Ibnu Muhammedzeyn


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ሚዛናውይ እንሁን ሌሎች ሰዎች ባጠፉት ጥፋት ዲንና ባልተቤቶቹ ላይ ጭፍን ጥላቻ አይኑረን

ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ )
እንዲህ ይላሉ:-
«የፂም ባልተቤትን ሲዋሽ ካየህው
የፂም ባለቤትን ሲከዳ ካየህው
የፂም ባልተቤትን ሲሰርቅ ካየህው

ነውሩ ያለው በፂሙ ላይ አይደለም
ይልቁንም ነውሩ ያለው በፂሙ ባለቤት ላይ ነው
ፂምማ ነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ካዘዙባት እና ግዴታ ካደረጓት ሱናዎች ናት"
ምንጭ [ኢጃበቱ ሳኢል ገፅ 222]
_____________________________
እኔም አልኩ
የምትዋሽ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
የምትሰረቅ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ዝሙት የምትሰራ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ነገር ከወዳ ወዲህ የምታመላልስ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ሰው የምታማ ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ሀያእ የቀለላት ኒቃብ ለባሽ ካየህ
ነውሩ ያለው በኒቃቡ ላይ ሳይሆን በኒቃብ ለባሿ ላይ መሆኑን እወቅ።

ኒቃብ ለባሾች በሚያጠፉት ጥፋት ኒቃብ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያደረባቸው ብዙ ሰዎች አሉ
እናንተ ኒቃብ ለባሾች ባጠፉት ጥፋት በኒቃብ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያሳደራችሁ ሰዎች ሆይ!
ኒቃብ ለብሰው ከላይ የዘረዘርኳቸውን እና ሌሎችንም ከለበሱት ኒቃብ እና ጅልባብ ጋር ሊሄድ የማይችል ሀያእ የጎደለው እኩይ ተግባር የሚፈፅሞ ዋልጊዎች እንዳሉ ሁሉ
#ኒቃብ ለብሰው ከሀራም የሚጠነቀቁ
የታዘዙትን በቻሉት መጠን የሚተገብሩ
ሀያእ የተሞሉ በጥቅሉ አላህን የሚፈሩ
የአላህ ባሮችም እንዳሉት አትዘንጉ

እኛ ሰውን ግልፅ ባደረገው ነገር ስለሆነ ልናውቀው የምንችለው ኒቃብ የለበሱ እህቶችን ከተገላለጡት የበለጠ ማክበርም መውደድም ይገባናል
ምናልባች ኒቃብ ለብሳ እኩይ ተግባር ስትሰራ ካየናት ኒቃቡን አልያም ኒቃብ ለባሾችን ሳይሆን በጅምላ መወረፍም ይሁን መጥላት ያለበን ያችኑ ኒቃብ ለብሳ እኩይ ተግባር ስሰራ ያየናትን መሆን አለበት።
___________________________

በጥቅሎ በዲን ዙሪ በሸሪአ በዟሂር
እንዲተገበሩ የታዘዝነውን ነገር የሚተገብር ሰው የተለያዩ ሀራሞችን ሲፈፅም ካየነው ማውገዝም ሆነ መጥላት ያለብን ያንኑ ሀራም የሰራውን ሰው ብቻ መሆን አለበት።
የጅምላ ጭፍጨፋ አይጥ ባጠፋ ዳዋ ይመታ ነገር አካሄድ ፍትህም አይደለም
ከዚህም አልፎ የአለማቱን ጌታ ቁጣ ሊያመጣብን ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልገናል።
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn
✍ ኢብኑ ሙሀመድዘይን


አላህን የሚፈሩ ሰዎች ለምን ይሆን ከአንድ በላይ ማግባትን የሚወዱት???

ኢማሙል ቁርጡቢ (ረሂመሁላሁ ተአላ) እንዲህ ይላሉ "አላህን የሚፈራ ሁሉ (አላህን ከማይፈራ ሰው የሴት) ስሜቱ የበረታ ነው። ምክኒያቱም ያ አላህን የማይፈራው (ስሜቱን) በማየት እና በእጁ(ሴቱችን) በማሸት ያወጣል የነብዩን(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) [ሁለት አይኖች ዝሙት ይሰራሉ ሁለት እጆች ዝሙት ይሰራሉ] የሚለውን ሀዲስ አታይምን? (አታስታውልምን?)
በማየት እና በእጅ በመንካት ምክኒያት ስሚት የሚቅንሰ ከሆነ የሰውየ ከሚስቱ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ቀላል ይሆናል ማለት ነው።
ያስ አላህን የሚፈራው ያልተፈቀደችለትን ሴት የማያየው እና የማይነካው ስሜቱ በነፍሱ ውስጥ የተሰባሰበ(የታመቀ) ይሆናል። በዚህም ምክኒያት ስሜቱ(ከሚስቱ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ጅማእ) ብዙ እና የበረታ ይሆናል ተብሏል" [ ተፍሲር ቁርጡቢ ]
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn
✍ ኢብኑ ሙሀመድዘይን


ሶላት ለምንድን ነው ከንቅልፍ የሚበልጠው?

መልስ!!!

እንቅልፍ ሞት ነው
ሶላት ደግሞ ህይወት ስለሆነ
ስለዚህ ሶላት ከንቅልፍ
ይበልጣል

እንቅልፍ ለነፍስያ መታዘዝ ሲሆን
ሶላት ደግሞ ለአላህ መታዘዝ ስለሆነ
ስለዚህ ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል!!!

እንቅልፍ አካላውይ ረፍት ሲሆን
ሶላት ደግሞ ሩሀውይ(መንፈሳውይ) ረፍት ነው።
ስለዚህ ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል!!!

