አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ አልተፈቀደምና እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡
‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡
በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው ፡፡ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ስለማናውቅ ለመፍረድ መቸኮል የለብንም።
👍
https://t.me/Islamicmotivati0n