ሽረተ ፅልማሞት (ክፍል ሁለት)
╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩╩
ከህይወት ዘመን ታሪኮቼ ሁሉ ለልጄ የማወርሰው ታላቁ የህይወቴ ማስታወሻ የሆነው ይህ ታሪኬ ተፈጥሮኣዊው ማንነቴን የተቀበልኩበት የዚህ ክረምት ገጠመኜ ነው፤ ለልጄም ብቻ ሳይሆን ለወገኖቼም ጭምር! 2008 ዓ.ም ክረምት!
በሲሳይ ዘለቀ
‹ከማነው የወሰደው?› በማለት አንደኛው ፖሊስ ጠየቀኝ፤
‹ከኔ ነው፤ከኔ› ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ
‹ሞባይል ብቻ ነው የወሰደብሽ? ወይስ ሌላም ነገር አለ?› ሁለተኛው ፖሊስ ጠየቀ፤
‹አዎ ሞባይል ብቻ ነው...›
‹በቃ ጣብያ እንሂድና ቃልሽን ስጪ›
ብዙ ሰዎች ከበውኝ ነበር ለካ ድንጋጤዬ ለቆኝ ከመሃላቸው ስወጣ ነው የታወቀኝ፤ አንዳንዶቹ አይዞሽ ተረጋጊ እያሉ ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፤ ዳር ላይ ቆመው የተፈጠረውን ነገር ሁሉ በአርምሞ ይመለከቱ የነበሩ አንድ ልብሰ-አካላቸው የተጎሳቆሉ ደካማ አዛውንት ግን ጠጋ አሉኝና በደከመ ድምፃቸው ‹ልጄ! ልጄ ግዴለም እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያለምክንያት አይከውንም፤ ሁሉም ነገር ለበጎ ነውና ተዪው! አዎ እርግፍ አርገሽ ተዪው! አንቺም በሰላም እንደወጣሽ በሰላም ግቢ፤ ከአካልሽ የቆረሰው፣ ከልቦናሽ የሰወረው አንዳች የለም፤ ኋላስ ቢሆን ሰው ሰርቶ የሰጠሽን ሰው ወሰደው እንጂ...› ብለው ከመጨረሳቸው በፊት ‹ምን ሆነዋል እርስዎ ደግሞ! ለበጎ ነው ይሉኛል እንዴ? እስከዚህም ነጥቆኝ እንጂ ሰጥቶኝ እኮ አልሄደም!› አልኳቸው በቁጣ፤ ‹ተይ እንጂ አንቺ አባትሽ ይሆናሉ እኮ...› አንዷ ሴትዮ ቀጠለች፤ ፖሊሶቹም ‹ነይ በቃ እንሂድ› ሲሉ የታክሲ አስከባሪውም ‹በቃ ተበተኑ! ተበተኑ! ዳይ ሼባው በቃ ላሽ በል፤ ምክርህ አይነፋም› ሲል ጥቂቶቹ እየተሳሳቁ ሄዱ፤ የአዛውንቱ ሰውዬ አይን ግን እስከተወሰነ መንገድ በስስት ሲከተለኝ እመለከት ነበር፤ ነገር ግን ለምን እንደሚመለከቱኝ ፈፅሞ አልገባኝም፣ እኔም ቦታ ሳልሰጣቸው ከፖሊሶቹ ጋር ወደ ጣብያ ተጓዝን፡፡
ከፖሊሶቹ ጋር ተያይዘን እዛው አካባቢ ካለ ጣብያ ገብተን ቃሌን እና የእቴቴን ስልክ ሰጥቼ ወጣው፤ ቀኑ መሽቷል፤ ሰዓት ስጠይቅ 12፡25 ሆኗል፤ ከዚህ በኋላ ቤቲ ጋር መሄድ አልችልም ምክንያቱም አቃቂ ነው የምገባው፤ ስልክ እንዳልደውልላት ስልኳን በቃሌ አላውቀውም፤ ስለዚህ ቀጥታ ወደለገሃር ጫፍ ተጉዤ የቃሊቲን ታክሲ ለመሳፈር ወሰንኩ፡፡