ሙእሚንም ይሆን ካፊር በእንቅልፍ ይጋራሉ
ሶላትን ግን ሙእሚን እንጅ አይሰግዳትም
ስለዚህ ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል!!!

የፈጅርን ሶላት ምን ያማረች አደረጋት
ግዴታዋ በአላህ ዚማ ላይ ታደርጋሀለች
ሱናዋ ደግሞ ከዱኒያ እና በውስጧ ካለው ይበልጣል።

አላህ የሱቢሂ ሶላትን ያግራልን
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn
✍ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን


Ibnu Muhammedzeyn:
አብዱላህ ኢብኑ መስኡድ ረሱልን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)
"ከሰው ልጆች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በሂይወት እያሉ ቂያማ የምታገኛቸው እና መቃብርን መስጅድ አድርገው የሚይዙ ናቸው" ሲሎ ሰምቻቸዋለሁ ይላል
ኢብኑ ኹዘይማህ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn


ትክክል በሆንኩ ጊዜ ከሚያሞግሱኝ ይልቅ በተሳሳትኩ ጊዜ በቅንነት የሚያርሙኝ ለኔ የበለጠ ጠቃሚ ወዳጆቼ ናቸው።
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn


እውነተኛ ጓደኛህ ማለት

👉 ስታየው አላህን የምታስታውስበት

👉 አብረህው ስትሆን የሚመክርህ
አልያም በመልካም ስትመክረው የሚቀበልህ።

👉 ከሱ ስትርቅ በመልካም ዱአ የሚያደርግልህ እና በመልካም የሚያወሳህ

👉 ሚስጥርህን የሚደብቅልህ እና ሚስጥሩን የሚያካፍልህ

👉 ስታደምጠው እውቀትን የሚጨምርልህ።

👉 በገፅታው ወደሱና የሚመራህ

👌 በጥቅሉ ከሱጋር ስትሆን ኢማን እና እውቀትን የሚጨምርልህ ነው ።
https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn


ዚህ ተቃራኒ ሱንዩንም ሙብተዲኡንም በአንድ አይን የሚያዩ ከዚህም አልፈው አይሁድ እና ነሷራዎችን እንኳ ሳይቀር ወንድሞቻችን ናቸው የሚሉ አሉ። ከነዚህም ውስጥ በዘመናችን ኢኽዋኖች ይገኙበታል።

ሌሎችም ወላእ ወልበራአቸው ለአላህ ሳይሆን ለሚከተሉት ቡድን እና ኢማም ነው የሚያደርጉት። የነሱን አካሄድ የሚወድን አስተምሮታቸውን የሚከተልን ለምን የቢዳአ አይነቶችን እና የሀራም አይነቶችን አይፈፅምም ይወዱታል ።
በተቃራኒው የእነሱን አስተምሮት የማይከተል የሚነቅፋቸው ከዚህም አልፎ በጥፋታቸው ላይ በመረጃ መልስ የሚሰጥ ከሆነ ለምን ሱንይ አሊም ለዲኑ ብዙ ነገሮችን ያበረከተ የዲን ኻዳም አይሆንም ካፊርን እና ሙብተዲእን ከሚጠሉት በላይ ይጠሉታል! ክብሩን በሚነኩ ዘለፋዎች ይሰድቡታል! ከዚህም አልፎ የዲን ጠላት አድርገው ለአላዋቂው ማሀበረሰብ ይስሉታል! አልፈውም ከዲን እስከሚያስወጡት ይደርሳሉ።
ወደታችም ይርገብም ወደላይም ይወጥር ሁለቱም ፅንፈኝነት ነው።
ከአህሉሱና አካሄድ አይደለም።

አህሉሱናዎች በሁሉም አቂዳቸው መካከለኛ እንደሆኑት ሁሉ በዚህም ርእስ ላይ ከሁለቱ ፅንፈኛዎች አቋም መካከል ላይ ይገኛሉ።

አህሉሱና ወልጀማአዎች ዘንድ ወላእ ወልበረእ ለሶስት ይከፈላል።

ሶስቱ ክፍሎች እና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በአላህ ፍቃድ በክፍል ሁለት ላይ ይቀጥላሉ…

ሌሎች ፅሁፎችን ለማገኘት እሄን ሊንክ ጆይን ይበሉ

https://telegram.me/IbnuMuhammedzeyn

✍ ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን [ሸእባን 30 1439ሂ]


በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ ፍፁም አዛኝ በኾነው።

عقيدة الولاء والبراء
ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት

ክፍል 1

በቅድሚያ ወላእ ወልበራእ ቋንቋውይ እና ሸሪአውይ ፍቹ(ትርጉሙ) ምንድን ነው?

"ወላእ" ማለት በቋንቋ "መውደድ መቅረብ መርዳት" ማለት ነው። [ሙእጀሙል ወሲጥ]
"ወላእ" በሸሪአውይ ፍቹ
"አላህንና መልእክተኛውን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲሁም ዲነል ኢስላምንና ተከታዮቹን ሙስሊችን መወደድ እና አላህንና መልእክተኛውን እንዲሁም የእስልምና ሀይማኖትንና ተከታዮቹን ሙስሊሞቹን መርዳት ማለት ነው"።

"በራዕ" ማለት ቋንቋውይ ፍቹ:-
በራእ በቋንቋ ብዙ ትርጉሞች አሉት። ከነዚያ መሀል አንዱ እና ላለንበት ቦታ የሚገጥመው "መጥራት፣ከጥላቻ እና ከጸብ ጋር መራቅ" ማለት ነው።
"በራዕ"ማለት ሸሪአውይ ፍቹ ደግሞ
"ከአላህ ውጭ የሚመለኩ አማልክቶችን እና ከሀዲዎችን የአላህን ጠላቶች ለአላህ በሎ መጥላት ማለት ነው"

