Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ሰለምቴነት ማሸማቀቂያ አይደለም!
~
አንዳንድ ሰዎች በእምነታዊ ጉዳዮች ላይ ስሜታቸውን ለመከተል፣ ከወረዱበት ለመውረድ ፈቃደኛ ያልሆላቸውን ሙስሊም ወደ ኋላ ታሪኩ በማጠንጠን “አንተ ሰለምቴ አይደለህ? ምን ታውቃለህ?” እያሉ ሊያሸማቅቁ ይጥራሉ። የተለየ አውቀው፣ የተሻሉ ሆነው ሳይሆን እንዲሁ የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላላጨበጨበ ብቻ አንድን ሙስሊም በዚህ መልኩ ለማሸማቀቅ መሞከር ጋጠ-ወጥነት ነው።
ሰለምቴነት ክብር እንጂ ነውር አይደለም። ሰለምቴነት ገድል እንጂ ማሸማቀቂያ አይደለም። በዚህ ፈተናው በበዛበት፣ የጥፋት ሃይሎች በሚርመሰመሱበት፣ ኢስላምን የሚያጠለሹ አካላት እንደ አሸን በፈሉበት፣ እጅግ ከባባድ ማደናገሪያዎች ያለ ገደብ በሚለቀቁበት ዘመን በምንም ሰበብ ቢሆን ወደ ኢስላም የሚመጡ ሰዎች ሊከበሩ እንጂ ሊጠለሹ አይገባቸውም። ድክመትም ካለባቸው መሸፈ፞ን እንጂ ማጋለጥ አይገባም። ከቻልን ሞራል እንስጥ። ይህን ማድረግ ካቃተን በማሸማቀቅ ገፍተን እንዳናስወጣቸው እንጠንቀቅ።
ክርስቲያን ወይም አይሁድ የነበረ ሰውኮ ወደ ኢስላም ቢገባ በእጥፍ እንደሚመነዳ ነብዩ ﷺ ተናግረዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] አልኢማም አልቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሐቸው بَابُ فَضْلِ مَنْ أَسْلَمَ مِنْ أَهْلِ الكِتَابَيْنِ የሚል ርእስ እንዳሰፈሩ እናስተውል። ‘ፈድል’ ማለት ልቅና፣ ብልጫ ማለት ነው። ነብያችን ﷺ ለሮማው ንጉስ ሒረቅል በፃፉት ደብዳቤ ላይ ወደ ኢስላም ሲጠሩት ምን ነበር ያሉት?
أَسْلِمْ تَسْلَمْ، يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ
“ስለም። ትድናለህ። አላህ ምንዳህን #ሁለት_ጊዜ ይሰጥሀል።” [ቡኻሪና ሙስሊም] ይሄ መልእክት በሒረቅል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። የኢብኑ ሐጀርን ማብራሪያ ይመልከቱ። [ፈትሑል ባሪ፡ 8/221]
በነገራችን ላይ አንድ ካፊር ወደ ኢስላም ከገባ ከመስለሙ በፊት ሲፈፅማቸው የነበሩ መልካም ስራዎች ይታሰቡለታል። ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ረዲየላሁ ዐንሁ “በዘመነ ጃሂሊያ ስፈፅማቸው ስለነበሩት ዒባዳዎች፤ ሶደቃ፣ ባሪያ ነፃ ማውጣት፣ ዝምድናን መቀጠል በተመለከተ ንገረኝ እስኪ። ምንዳ ይኖራቸዋልን?” ብለው ነብዩን ﷺ ቢጠይቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱላቸዋል፡-
أَسْلَمْتَ عَلَى مَا أَسْلَفْتَ مِنْ خَيْرٍ
“ካሳለፍከው መልካም ስራ ጋር ነው የሰለምከው።” [ሶሒሕ ሙስሊም]
ልብ በል! ሐኪም ኢብኑ ሒዛም ከመካ መኳንንት የነበሩ ሲሆን በድር ላይ ከቁረይሾች ጋር ተሰለፈው ጦርነቱን ተካፍለዋል። አላህ ሲያድላቸው እንደ አጋሪ ጓደኞቻቸው በድር ላይ ሳይገደሉ በመትረፋቸው ኋላ ላይ ሰልመዋል። ለዚህም ነበር “የበድር ቀን ከመገደል ባተረፈኝ ጌታ ይሁንብኝ” እያሉ ይምሉ የነበሩት።
ወንድሜ ሆይ!
