#ተቋሙ_ሐሰተኛ_የትምህርት_ማስረጃን_ለማጥራት_ከባለድርሻ_አካላት_ጋር_በቅንጅት_እየሠራ_ነው
====== ====== ====
ታደሰ ብናልፈው
አዲስ አበባ፡- በፌዴራልና በክልል የመንግሥት ተቋማት በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው የሚሠሩ ግለሰቦችን ለማጥራት በትብብር እየተሠራ መሆኑን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።
የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ማርታ አድማስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት በሚሠራው መጠነ ሰፊ ሥራ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠሩ ነው።
የፌዴራልና የክልል ተቋማት አዲስ የሰው ኃይል ቅጥር ሲፈፅሙ እና የደረጃ ዕድገት ሲሠጡ የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ መሆንና አለመሆኑ እንዲጣራላቸው ወደ ተቋሙ መላካቸው አብረው የመሥራት ቁርጠኝነታቸውን ያሳያል ብለዋል።
እንደማሳያም የደበብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከክልል እስከ ወረዳ ያለው የመንግሥት መዋቅር ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማጋለጥና በማጥራት ሂደት ቀዳሚ እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ተቋማት ከትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን ጋር በቅርበት እየሠሩ መሆኑን ወይዘሪት ማርታ ተናግረዋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ማምጣታቸውንና መረጃ ተቀብሎ የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የ12ኛ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለከፍተኛ የመንግሥት ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው እንዲሠለጥኑ የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው የግል ተቋማት መግቢያ ነጥብ መኖሩን አውስተው ተማሪዎች የግል የትምህርት ተቋማትን ሲቀላቀሉ የፌደራል የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን ነጥብ አሟልተው መግባታቸውን ለማጥራት የተማሪዎችን ሰነድ እየፈተሹ እንደሆነ አብራርተዋል።

አያይዘውም መስፈርቱን ሳያሟሉ በተገኙ ተማሪዎች እና ከተፈቀደላቸው የማስተማር፣ የፕሮግራም እና የቁጥር ፍቃድ ውጭ እየተቀበሉ በሚያሠለጥኑ የግል ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የግል ተቋማት በአንድ የሙያ ዘርፍ ከተፈቀደላቸው የተማሪ ቁጥር በላይ አልፈው ሲያሰለጥኑ ከተገኙ ተማሪዎች ብቻ መቀጣታቸው ቀርቶ ተቋማትንም ለመቅጣት ከፍትሕ አካላትና ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ጋር ለመሥራት መታቀዱን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ተቋሙ የማስተማር ፍቃድ እና የሚሰጣቸው የፕሮግራም ፍቃድ የማጣራት ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ለኅብረተሰቡም ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንዲኖረው ማንኛውንም የሚዲያ አውታር በመጠቀም ግንዛቤ እንዳስጨበጠና በማስጨበጥ ላይ እንደሆነ የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተናግረዋል።
ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት የፌዴራል መንግሥት በተለያየ ዘርፍ ከባለሥልጣኑ ጋር እየሠራ መሆኑን እና ወደፊትም በቁርጠኝት ለመሥራት ጥናት እየተደረገ እንደሆን ጠቁመው ትውልድ ገዳይ የሆነውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለማጥራት መንግሥት፣ ኅብረተሰቡ እና ሚዲያዎች በማጋለጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።