በአሁን ሰአት አላህ ያዘነላቸው ቀላሎች ቢሆኑ እንጅ አቂደተል ወላእ ወል በራእን አያውቁትም። በል እሄን አቂዳ እራሳቸውን ወደ ሱና እንኳ የሚያስጠጉ ሰዎች ሲዘነጉት ይታያል። ነገሩ አምልኩ ነው። አምልኮ ከሆነ ደግሞ እንዳማንኛውም አምልኮ ኢኽላስ እና ኢቲባእ ያስፈልገዋል።

እወቅ ወንድሜ:- ወላእ ወልበራእ ከአህሉሱና ወልጀማአ መሰረቶች(አቂዳዎች) መካከል ነው።
"አህሉሱና ወልጀማአዎች ወላእ ወልበራእ ሸሪአውይ ግዴታ መሆኑን እና ከላኢላሀኢለላህ ሸርጦች(መስፈርቶች) አንዱ መሆኑን ያምናሉ።"[አል-ወጅዝ ገጽ 121]
ለዚችም አቂዳ በኢስላም ትልቅ ቦታ አላት ወደፊት ባሉት የተወሰኖ ነጥቦች ደረጃዋ ግልፅ ይሆናል:-
① የላኢላሀኢለላህ ክፍል ነው። የላኢላሀኢለላህ ማእና ከአላህ ውጭ ከሚመለኩ አማልክቶች መጥራት ነው። አላህም " አለህንም በብቸኝ ነት አምልኩ ፃኦትንም ራቁ" [አን-ነህል አንቀፅ 36] አለ

② ወላእ ወልበራእ የእስልምና ጠንካራው ገመድ ነው
መልእክተኛው (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) "የእስልምና ጠንካራው(አስተማማኙ) ገመድ ለአላህ ብሎ መወዳጀት ለአላህ ብሎ መጣላት ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት ነው።" ብለዋል [ሲልሲለቱል አሃዲሲ ሶሂሃቲ ቁ 998]

③ አቂደተል ወላዕ ወልበራዕ ቀልብን የኢማንን ጥፍጥና ለማቅመስ ሰበብ ነው።
መልእክተኛው (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) "ሶስት ነገሮች በእርሱ ውስጥ (የተገኙ ለት) ሰው የኢማነን ጥፍጥናን አገኘ (እነሱም) እርሱ ዘንድ አላህ እና መልክተኛው ከነሱ ውጭ ካሉ (ሰዎች) በላይ የተወደዱ ሊሆኑ፣አንድን ባሪያ ለአላህ ብሎ እንጅ ላይወድ እና አላህ ከክህደት ካወጣው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን በእሳት ወስጥ መጣልን እንደሚጠላው ሊጠላ ነው።" [ቡኻሪ እና ሙስሊም]

④ እችን አቂዳ(ወላዕ ወልበራዕን) በማሟላት ኢማን ይሟላል ።
የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- "ለአላህ ብሎ የወደደ ለአላህ ብሎ የጠላ ለአላህ ብሎ የሰጠ ለአላህ ብሎ የከለከለ በእርግጥ ኢማንን አሟልቷል"[አቡዳውድ]

⑤ የተውሂድ ሰዎችን መውደድ እና መርዳት
የሽርክ ሰዎችን መጥላት እና ጠላት አድርጎ መያዝ እንድንከተለው የታዘዝ ነው የኢብራሂም (አልይሂ ሰላም) እና ከሱ ጋር ያሉ አማኞች መንገድ ነው።
አላህም ስለዚህ መንገድ በተከበረው ቁራአኑ ሲነግረን እንዲህ ይለናል:- " በኢብራሂም እና ከነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእመናን) መልካም መከተል አለቻችሁ።
ለህዝቦቻቸው "እኛ ከእናንተም ከአላህ ሌላ ከምትገዙትም ንፁሆች ነን። በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛ እና በእናንተ መካከል ጠብ እና ጥላቻ በእርግጥ ተገለፀ።" ባሉ ግዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)።" [አል-ሙምተሂናት አንቀፅ 4]
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አምስት ነጥቦች የወላእ ወልበራእን በኢስላም ያለውን ደረጃ ምን ያህል እንደሆን በግልፅ ያሳያሉ።

አላህ በቁራአኑም ካፊሮችን እንድንጠላ ሙእሚኖችን እንድንወድ በብዙ አንቀፆች ነግሩናል።
ለምሳሌ ያህል የተወሰኑትን ቁራአናውይ ማስረጃ እንመልከት:-
① "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክሪስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ። ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው። ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው። አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናም።" [አል-ማኢዳ አንቀፅ 51]
ይህ የመፃሀፍ ሰዎችን ወዳጅ አድርጎ ስለመያዝ ለይቶ የሚከለክል አንቀፅ ነው።

ባጠቃላይ ከፊሮችን ወዳጅ አድርጎ መያዝ ክልክል እንደሆነ በሌላ ቦታ እንዲህ ሲል ይከለክላል
② "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ዳጅ አድርጋችሁ አትያዙ።" [አል-ሙምተሂናት አንቀፅ 1]
እንደውም ከዚህም አልፎ አላህ (ሱበሀነሁ ወተአላ) ከሀዲዎችን በዝምድና እንኳ ከኛ ጋር ቢተሳሰሩም ወዳጅ አድርገን እንዳንይዛቸው ይከለክለናል።

③ " እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁ እና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው። ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው።" [አት–ተውባህ አንቀፅ 23]

