀገራቸው በግጭቱ የተጎዱትን ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት እና በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት በሽግግር የፍትህ ሂደት እንዲከበር ፈረንሳይ ትፈልጋለች ብለዋል።
ማክሮን ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የዲፕሊማሲም ሆነ የኢኮኖሚ ግንኙነቶችን አጠናክራ እንደምትቀጥል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልፀዋል።
ማክሮን በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በ25 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ የታደሰውን የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ቤት የነበረውን እና የታደሰውን ብሄራዊ ቤተ መንግስት ጎብኝተዋል። ይሄን ቦታ የኢትዮጵያ መንግስት ሙዚየም አድርጎ ለህዝብ ክፍት ለማድረግ ማቀዱ ይታወሳል።