እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ።
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
«መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው»
/መዝ. ፹፮፥፩/
ስለ እመቤታችን የትውልድ ሐረግ ከመወለዷ በፊት ነብያት በመንፈስ ቅዱስ በመቃኘት ትንቢት ይናገሩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ያስተምረናል፡፡ ለምሳሌ ያህልም የዝማሬና የትንቢት ጸጋ በእግዚአብሔር የተሰጠው እንደ ልቤ የተባለ ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስቀድሞ ስለ ሥርወልደቷ፣ አምላክን እንደምትወልድ፣ ስለ አማላጅነቷ በመዝሙር ተናግሯል ለምሳሌ በመዝ ፹፮፥፩ ላይ ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን›› መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ በማለት ከቤተክህነት ከቅዱሳን እንደምትወለድ በምሳሌ ገልፆታል፡፡
ልጁም ጠቢቡ ሰሎሞን መኃ.መኃ.4.9 ‹‹እቴ መርዓት ሙሽርዬ ከሊባኖስ ነይ" እያለ የተወለደችበትን ሀገር እንደጠቀሰ መመልከት ይቻላል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ‹‹ትውፅእ በትር እምሥርው እሰይ ወየዐረግ ጽጌ እምኔሃ›› ትርጉሙም ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከርሷ ይወጣል በማለት ተናግሯል ት.ኢሳ ፲፩፩
በሐዲስ ኪዳንም እንደምንመለከተው ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ መጀመሪያ የዘር ሐረጉን በዳዊት ጀምሮ እስከ ማታን ይቆጥራል በአይሁድ ልምድ ሴቶች በዘር ቆጠራ ስለማይቆጠሩ ዘፍራን በያዕቆብ ወገን አድርጎ ቆጠረ በዚህም ከዳዊት ወገን መሆኗን አሳውቋል፡፡
የእመቤታችን ወላጆች በምዕራብያውያኑና በምስራቅያውያኑ ዘንድ ታዋቂ በሆነው በመጽሐፈ ያዕቆብ (መጽሐፈ ልደታ ለማርያም) የእናቷ ስም ሐና የአባቷ ስም ኢያቄም እንደሚባል ጽፏል፡፡ ሐና በዕብራይስጥ "ውብ ተወዳጅ" ማለት ነው፡፡ ኢያቄም በዕብራይስጥ እግዚአብሔር የሠራው ያከናወነው ማለት ነው፡፡ እንዳንድ መናፍቃን ለእመቤታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሳ አንድ ስለመውለዷ የጻፈ የለም ከአፄ ዘርዓያዕቆብ ውጪ ይላሉ፡፡ ግን ከላይ የተመለከትነው መጽሐፍ በጣም ጥንታዊ በዘመን የማይደራረስ መሆንን የታሪክ ድርሰቶች ይናገራሉ፡፡ አፄ ዘርዓያዕቆብ የነበረው በ1399-1468 ባሉት ዓመታት ሲሆን ሐዋርያው ታናሽ ያዕቆብ የጻፈውን መጽሐፍ በ150-215 ዓ.ም ሊቁ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ እና ኦርገን እንደተጠቀሙበት እንመለከታለን ቀደምት አባቶቻችን ግን የሐና ቅድመ አባቶቿ ቴክታና ጴጥሪቃ ሲባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ደግና ቅዱሳን እንደነበሩ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጠጎች ወርቅ ብር የተትረፈረፈላቸው ነበሩ፡፡ ጴጥሪቃ ሀብቱን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ለሚስቱ ይህን ሁሉ ሀብት ምን እናደርገዋለን እንኳን ለእኛ ለልጅ ልጆቻችን ይተርፍ ነበር ግን እኔም አንቺም መካኖች ነን ባላት ጊዜ ቴክታ እግዚአብሔር ከኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይሆነናልና ሌለ አግብተህ ውለድ፡፡ አለችው እሱም ይህን እንኳን ላደርገው እንደማላስበው እግዚአብሔር ያውቃል አላት፡፡ ማታ በህልሟ ቴክታ ነጭ እንቦሳ ከማኅጸኗ ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ሰባተኛዋ ደረሰ ሰባተኛዋ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይታ አድንቃ ለባሏ ነገረችው እሱም በልቡ እያደነቀ ወደ ህልም ፈቺ ጋር ሄደ፡፡ ህልም ፈቺውም ነጫጮቹ እንቦሶች ሰባት ደጋግ ልጆች ይወልዳሉ ሰባተኛዋ ግን በመላዕክት ሁሉ የከበረች ትሆናለች የፀሐይ ነገር ግን አልተገለፀልኝም በማለት ተረጎመላት፡፡ ጴጥሪቃ ሄዶ የህልሙን ፍቺ ነገራት እርሷም የእስራኤል አምላክ የሚያደርገውን እርሱ ያውቃል በማለት ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ በዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች ስሟንም ሔመን አሏት ሔመን ዴርዴን ወለደች ዴርዴም ቶናን ወለደ ቶናም ሲካርን ወለደች ሲካርም ሴትናን ወለደች ሴትናም ሔርሜላን ወለደች ሔርሜላም የተከበረችና የተመረጠች ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ አያት የምትሆን ሐናን ወለደች፡፡ ሐና በመልካም አስተዳደግ አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ከነገደ ይሁዳ ወገን ለሚሆን የአላዛር የልጅ ልጅ ለሚሆን የቅስራ ልጅ ከሚሆን ከኢያቄም ዳሯት፡፡ ሐናና ኢያቄም በእግዚዓብሔር የሚወደዱ ደጋጎች ነበሩ ፡፡ ግን ልጅ አልነበራቸውም! ወደ ቤተ መንግስት በመሔድ እግዚዓብሔርን ደጅ ይጠኑት ነበር አንድ ቀን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከቱ በዚህን ጊዜ ሐና "አቤቱ ጌታዬ ግዑዛን እንስሳ ልጅ የሰጠህ ለኔ ለምን ነሳኸኝ" በማለት ሱባኤ ያዙ ኢያቄም ወደ ምድረ በዳ ሄደ ሐናም በቤቱ አትክልት ስፍራ አካባቢ ሱባኤ ያዘች በሱባኤያቸውም ፍፃሜ ራዕይ ተመለከቱ፡፡
ሐናም ለኢያቄም በህልሜ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ አደረች ብላ ነገረችው ምስጢሩም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን ነጭነቷ ንፅህናዋ፣ ቅድስናዋን የሚገልጽ ነው፡፡ ኢያቄምም የተመለከተውን ራዕይ ነገራት በህልሙ ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወረደ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ብሎ ነገራት፡፡ ምስጢሩም ወፍ የተባለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ነጭነቱ ንጹሐ ባሕሪ መሆኑን ሲያመለክት ነው፡፡ ይህን ራዕይ ሐምሌ ፴ ቀን ተመልክተው ልጅ ብንወልድ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ትሁን ብለው ተሳሉ እመቤታችን በእግዚአብሔር ፈቃድ በብስራተ ገብርኤል ነሐሴ ሰባት እሑድ ቀን ተፀንሳለች፡፡እመቤታችን በማኅፀንም ሆና ብዙ ተአምራትን አድርጋለች፡፡ ሁለቱን ለአብነት ያህል እናያለን፡፡
ሐና በርሴባ የምትባል አንድ ዓይና አክስት ነበረቻት ልትጠይቃት መጥታ ሳለ እግዚአብሔር በቸርነት ጎበኘሽ ብላ ማኅፀኗን በዳሰሰችበት እጇ የጠፋ ዓይኗን ብታሸው በርቶላታል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ ሆዷን እየዳሰሱ ድነዋል፡፡
ሐና የምትወደው ሳምናስ የሚባል የአጎቷ ልጅ ሞቶ በቤተሰብ ልማድ የአልጋውን ሸንኮር ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ሙቱ አፈፍ ብሎ ተነስቶ ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የአምላክ አያቱ ሐና ሰላም ላንቺ ይሁን ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡
በእናቷ ማኅጸን ሳለችም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአዳም ጅምሮ በዘሩ ሁሉ ሲተላለፍ የነበረው ጥንት አብሶ እመቤታችንን እንዳይነካት ከእናቷ ማኅጸን ጀምሮ ጠብቋታል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች፡፡በሊባኖስ መወለዷም ሰሎሞን ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ መኃ.መኃ ዘሰሎሞን 4.9 ያለው ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ቤተ-ክርስቲያናችንም "ልደተ ለማርያም" በማለት በዓሉን በቅዳሴ፣ በማህሌት በታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ታከብረዋለች፡፡ ሐናና ኢያቄም እግዚአብሔር በሰጣቸው ልጅ ተደስተው በተወለደች በ8 ቀኗ ማርያም ብለው ስም አወጡላት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን፡፡ሀገራችንን ትጠብቅልን በዓለም ላይ የመጣውን መቅሰፍት ትመልስልን፡፡ዳግመኛ ተሰባስበን በዓሏን ለማክበር ያብቃን አሜን
@Orthodoxess
@orthodoxess