የኑሮ መክበዱ፤
ሁሉ ነገር መወደዱ፤
እህል ከጎተራ ሲጠፋ፤
ፍሬ ባትሰጥ መሬት ታርሳ፤
ቀና ብሎ ዓይን ሲያይ፤
ደመና የለም በላይ፤
ምድር ከሰማይ ይጠብቃል፤
ሰማይ በምድር ላይ አፍጥጧል፤
ጊዜው ቢመስል የዝምታ፤
አምላኬ ምድርን የረሳ፤
ግን ጨለማው መበርታቱ፤
ሊነጋ ነው ለሊቱ።
አያለው |ሳሙኤል ተ/ሚካኤል
ሁሉ ነገር መወደዱ፤
እህል ከጎተራ ሲጠፋ፤
ፍሬ ባትሰጥ መሬት ታርሳ፤
ቀና ብሎ ዓይን ሲያይ፤
ደመና የለም በላይ፤
ምድር ከሰማይ ይጠብቃል፤
ሰማይ በምድር ላይ አፍጥጧል፤
ጊዜው ቢመስል የዝምታ፤
አምላኬ ምድርን የረሳ፤
ግን ጨለማው መበርታቱ፤
ሊነጋ ነው ለሊቱ።
አያለው |ሳሙኤል ተ/ሚካኤል