④ [ሱረቱል ሙጃደላህ አንቀፅ 22] ብንመለከትም እሄንኑ ነው የሚያጠናክርልን

ዛሬ ግን በጣም የሚገርመው እነዚህን የቁራአን ማስረጃዎች ችላ በማለት በተቃራኒው "ክሪስቲያን ወንድሞቻችን" የሚሉ ተፈጥረዋል። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አላዋቂዎች ደኢ፣አሊም እና ሙፍቲ ብለው ከሚያስቧቸው ሰዎች መሆኑ ነው።
የዘመኑ ታላቅ አሊም ሸይኽ ፈውዛን(ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
" ይህን ትልቅ መሰረት ከሰዎች ብዙው አያውቀውም እንደውም ወደ ኢልም እና ዳእዋ የሚጠጋ ከፊልን በሪደዎ ስለክርስቲያኖች "እነርሱ ወንድሞቻችን ናቸው" ሲል ሰምቸዋለሁ ምንኛ አደገኛ ንግግር ናት" ምንጭ [አል-ኢርሻድ (2/ 289)]
አላህ ካፊሮችን የተውሂድ ጠላቶችን ወዳጅ አድርገን መያዝን እርም እንዳደረገብን ሁሉ
ሙእሚኖችን መውደድን ግዴታ አድርጎብናል
① "ረዳታችሁ አላህና መልክተኛው እነዚያም ያመኑት ናቸው። (እነርሱም) እነዚያ ሶላትን በደንቡ የሚሰግዱ እነርሱም ያጎነበሱም ኾነው ምጽዋትን የሚሰጡ ናቸው። አላህንና መልክተኛውን እነዚያንም የሚወዳጅ ሰው (ከአላህ ጭፍሮች ይኾናል)። የአላህም ጭፍሮች እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው።" [ማኢዳ 55–56]
② [ሱረቱል ፈትህ አንቀፅ 29] እሄንኑ ነው የሚያጠናክር ማስረጃ ነው።
③ "መእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው።" [ ሁጅራት 10]
④ አማኞች ሀገራቸው፣የኖሩበት ዘመን ብሎም ዘራቸው ቢራራቅም በሀይማኖታቸው በአቂዳቸው ወንድም አማቾች ናቸው።
አምላካችን አላህ በተከበረው ቁራአኑ እንዲህ ይለናል:–
"እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት ‘ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምህረትን አድርግ። በለቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ። ጌታችን ሆይ! አንተ ሩህሩህ አዛኝ ነህና’ ይላሉ።" [ሀሽር 10]

መእሚኖች ዘመናቸውም ሆነ አገራቸው ምንም ያህል ቢራራቅ ወንድም አማች ናቸው ከፊሉ ለከፊሎ ዱአ ይደራረጋሉ ይተሳሰባሉ።

ከላይ ያሳለፍነው ቁራአናውይ እና ሀዲሳውይ ማስረጃዎች ስለ ወላእ እና በራእ በኢስላም ስላለው ደረጃ እና ግዴታ በግልፅ ያሳያሉ።

በወላእ ወልበራእ ዙሪያ ድንበር ያለፉ ሰዎች ይታያሉ። ከፊሎቹ በወላእ ወልበራእ ስም ካፊሩንም ጥፋት ላይ የወደቁ ሙስሊሞችን በእኩል የሚጠሉ ድንበ
ር አላፊዎች አሉ በዘመናችንም ፊርቀቱ ተክፊሮች በዚህ መንገድ ይታወቃሉ።

ሌሎች ደግሞ ከነ


‏نسألُ الله ﷻ أن يتقبل منّا ومنّكم صيامنا وقيامنا وصالح أعمالنا ، وأن يعيد علينا هذه المواسم المباركة أعواماً عديدة ونحن بصحة وعافية وأُلفةٍ وسُنّة وأمن وإيمان


تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል

አላህ ከኛም ከእናንተም ጥሩ ስራችንን ይቀበለን
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

እሄው ውዱ እና የተከበረው ወር ሊያልቅ ትንሽ ግዜ ቀሩት
ለሰራበት ሰው ሀቁንጠብቆ ለፆመው በመልካም ሲመሰክርለት
ግን ሀቁን ጠብቆ ላልፆመው እንዲሁ በመዘንጋት እና በዛዛታ ላሳለፈው ድግሞ ምስክር ይሆንበታል

ሰዎች ሆይ በዚህ በተከበረ ወር ምን እንደሰራችሁ አሰተንትኑ ይህ ወር የተከበረ እንግዳ ነው እሄው ማለቂያው ተቃርቧል እንግዳ ደግሞ አስተናገጁን በጥሩ ታስተናገደው ያመሰግናል ከዚህ በተቃራኒ ከሆነ ግን…

አደራ ረመዷን ከሚወቅሰን እና ከሚታዘበን ሰዎች እንዳንሆን
ከወዲሁ ባለቸው ግዜ እራሳችንን ሂሳብ እናድርግ ግዚያችንን ኸይር በመስራት ከሆነ ያሳለፍነው አላህን እናመስግን ኸይር ስራችንን እንዲቀበለንም እንለምነው የተረፈውንም በምልካም እንጨርሰው
ግን ወሩን በመዘናጋት ከሆነ ያሳለፍነው በተረፈችው ግዜ እንቶብት አላህ የቶበተኞችን ቶበት ይቀበላል

ያለፈው አልፏል በቀረችው ትንሽ ቀን በኸይር ስራ፣በተውበት እና በስቲግፋር እንቻኮል ምናልባት አላህ እስካሆን ለተዘናጋነው ነገር ማካካሻ ሊያደርግልን ይችላል

ይህ የተከበረ ወር ቀኑ በፆም፣በዚክር፣በቁራአን እና በተለያዩ ኸይር ስራ ሌቱ በሶላት ያሸበረቀ እና የተዋበ ነበር
ግን ማንም ነገር አብረህው ብትኖር መለያየት የማይቀር ስለሆነ እሄው ረመዳንም ሊሰናበተን ቆርጦ ተነስቷል

