ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።
ከብድሩ 90 በመቶው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጿል።
ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።
ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው።
የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደሆነም ባንኩ ባሰራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።