ቤት እንደገባው ከፍተኛ እልህና ንዴት ተናንቆኝ ነበር፤ ከምንም ነገር በላይ እነዛ ሁሉ ስልክ ቁጥሮች፤ መልዕክቶች፤ ሁሉም ገደል ገቡ በቃ! በጣት ከሚቆጠሩ ጓደኞቼ ውጪ የማንንም ስልክ በቃሌ አላውቅም! እቴቴ ክፍሌ ድረስ መጥታ ‹ምን ሆነሻል ዛሬ ለምንድነው እራት የማትበዪው?› አለችኝ፤ ‹ተዪኝ ባክሽ እቴቴ እናንተ ብሉ እኔ ማረፍ እፈልጋለው› ብያት በሬን ዘግቼ ተኛሁ፡፡
እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም፤ ተነስቼ የእናቴን ስልክ አምጥቼ ወደስልኬ ደወልኩ ‹የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም...› ስልኩን መለስኩትና ወደ አልጋዬ ተመለስኩ፤ እቴቴ የገዛችልኝን የግል ማስታወሻዬን አውጥቼ የገጠመኝን ልፅፍ አሰብኩና በእንደዚህ አይነት መጥፎ አጋጣሚ የሚጀምር ፅሁፍ አዲሱ የግል ማስታወሻዬ ላይ መፃፌ ስላልተዋጠልኝ ተውኩትና መልሼ ጋደም አልኩ፤ ደክሞኝ ስለነበር መብራት አጥፍቼ ለመተኛት ሞከርኩ፡፡
ከነበርኩበት ክፍል ወጥቼ በሬ ላይ ቆምኩ፤ ጨለማ በመሆኑ የተነሳ ምንም የሚታይ ነገር የለም፤ ለጥቂት ደቂቃ በተመስጦ አካባቢዬን ስመለከት ቆይቼ ፊት ለፊት በርቀት ላይ በትንሹ የምታበራ አነስተኛ ነገር ተመለከትኩ፤ ከዛ ሁሉ ድቅድቅ ጨለማ ይህች የብርሃን ቅንጣት ጎልታ ታየችኝ፤ ልቦናዬን አሰባስቤ በትኩረት ስመለከታት ወደኔ ስትቀርብ መጠኗ እየጨመረ መጣ፤ ግን ምን እንደሆነች ለማወቅ ስለጓጓው ከቆምኩበት በረንዳ ላይ ወርጄ ወደ እሷ ቀስ ብዬ መራመድ ጀመርኩ፤ ወደ እርሷ በቀረብኩ ቁጥር እያደገች መጣች፤ ብርሃኗም እየጨመረ ሲመጣ ታየኝ፤ በሂደትም ብርሃኗ አካባቢውን በብርሃን ስለሞላው ያለሁበትን ሰፈር በግልፅ ማየት ቻልኩ፤ መጨረሻው የማይታይ ቀጥ ያለ መንገድ መሃል ቆሜያለው፤ መንገዱም የተሰራው በነጭ የጠጠር ንጣፍ ሲሆን በግራና በቀኝ የተለያዩ ሕብረ ቀለማትን የሚተፋ ጭስ መሳይ አጥር ይታያል፤ ቀና ብዬ ሰማዩን ስመለከት በተለያዩ ቀለማት ስለተዋበ ልቤን ማረከኝ፤ አይኔን ወደምታበራው ነገር ስመልስ ግን ያልጠበኩት ነገር ገጠመኝ፤ አንዲት በግምት እድሜዋ የሰባት አመት ህፃን የሆነች ልጅ ነች፤ የለበሰችው የሀበሻ ቀሚስ በነፋሻው አየር በመጠኑ እየተውለበለበ እንደ እንፋሎት ያለ ብርሃን ይተፋል
( ይቀጥላል...)
ቀጣይ ክፍል
👉 @hanahailu