1. እስኪ የነ ዑመርንና ሌሎችም በጀነት የተመሰከረላቸውን ሶሐብዮች ታሪክ እናንብብ። ከነዚያ ታላላቅ የኢስላም ፈርጦች ውስጥ ቀድሞ ጣኦት አምላኪ የነበሩትኮ እጅግ በርካታ ናቸው።
2. እስኪ የነ ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም፣ የነብያችን ﷺ ሚስት ሶፍያን ታሪክ እናገላብጥ። ከነዚያ እንቁ ሶሐብዮች ውስጥ ቀድሞ አይሁድ የነበሩት ብዙ ናቸው።
3. እስኪ የነ ሰልማኑል ፋሪሲ፣ ዐዲይ ኢብኑ ሓቲምና መሰል ሶሐቦችን ታሪክ እንፈትሽ። አዎ ከነዚያ ወደር የለሽ የኢስላም ጀግኖች ውስጥ ከመስለማቸው በፊት በክርስትና ውስጥ ያለፉ ነበሩ።
4. ከሶሐቦች ጊዜ ወዲህም ታሪክ የሰሩ፣ ለኢስላምና ለሙስሊሞች በዋጋ የማይተመን ውለታን የዋሉ በርካታ ሰለምቴዎች አልፈዋል።
ልብ በል ወንድሜ! ልብ በይ እህቴ! ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት እንጂ የማንም ግላዊ ንብረት አይደለም። ኢስላም ለሰው፣ ለጂኑ ባጠቃላይ የቀረበ አምላካዊ መድህን እንጂ ያሰኘንን የምናስገባበት፤ የደበረንን የምናስወጣበት ያባታችን ግቢ አይደለም። ኢስላም ልክ ቄሶች “ውጉዝ ከመ አሪዮስ!” ብለው እንደሚያባርሩት ሸይኾችም እንዳሻቸው የሚፈርዱበት ቀልደኛ ቀኖና የለውም። ስለዚህ ወንድሜ! እስልምናን ከአባት ከአያት የወረስከው አንተ፣ በኢስላም ላይ ከሰለምቴው የተለየ የባለቤትነት መብት የለህም። ከአላህ ዘንድ ያለህ ደረጃ ከፍ የሚለው በተቅዋህ ብቻ ነው። ለሰለምቴው ኢስላምን የሰጠው የፈጠረው ጌታ እንጂ እኔ ወይም አንተ አይደለንም። እኛ ይህን የጌታ ፀጋ አከፋፋዮች አይደለንም።
ምናልባት “በሰለመ በማግስቱ ፈትዋ ካልሰጠሁ ብሎ የሚገላገል ሰለምቴስ ዝም ይባል ወይ?” የሚል ሊኖር ይችላል። ይሄ ሌላ ርእስ ነው። እያወራሁ ያለሁት ሰለምቴነትን ለማንቋሸሻነት ስለሚጠቀሙ አካላት ነው። የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላልፈሰሰ ብቻ “እሱኮ ሰለምቴ ነው?” በማለት ለማንጓጠጥ መሞከር ምን ማለት ነው? እስኪ አስቡት! በሚያጋጥሙ አንዳንድ አለመግባባቶች የተነሳ “እሱኮ መስለሙንም እንጃ!”