ወዳጆቹ በመሄዱ ምክኒያት ልባቸው በሀዘን ተሞልቷል ጉንጫቸው በእንባርሷል አንገታቸውን ትጋዜው አስደፍቷቸዋል የተከበረ የተላቀ እንግዳ ሊሄድ ቆርጦ ሲነሳ እንዴትስ አይታዘን እንዴትስ አይለቀስ

ይች የተከበረችና ውድ የሆነች ሌት እና ቀን እሄው በጣም ፈጥና ተጓዘች ወይ!ቁጭታችን በዚች ሌት እና ቀን ማለቅ

በዚህች ወር በሰራው ስራ ምክኔያት አላህ የማረው፣ዱኒያ አኼራውን ያስተካከለለት እና ከእሳት ሁር ያለው ብዙ ነው
ያ አላህ ከነዚህ ውብ ባሪያዎችህ በራህመት እዝነትህ አድርገን

አላህ ይጠብቀን እና ከነዚህ የአላህ ባሪያዎች በተቃራኒ ደግሞ ቀኑን በእንቅልፍ ሌቱን በዛዛታ በማላያእኒ ያሳለፉ በፆማቸው ረሀብ እና ውሃ ጥምን ብቻ ያተረፉ ስንቶች ናቸው?
የረመዳን ጣእምነዋን ጭራሽ ሳይቀምሷት ልታልቅ ያለች ባቸው ዝንጎዎች ብዙ ናቸው አላህ ከንደነዚህ አይነቶቹ ይጠብቀን

እንዲህ የሆናችሁት ወንድም እና እህቶች ንቁ በቀረቸው ቀን ጥፋታችሁን አስተካክሉ ወደጌታችሁ ተመለሱ

አላህ የሱን ውዴታ ካገኙት፣ የፆምን ሀቅ ጠብቀው ከፆሞት ከእሳት ሁር ከተባሉት ያድርገ እንድሁም አድሚያችንን አርዝሞለን አሮመዳንን ደግመን ደጋግመን የምናገኘው ያድርገን አሏሁመ አሚን

https://t.me/IbnuMuhammedzeyn
✍ ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን (ረመዳን 29 1439ሂ)


ዘካተል ፊጥር የሚያወጣው ሰው ለድሆች እና ሚስኪኖች እራሱ መስጠቱ ነው።
ታማኝ ሰብሳቢም ካለ ለእነሱም ሰጥቱ እነሱ ለሚገባቸው እንዲያከፋፍሉም ማድረግ ይቻላል።
ለሰብሳቢዎች ከሰጠ ይህ ከሱ ኢንሻአላህ ያብቃቃዋል።
ለምሳሌ በሀገራችን አንዳንድ አከባቤዎች ላይ በስጅድ ግቤ ተስብስቡ እንደሚከፋፈለው ማለት ነው።

10, ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ቦታ
# «ዘካተል ፊጥር በሚወጣበት አከባቢ ላሉ የሀገሩ ተወላጅ ይሁኑም አይሁኑ በሰአቱ ለተገኙት ድሆች ይሰጣል በተለይ ቦታው እንደ መካ እና መዲና ብልጫ ያለው ከሆነ ወይንም በጣም ድሆች የሚበዙበት ከሆነ (እዚያው ሀገር ይሰጣል) ግን በሀገሩ ውስጥ ምንም ደሀ ከሌለ አልያም የሚገባው ከታጣ (በታማኝ ወኪል አማካኝነት) ወደሌላ የሚገባው ሀገር ይላካል» [መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን 146]
*ወሏሁ ተአላ አእለም ወአህከም*

አላህ ፆም እና ኢባዳቸውን ተቀብሏቸው ይቅር ከተባሉት ባሮቹ ያድርገን

ሌሎች ፅሁፎችን ለማንበብ ጆይን ይበሉት
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn

✍ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን (ረማዷን 27 1439ሂ)


*ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች ስለ ሶደቀትል ፊጥር*

በአላህ ስም እጅግ አዛኝ እና ፍፁም ሩህሩህ በሆነው።

ይህ ፅሁፍ ቲንሽ ቢረዝምም በሶደቀተል ፊጥር ዙሪያ ወሳኝ 10 በውስጡ የተለያዩ ፋይዳ የያዙ ነጥቦችን ስለዳሰሰ በትእግስት ያንብቡት ።
ሲጨርሱም የአጅሩ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ለሌሎች ሸር ያድርጉት።
________________________________
አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ በእዝነቱ ለፆመኞች መፅዳጃ ለድሆች ምግብ ይሆን ዘንድ በፆም መጨረሻ ላይ ሶደቀተል ፊጥርን ደንግጎልናል።

1, የሶደቀተል ፊጥር ብይን ምንድን ነው? ሱና ወይንስ ግዴታ
# ሶደቀተል ፊጥር ከሞስሌሞች በወንድም በሴትም በትልቅም በትንሽም በጨዋም በባሪያም ላይ የተደነገገ ግዴታ ነው።
ከኢብኑ ኡመር እና ከሌሎች ሱሀቦች እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ "ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አድርገዋል" [ቡኻሪ እና ሙስሊም]

