❤️🔥 አርምሞ ❤️🔥
አርምሞ (ዝምታ) መንፈሳዊ ሰው ካሉት ድንቅ ችሎታዎች መካከል አንዱ ነው:: ይህ ደግሞ የልብ፣ የነርቭ፣ የአሳብ፣ የስሜት፣ የጠባይና የሰውነት አርምሞን ያጠቃልላል:: የዝምተኛ ሰው ልብ ምንም ዓይነት ምክንያት ቢገጥሙትም ፈጽሞ አይታወከም:: ችግሮቹ ምንም ዓይነት ነገር ቢያደርሰብትም ዝምታውን አያጣውም:: ነቢዩ ዳዊት ይህን አስመልክቶ ሲናገር:- ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማማናለሁ።» (መዝ 26:3) ብሏል::
እንዲህ ዓይነቱ አርምሞ ከእምነት የሚመነጭ አርምሞ ነው:: አንድ ሰው ውስጣዊ ሰላሙን ሲያጣ በዐይኖቹ ፊት የሚመለከታቸው ነገሮች ሁሉ የታወኩ ይሆኑበታል፤ቀላሉም ነገር ውስብስብ ይሆንበታል፡፡
ይህ ውስብስብነት የሚመጣው ግን ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው:: ልብ ከተረጋጋ ነርቮቹም ይረጋጋሉ፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ የሰው ቁጣ ገንፍሎ አይወጣም፤ ይልቁንም ችግሩን በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ያቃልለዋል::
የሰው አዕምሮ አንድ ችግርን ማቃለል ከተሳነው ነርቮቻችን ለማገዝ በመካከል ጣልቃ ይገባሉ:: የተነሣሱት ነርቮች የመፍትሔ እጦትን ሊያሳውቁ ይችላሉ፣ ነርቮቹ ይበልጥ እየታወኩ በመጡ ቁጥር ደግሞ ይበልጥ ይነሣሳሉ፡፡ የተረጋጋ ልብ እና ነርቭ ያለው ሰው የአሳብና የድርጊት ዝምታን ገንዘቡ ማድረግ ይችላል:: አሳቦቹ ምንም ዓይነት ሁከት የሌለባቸውና የተመጣጠኑ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም ድርጊቱን የሚፈጽመው ከቁጣ ወይም ከጭንቀት በራቀ መንገድ በአርምሞና በትክክለኛነት ነው፡፡
ሰው ውስጣዊውን ሰላም እንዲያገኝ የሚረዳው ውጪያዊው ሰላም ነው:: ይህም በውስጡ ምንም ዓይነት የሚያውክ ሁኔታ የሌለበት ሰላማዊ አካባቢን ይፈጥራል:: ምክንያቱ ይህ በመሆኑም መነኰሳት ከሁከት፤ ከሰዎች ጫጫታ ወይም ከሚያውክ ወሬና ግጭት ርቀው በምድረ በዳ ውስጥ በሰላም ይኖራሉ፡፡ እነርሱ እንደዚህ ያለውን አርምሞ ተላምደውታል::
የመለየትና የብቸኝነት ሕይወት በአጠቃላይ አርምሞን ያመጣል:: የዚህ ምክንያቱም ስሜቶቻችን ሁሉ ስለሚረጋጉ ነው:: ቅዱሳን አባቶቻችን ስሜቶች የአሳቦች መንገድ ናቸው ይላሉ:: የምታዩት፤ የምትሰሙትና የምትዳስሱት ነገር ሁሉ አሳብ ይሰጣችኋል፡፡ ስሜቶቻችሁ ወሬ ከመሰብሰብ ተለይተው በእረፍት ላይ ከሆኑ አሳቦችን ከማሰብ እፎይ ትላላችሁ:: ፀጥ ያለ ቦታ የስሜትን መረጋጋት ያግዛል ይህ ደግሞ ወደ አሳቦች፥ ወደ ልብና ወደ ነርቭ መረጋጋት ያመራል::
ብዙ ሰዎች ጫጫታ ካለበት ስፍራ ርቀው የሚሄዱት የአዕምሮ ሰላምን ለመፈለግ ነው:: ባላቸው ብርታት ሁሉ አርምሞን ለማግኘት በፍቅር የሚፈልጉት ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ያለ ሁከትና ያለ ጫጫታ መኖር የማይችሉ ሰዎችም አሉ:: አርምሞ ለእነርሱ አሰልቺ ነገር ነው::
╭══•|❀.........♡...........❀|: ══╮
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
╰══•|❀.........♡...........❀|: ══╯