፣ “እሱኮ የሰለመ ጊዜ ቄሶች በደስታ እንኳን ሄደልን ያሉት ነው”፣ “እሱኮ እንደገና ወደ ክርስትና ሳይመለስ አይቀርም”፣ “እሱኮ ሶላት አይሰግድም"፣ "እሱኮ ውዱእ ሲያደርግ ታይቶ አይታወቅም"፣ "እሱኮ ይሰክራል …” ወዘተ በሚሉ እጅግ ሰቅጣጭና ፀያፍ ውንጀላዎች በሃሰት የሚወ፞ነጀል ሰለምቴ ምን እንደሚሰማው አስቡ እስኪ!! በተጨባጭ የተከሰቱ ሃሰተኛ ውንጀላዎችን ነው በምሳሌነት የጠቀስኩት። ተወንጃዮቹ ደካሞች ቢሆኑ ኖሮ በቀላሉ ወደ ኩፍር ተገፍተው ከኢስላም በሸሹ ነበር። ግና ኢስላም ማለት የነዚህ ዋልጌዎች የግል ንብረት እንዳልሆነ ጠንቅቀው ማወቃቸው በጃቸው። ግና ሰዎቹን ከማወቃቸው በፊት ኢስላምን ማወቃቸው ጠቀማቸው። እንጂ እንደዋዛ አኩርፈው በበረገጉ ነበር።
ወላሂ! አንድ ስንት ስራ የሰራ ወንድም ፈፅሞ ይዋሻሉ ብለን በማንገምታቸው ሰዎች በተደጋጋሚ በመወ፞ንጀሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች እስልምናውን እስከሚጠራጠሩት የደረሱበት ሁኔታ በተጨባጭ አውቃለሁ። መነሻው ግን የእነዚያ ታማኞች የመሰሉን ሰዎች ክፋት ነበር።
በተረፈ ሰለምቴ ሆነው ስንቶችን ቁጭ አድርገው እየገሩ ያሉ ኡስታዞች አሉ?! ሰለምቴ ሆነው ለስንቶች መስለም ሰበብ የሆነ ስራ ላይ በሰፊው የዘመቱ አሉ?! ካረገዙ በኋላ በባሎቻቸው ተከድተው ብዙ ፈተና ቢደርስባቸውም ከነ ችግራቸው በኢስላማቸው ላይ እንደፀኑ ያሉ ስንት ሰለምቴዎች አሉ?! ወንድ ወይም ሴት ተከትለው ስንቶች በሚከፍሩበት ዘመን ለኢስላም ሲሉ ከቤተሰብ የተቆራረጡ፣ ትዳራቸውን የበተኑ ስንት ቆራጥ ሰለምቴዎች አሉ?! ነባር ሙስሊሞች በእርዳታ በቆሎ እምነታቸውን በሚቀይሩበት ምድር ለኢስላም ሲሉ ሁለ ነገራቸውን አጥተው ለእለት ጉርስ የተቸገሩ ስንት ፈተና ያልበገራቸው ሰለምቴዎች አሉ?!
ደግሞም አላዋቂ ሰለምቴ እውቀት በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ያላቅሙ ገብቶ ካገኘን ብቃቱ ካለን በአደብ ማስተማር እንጂ ሰለምቴነቱን ለማሸማቀቂያ መጠቀም፣ ሰለምቴነቱን እንደ ነውር በመቁጠር በየደረሱበት ማማት የለየለት ብልግና ነው። መሀይም የሆነ ሰው ሰለምቴም ባይሆን ያላቅሙ እንዲያወራ የተሰጠው የተለየ ስልጣን ወይም መብት የለውም። ስለዚህ ሰለምቴው በተለየ የሚኮነንበት ምክንያት ምንድነው? ሰለምቴ ሆኖ ከብዙዎቻችን የተሻለ ግንዛቤ ያለው ስንት ሰው አለ? ከውልደት እስከ እርጅና እድሜውን ኢስላም ውስጥ አሳልፎ አሊፍ ትቁም ትጋደም የማያውቅ እልፍ አእላፍ ህዝብስ የለም ወይ? እውቀትኮ በመማር እንጂ በውልደት የሚገኝ አይደለም። “ሸንበቆ አስር አመት ውሃ ውስጥ ቢቆይ አዞ አይሆንም” ይባላል። ለውጥ ከአላህ እገዛ ጋር በጥረት እንጂ በምኞትም በጉራም አይገኝም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 01/2012)