2,የተደነገገበት ጥበቡ(ሂክማው) ምን ይሆን?
# ሚስኪኖችን ለማስደሰት፤በኢድ ቀን እነሱ እንዳይለምኑ ከሀብታሞች ጋር እኩል በመደሰት ኢድን እንዲያሳልፉ በዚህም ምክኒያት ለሀብታሙም ለደሀውም እኩል የኢድ ቀን እንዲሆን፤እንዲሁም ፆመኛን ከጉድለቱ ከሀጢአቱ ከውድቅ እና ፀያፍ ንግግሩ ለማፅዳት፤አላህ ፆመን በሰላም ስላስጨረሰን የዚህን ታለቅ ኒእማ ሹክር ግልፅ ለማድረግ እና ለሌሎችም ጥበቦች ሶደቀተል ፊጥር ተደነገገችልን
ከኢብኑ አባስ (ረዲየሏሁ አንሁማ) "የአላህ መልእክተኛ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ፆመኛን ከፀያፍ እና ከውድቅ ንግግር መፅዳጃ ለሚስኪኖች ደግሞ ምግብ ይሆን ዘንድ ሶደቀተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ" ማለተቻው ተላልፏል። [አቡ ዳውድ]

3, ዘካተል ፊጥር በማን ላይ ግድ ትሆናለች?
# አንድ ቀን ከነ ለይሉ ከቤተሰቦቹ ጋር የሚመገበው ኑሮት ከዚያ ለሶደቀተል ፊጥር የሚሆን ትርፍ ባለው ሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ ትሆናለች
አንድ ቀን ከነልይሉ ከቤተሰቡ ጋር የሚመገበው ብቻ ከሆነስ ያለው ማለት ከቀለቡ አልፎ ለሶደቀትል ፊጥር የሚሆን ባልተረፈው ሙስሊም ላይ ግዴታ አትሆንበትም።

4, ዘካተል ፊጥር ካማን ትወጣለች?
# አንድ ሰው ከራሱ እና ከሚያስተዳድራቸው ቤተሰቦቹ ሊያወጣ ግድ ይለዋል
ከኢብኑ ኡመር(ረዲየላሁ አንሁማ)
"የአላህ መልእክተኛ ከምትመግቧቸው ከትንሽም፣ከትልቅ እና ከጨዋም፣ከባሪያ ሶደቀተል ፊጥር(እንድታወጡ አዘዙ)።" ማለተቸው ተላልፏል [በይሀቂ]

በተረገዘ ልጅ ሱደቀተልፊጥር ግዴታ አይሆንም ግን በፍላጎቱ ቢያወጣለት ምንም ከልካይ የለም
*ማሳሰቢያ:–* ሶደቀተል ፊጥር የምትወጅበው በረመዳን የመጨረሻ ቀን ፃሀይ ከመግባቷ በፊት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሰው የፆም የመጨረሻው ቀን ፃሀይ ከመጥለቋ በፊት ልጅ ቢወለድለት በዚህ ልጅ ላይ ሶደቀተል ፊጥር ግድ ትሆንበታለች
ግን ልጁ የተወለደው በኢድ የመጀመሪያው ለይል ማለትም የመጨረሻው ቀን የፆም ፃሀይ ተገባች ከሆነ የተወለደው በዚህ ልጅ ላይ ማውጣት ግድ አይሆንም።

5, ዘካተል ፊጥር መቸ ትሰጣለች?
# ዘካተል ፊጥር ሁለት የመሰጫ ግዜዎች አሏት
ሀ, የሚቻልበት
ለ, የሚወደድበት

ሀ, የሚቻለው:- ከኢድ በአንድ ቀን ወይንም በሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት ነው። ከኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁማ "ሱሀቦች ከኢድ በአንድ ቀን እና በሁለት ቀን ቀድመው እንደሚሰጡ ተዘግቧል"[ቡኻሪ]

ለ, የሚወደድበት ግዜ ደግሞ የኢድ ለት ከፈጅር በኋላ ከሶላት በፊት ነው።
የአላህ መልእከትኛ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) "ዘካተል ፊጥር ሰዎች ወደመስገጃ ቦታቸው ሳይወጡ እንድትወጣ አዘዋል" [ቡኻሪ እና ሙስሊም]
አቡ ሰኢድ አል–ኹድርይም "በነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን ከምግብ አንድ ቁና (የኢድ) አል–ፈጥር ቀን እናወጣ ነበር" ብለዋል[ቡኻሪ እና ሙስሊም]
ስለዚህ ከኢድ በአንድ ወይንም በሆለት ቀን መስጠቱ ቢቻልም በላጩ ግን የኢድ ለት ከሶላት በፊት መስጠቱ ነው።
ለዚህም ሲባል የኢደ አል–ፈጥር ቀን ሰዎች ዘካተል ፊጥርን ለማውጣት ሰፊ ግዜ እንዲያገኞ የኢድ ሶላትን ማዘግየት ይወደዳል።

*ማሳሰቢያ:-* ዘካተል ፊጥርን ያለምንም ሸሪአውይ ምክኒያት ከሶላት በኋላ የሰጠ ሰው በእርግጥ ግዴታው አልፎታል እንደማንኛውም ተራ ሶደቃ ነው የሚሆንለት እንጅ ዘካተል ፊጥር አይሆንለትም ለዚህም ሲባል ኢብኑ አባስ እንዲህ ይላሉ:-
"የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለፆመኛ ከፀያፍ እና ከውድቅ ንግግር መፅዳጃ እንድሁም ለድሆች ምግብ ይሆን ዘንድ ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ ከሶላት በፊት የሰጣት እሷ ተቀባይነት ያላት ዘካ ትሆናለች ከሶላት በኋላ የሰጣት እሷ እንደማንኛውም (ተራ) ሶደቃ ትሆናለች።" [ አቡ ዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ]

6, የዘካተል ፊጥር ልክ
ዘካተል ፊጥር ለአንድ ሰው የሚወጣለት በመልእክተኛው ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ቁና(መስፈሪያ) አንድ ቁና (መስፈሪያ) ነው።
ከአቡ ሰኢድ አል–ኹድርይ (ረዲየሏሁ አንሁ) እንደተላለፈው
"በነብዩ(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን ከምግብ አንድ ቁና የ(ኢድ) አል–ፈጥር ቀን እንሰጥ ነበር" ይላሉ። [ቡኻሪ እና ሙስሊም]

