በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 704 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7, 334 የላቦራቶሪ ምርመራ 704 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 551 ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 39 ከትግራይ ክልል፣ 30 ከኦሮሚያ ክልል ፣ 26 ከጋምቤላ ክልል ፣ 21 ከአማራ ክልል ፣ 11 ከሲዳማ ክልል ፣ 10 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 5 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ 3 ከአፋር ክልል ፣ 3 ከሶማሌ ክልል ፣ 3 ከሐረሪ ክልል እና ከደቡብ ክልል 2 ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 የደረሰ ሲሆን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 170 ደርሷል፡፡
በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ ዘጠና ስድስት (196) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5,137 ደርሷል።
@EBS_TV1