ምን ነካሽ እህቴ ??
በሱሪ በጉርዱ በጣም ተወጣጥረሽ
ደግሞ ከዛ በላይ ኮስሞቲክስ ጨማምረሽ
ስልጣኔ መስሎሽ ሽቶውን ጨምረሽ
አላማሽ ምንድነው? እህቴ ምን ነካሽ?
ለምክር አይበቃም አውቃለሁ እውቀቴ
ግን ትንሽ ልበልሽ አድምጪኝ እህቴ!
የእስልምና ህግ ማወቅን ከፈለግሽ
እንዲህ እኮ አይደለም እህቴ ምን ነካሽ?
ጭራሽ በአደባባይ እንደዚህ ተውበሽ
ከወንዶችም ጋራ እኩል ተሰልፈሽ
እርቃንሽን ሆነሽ ለብሰሽ እንዳለበስሽ
የስንት ወንድሞችን ልብ አሸፍተሽ
እንዳሻሽ ልትሆኚ አንች እንደተመቸሽ
ሸሪዐ አይፈቅደውም እህቴ ምን ነካሽ
ስሚኝማ እህቴ...
እንደዚህ አይደለም ሸሪዐ የሚያዘን
ጌታን እያመፅን ጥፋት እያስፋፋን
የእስካሁኑ ይብቃ አይብዛ ጥፋትሽ
ቀጥ ብለሽ ተጓዥ እስልምና ይግባሽ
በሰለፎች መንገድ እህቴ አስተውለሽ
ይግባሽ ተአለሚ ይኑርሽ እውቀቱ
የሰሀቦች መንገድ እሱ ነው እውነቱ
በቁርዐን በሀዲስ ብቻ የሚመሩ
በዲን የሚብቃቁ ምንም ማይጨምሩ
የአላህን ትዕዛዝ ብቻ የሚያከብሩ
ስድብና ዛቻ የማይበግራቸው
የአላህ ወዳጆች እነሱ እኮ ናቸው፡፡
እናማ እህቴ
የነሱን ፈለግ አንችም ተከትለሽ
በተውሂድ በሱና በኢማን አጊጠሽ
በሀያዕ ተሞልተሽ በሂጃብ ተውበሽ
ፍካትሽ ድምቀትሽ ለባልሽ ብቻ አድርገሽ
ለአባትም ኩራት ለወንድም ጌጥ ሆነሽ
ያኔ እስልምናን ከፍ ታደርጊያለሽ!!!
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇
@RehimWAschannal
@RehimWAschannal
በሱሪ በጉርዱ በጣም ተወጣጥረሽ
ደግሞ ከዛ በላይ ኮስሞቲክስ ጨማምረሽ
ስልጣኔ መስሎሽ ሽቶውን ጨምረሽ
አላማሽ ምንድነው? እህቴ ምን ነካሽ?
ለምክር አይበቃም አውቃለሁ እውቀቴ
ግን ትንሽ ልበልሽ አድምጪኝ እህቴ!
የእስልምና ህግ ማወቅን ከፈለግሽ
እንዲህ እኮ አይደለም እህቴ ምን ነካሽ?
ጭራሽ በአደባባይ እንደዚህ ተውበሽ
ከወንዶችም ጋራ እኩል ተሰልፈሽ
እርቃንሽን ሆነሽ ለብሰሽ እንዳለበስሽ
የስንት ወንድሞችን ልብ አሸፍተሽ
እንዳሻሽ ልትሆኚ አንች እንደተመቸሽ
ሸሪዐ አይፈቅደውም እህቴ ምን ነካሽ
ስሚኝማ እህቴ...
እንደዚህ አይደለም ሸሪዐ የሚያዘን
ጌታን እያመፅን ጥፋት እያስፋፋን
የእስካሁኑ ይብቃ አይብዛ ጥፋትሽ
ቀጥ ብለሽ ተጓዥ እስልምና ይግባሽ
በሰለፎች መንገድ እህቴ አስተውለሽ
ይግባሽ ተአለሚ ይኑርሽ እውቀቱ
የሰሀቦች መንገድ እሱ ነው እውነቱ
በቁርዐን በሀዲስ ብቻ የሚመሩ
በዲን የሚብቃቁ ምንም ማይጨምሩ
የአላህን ትዕዛዝ ብቻ የሚያከብሩ
ስድብና ዛቻ የማይበግራቸው
የአላህ ወዳጆች እነሱ እኮ ናቸው፡፡
እናማ እህቴ
የነሱን ፈለግ አንችም ተከትለሽ
በተውሂድ በሱና በኢማን አጊጠሽ
በሀያዕ ተሞልተሽ በሂጃብ ተውበሽ
ፍካትሽ ድምቀትሽ ለባልሽ ብቻ አድርገሽ
ለአባትም ኩራት ለወንድም ጌጥ ሆነሽ
ያኔ እስልምናን ከፍ ታደርጊያለሽ!!!
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇
@RehimWAschannal
@RehimWAschannal