ይህማለት አሊሞች የመልእክተኛውን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቁና የሚይዘውን በተለያየ ኪሎ ገምተውታል
ለምሳሌ:- ኢብኑ ኡሰይሚን 2ኪሎ ከ40 ግራም ነው ሲሉ ሌሎች የሱና አሊሞች ደግሞ 3 ኪሎ ነው ብለዋል

7, ዘካተል ፊጥር ከምን አይነት ነገር ነው የሚወጣው
#ለሰው ልጆች ምግብነት ከሚውል ነገር ሁሉ ማውጣት ይችላል
ለምሳሌ:– ተምር፣ገብስ፣ስንዴ፣ሩዝ፣ማሽላ እና ከሌሎችም ሰዎች ለምግብነት ከሚጠቀሟቸው ነገሮች ማውጣት ይቻላል።
በተለይ አብዛሀኛው የአከባቢው ማሀበረሰብ ለምግብነት ከሚያውለው ነገር ቢሆን ይመረጣል።
"የአላህ መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች በጨዋ፣በባሪያ፣በወንድና በሴት ዘካተል ፊጥርን ከተምር ወይንም ከገብስ አንድ ቁና እንዲወጣ ግድ አደርጉ የዛኔ ገብስ ከቀለባቸው ነበር"[ቡኻሪ እና ሙስሊም]
*ማሳሰቢያ:–* ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ፣በአልባሳት እና በተለያዩ ከምግብ ውጭ በሆኑ ነገሮች ማውጣት አይቻልም። ምክኒያቱም መልእክተኛው (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ማውጣት ያለብንን ነገር ለሰው ልጅ ምግብነት የሚውል መሆን እንዳለበት ለይተው ነግረውናል። እኛ ደግሞ ተከታዮች እንጅ አድስን ነገር ፈጣሪዎች መሆን የለብንም!!!
#«ዘካተል ፊጥር የምንሰጠውን ነገር ቂማውን(ግምቱን) ገምተን በገንዘብ መስጠት አይቻልም ይህ መልእክተኛው (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙትን ነገር በኽለፍ ነው» [መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን 143]

8, ዘካተል ፊጥር ለማን ነው የሚሰጠው?
# ዘካተል ፊጥርን ሊሰጡ የሚገባቸው ድሆች እና ሚስኪኖች ናቸው።
ከኢብኑ አባስ(ረዲየላሁ አንሁማ) እንደተላለፈው
"የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለፆመኛ ከፀያፍ እና ከውድቅ ንግግር መፅዳጃ ለሚስኪኖች ምግብ ይሆን ዘንድ ሶደቀተል ፊጥርን ግድ አደረጉ"[አቡ ዳውድ እና ኢብኑ ማጀህ]
በዚህ ሀዲስ ላይ መልእክተኛው (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) «ለሚስኪኖች» በማለት ዘካተል ፊጥርን ገድበውታል ስለዚህ አንዳንዶች እንደሚሉት ዘካተል ፊጥር በስምንቱ የገንዘብ ዘካ ለሚገባቸው መስጠት አይቻለም
የሚቻለው ለድሆች እና ሚስኪኖች ብቻ ነው። ይህም የብዙ አሊሞች ምርጫ ነው። እሄን አቋም ግልፅ ካደረጉ አሊሞች መካከል [ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ፣አል–አላመቱ ኢብኑል ቀይም አል–ሙሀዲስ ሸይኹል አልባኒ አል–ፈቂሁ ኢብኑ ኡሰይሚን እና ሊሎችም ይገኙበታል]

9, ዘካተል ፊጥርን እንዴት ለሚስኪኖች ማድረስ ይቻላል?
# በላጩ


[ከአሊሞች አንደበት ቁ (36)

ኢማሙ ኢብኑ አል-ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
"ሀቅ በሱ ላይ ተቀርቦለት ሳይቀበል የመለሰው ሰው በልቡ፣በአስተያየቱ እና በአቅሉ መበላሸት ይቀጣል" [ሚፍታሁ ዳሪሰአደቲ 1/160] ]
(https://t.me/IbnuMuhammedzeyn)




አል-አላመቱ ኢብኑ ቁዳማህ አት-ተዋቢይነ በሚለው ኪታቡ ከአብዱልዋሂድ ኢብኑ ዘይድ (የሚከተለውን አስገራሚ ታሪክ አስተላልፏል አብረን እንከታተለው)

አብዱልዋሂድ ኢብኑ ዘይድ እንዲህ ይላአሉ:-

"በአንዴት ሰፊና ላይ (እየተጓዝን ነበር) ንፋስ ወደ የብስ ጣለችን (እዚያም) አረፍን
ወዳው ጣኦዎትን የሚያመልክ ሰው አየን እና ወደሱም በማቅናት አንተ ሰው ሆይ ማንን ነው የምታመልከው? ብለን አልነው።

እሱም ወደ ጣኦዎቱ አመላከተን

ይህ የሚመለክ አምላክ አይደለም አልነው

(ታዲያ) እናንተ ማንን ነው የምታመልኩት? (ሲል ጠየቀን)
አላህን ነው የምናመልከው አልነው።

አላህ ማነው? (ሲል ጠየቀን)

(አላህ ብሎ ማለት በዛቱ) ከአርሹ በላይ ስልጣኑ በምድር ላይ በህያው እና በሙታን ላይ ፍርዶ የሆነ ነው አልነው።

በሱ(በአላህ መኖር) እንዴት አወቃችሁ? አለን

ይህ ንጉስ፣ታላቅ እና የተላቀ የሆነው(አላህ) ቸር የሆነን መልእክተኛን ላከልን እና በዚህ(በሱ መኖር) ነገርን አልነው።

መልእክተኛው ምን ሰራ? አለን

መልእክቱን አደረሰ ከዚያም አላህ ገደለው አልነው።

ከናንተ ጋር ምልክት ትቷልን? አለን

(እኛም) አዎ አልነው

እሱም (መልእክተኛው) ምን ትቷል? አለን

(እኛም) ከእኛ ዘንድ ንጉስ ከሆነ(ጌታው የወረደ) ቁራአንን ትቷል አልነው።

ንጉስ የሆነውን(ጌታችሁን) ቁራአን አሳዩኝ የንጉሱች መፃሀፍ ያማረች ልትሆን ይገባታል አለ

ሙስሀፍን(ቁራአንን) አመጣንለት

እሄን በጣም የሚያውቀው ማነው? (ሲል ጠየቀ)

ከቁራአን የሆነን ምእራፍ አነበብንለት (የጀመርነውን የቁራአን) ምእራፍ እስከምን ጨርስ ድረስ እሱ እያለቀሰ እኛም ከመቅራት አልተወገድንም እንቀራለን እሱም ያለቅሳል

ለዚህ የንግግር ባልተቤት ላይታመፅ ይገባል አለ እና ከዚያም ሰለመ የእስልምና ህግጋቶችን እና ከቁራአን ምእራፎችን አስተማርነው ከኛም ጋር በሰፊናይቷ ላይ አሳፈርነው።

በሄድን እና በእኛም ላይ ለይሉ ጨልሞ ሁላችንም የምኝታ ቦታችንን በያዝን ግዜ
እናንተ ሰዎች ሆይ ይሄ ያመላከታችሁኝ ጌታ ለይሉ በጨለመ ግዜ ይተኛልን? አለን

አንተ የአላህ ባሪያ እሱ ሂያው፣ትልቅ እና በራሱ ተቋቋሚ የሆነ ጌታ ነው አይታኛም አልነው።

ምንኛ የጠፋችሁ ባሮች ናችሁ ጌታችሁ ሳይተኛ እናንተ ትተኛላችሁን አለን እና ከዚያም ትቶን አምልኮውን ተየያዘው

ሀገራችን በደረስን ግዜ ለባልደረባየ ብየ አልኩት ይህ ሰው ወደእስልምና አድስ የገባ እና ሀገሩም እሩቅ ነው (አልኩት እና) ዲርሀምን ሰበሰብንለት እና ሰጠነው።

ይህ ምንድን ነው? አለ

ለጉዳይህ የምታጠፋው ይሆንሀል አልነው

ላኢላሀኢለላህ! እኔ በባህር ደሴት ላይ በውስጡ ጣኦዎት ሳመልክ ያላስቸገረኝን አሁን እሱን (አላህን)ካወቅኩት በኋላ ያስቸግረኛልን?! አለ

ከዚያም ለራሱ ስራን መስራት ያዘ ከዚያም በኋላ እስከሞተ ድረስ ትልቅ ሷሊህ ሆነ
ምንጭ [አተዋቢን ሊብኒ ቁዳማህ ገፅ 179]
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn
ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን (ሀምሌ 3 2009)


*በነዚህ አስር ቀናቶች በተለይ ለይለተል ቀድር በሚጠረጠርባቸው ለይሎች ይህን ዱዓ እናብዛ*

"اللَّهم إنَكَ عَفُوٌ تُحِبَ العَفْوَ فَاعْفُ عَنّي".

"اللَّهم إنَكَ عَفُوٌ تُحِبَ العَفْوَ فَاعْفُ عَنّي".

"اللَّهم إنَكَ عَفُوٌ تُحِبَ العَفْوَ فَاعْفُ عَنّي".

👆 አሏሁመ ኢነከ አፉውን ቱሂቡል ዓፍወ ፈዓፉወ ዐኒ

👉 አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ይቅር በለኝ
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn
*በመልካም ዱአችሁ አትርሱኝ*


ከአሊሞች አንደበት ቁ (35)

ሸይኽ ሷሊህ አሉሸይ (ሀፊዘሁሏህ) እንዲህ ይላአሉ:-
"የአላህን ጠላት እና ሸይጧን ከምትዋጋበት ነገር ትልቁ(መሳሪያ) እውቀትን ማሰራጨት ነው። በቻልከው ልክ በየሁሉ ቦታው አሰራጨው።"
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn
[አል ወሷያል ጀልያ (46)]


አይናፋር የሆነች(ሀያእ ያላት) ወጣት

√ ለወላጆቿ ኩራት
√ ለወንድሟ ልቅና
√ ለእህቷ መልካም አርአያ
√ ለባሏ ፀጋ
√ ለልጇ መልካም አስተማሪ
ነች
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn


ከአሊሞች አንደበት ቁ (34)
ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላአሉ:-
"ሶላት በቀልብህ ውስጥ ከብዳ ከታየችህ (ያቺ የከበደችህ ሶላት) ትርፍ እንኳ ብትሆን በቀልብህ ውስጥ ንፍቅና እንዳለ እወቅ
ምክኒያቱም ይህ ያ አላህ "ወደሶላት በቆሙ ግዜ ተሰላችተው ይቆማሉ"(ብሎ የገለፀው) የሙናፊቆች ባህሪ ነው።
ከቀልብህ(ለሶላት) መቅለልን እና መደሰተን ካገኘህ እሄ በኢማንህ ጥንካሬ ላይ አመላካች መሆኑን እወቅ

[ሸርሁ ሶሂሁ ሙስሊም ቅፅ 15]
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

596

obunachilar
Kanal statistikasi