The Christian News

Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።
@TCNEW

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri

#አሳዛኝ_ታሪክ

"ልጄ እርግማን ሳትሆን በረከት ናት" ምን አይነት ጠንካራ እናት ... 😭😭😭

እቺ ቃል ኪዳን ትባላለች 21ዓመቷ ነው። የምትኖረው ከእናቷ ጋር ሲሆን እናቷ በልጇ ህመም ምክንያት በተደጋጋሚ እረፍት ትወስድ ስለነበር በዚው ምክንያት ከስራ አቋረጠች።

ወላጅ አባቷ ይህ ነገር ሲፈጠር ትቷቸው ሄደ። በፍርድ ቤት ውሳኔ 18ዓመት እስኪሞላት ደረስ በወር 400ብር ተቆራጭ ያደርግላት ነበር ነገር ግን 18ዓመት ሲሞላት የሚያደርግላትን ድጋፍ አቋረጠ። በአሁኑ ሰዓት እናቷ ሂሩት የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን እየሰራች ለመኖር ይታገላሉ።

ቃል ኪዳን ቀይ እና ቆንጅዬ የነበረውች ልጅ ነበረ። መጀመሪያ አከባቢ እንደ ማድያት አድርጎ የጀመራት ይህ ህመም ዛሬ 17ዓመታትን ይዟት ዘልቋል። በ17የህመም እና የስቃይ አመታት ውስጥ ከፍተኛ የሚባል 20 የቀዶ ጥገናዎችን አድርገዋል።

እናቷ ሂሩት ያደገቸውን አዲስ አበባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት መኖሪያቸውን ቂርቆስ ነው። "ልጄን እግዚአብሄር ሰጥቶኛል ይሄ ለምን ሆነ አልልም ነገር ግን ከዚህ በላይ እንዳይሆን ብቻ እጸልያለሁ" ትላላች። ባለፉት 17ዓመት ውስጥ አብረዋት የቆሞ፤ ያገዟትን ሳታቋርጥ ታመሰግናለች።

ቃል ኪዳን እናቷን ያለመታከት ታመሰግናታላች። ንግግር ማድረግ እስኪያቅታት ድረስ እንባ እየተናነቃት ደጋግማ አመሰግናለ አመሰግናለው አመሰግናለሁ ትላለች።

በመላው አለም የምትገኑ ውድ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ቃል ኪዳንን እና እናቷን መደገፍ ለምትፈልጉ በሙሉ ከታች ያለውን አድራሻ መጠቀም ትችላላችሁ።

ስልክ፥- 0983310405
ንግድ ባንክ አካውንት:- 1000266380098

#ዘማሪ_ሙሉነህ_ጩፋሞ

የተወዳጁ ኢንጅነር፤ ጸሐፊ፤ ዘማሪ ሙሉነህ ጩፋሞ አሳዛኝ የህይወት እና የአገልግሎት ጉዞ።

አንዳንድ ጊዜ እግዚያብሄር የጠራቸው ሰዎች ችግር ውስጥ ይገባሉ ነገር ግን ችግሮች ሁሉ ለመልካም ይሆንላቸዋል።

ዮሴፍን ወንድሞቹ ስለ ህልሙ ሲሉ እንደገፉት እና እንደሸጡት ሁሉ ይህ ተወዳጅ ዘማሪ በዚህ ተመሳሳይ ይህወት ውስጥ አልፏል።

የዚህ ተወዳጅ ዘማሪ ወንድሞቹ ለሊት በር ሰብረው ገብተው ሊገሉት ገብተው ነበር ድንገት ግን ጌታ እነሱ ሰብረው በገቡበት በር አስመለጠው።

ይህ ተወዳጅ ዘማሪ አዲስ አበባ በሚኖርበት ወቅት ወንድሙን ከክፍለ ሃገር አስመጥቶ ስራ ይዞ አብሮት እንዲኖር አድርጎት ነበር። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ውስጥ ይህ ወንድሙ እየተቀየረ መምጣት ጨመረ አልፎ ተርፎ ከአገልግሎት አምሽቶ ሲመጣ በር ይዘጋበት ጀመር።

ከዚህ በኋላ በጓደኞቹ ቤት በመጠለል እና በድጋፍ ቆየ ነገር ግን ይሄም አልሆን ሲል ሁሉንም እርግፍ አድርጎ ትቶ ወደ ትውልድ ስፍራው (ክፍለ ሃገር ሄደ) ነገር ግን ይሄ ወንድሙ አሁንም አልተወውም ይልቁንስ ያገለግልበት የነበረው ቤተክርስቲያን በመደወል ጭምር ስሙን እያጠፋ እንዳያገለግል ያደርገው ነበር።

ይህ ተወዳጅ ዘማሪ ይህ ሁሉ ሳይፈጠር ከ20ዓመት ቀደም ብሎ እንዲህ ሲል ዘምሮ ነበር።

ከአንድ አባት ተወልደን
በአንድ ጉያ አድገን
ዛሬ ትልቅ ሆነን
ምነው ተለያየን
ከልጅነታን በቤቱ አድገናል
ፍቅሩ ቸርነቱን ደጋግመን አይተናል
ካልካድነው በስተቀር ውለታው አለብን
ስንት ያሳለፈንን እንዴት እንረሳለን

ሲል ዘምሮ ነበር ይህ በአንድ ወቅት የዘመረው ዝማሬ ከ20ዓመታት በኋላ በራሱ ላይ ተፈጸመ። ምንም እንኳን ዛሬ ወንድሞቹ ከጌታ ቤት ወደ ኋላ ቢመለሱም የሆነ ወቅት ግን በአንድ መድረክ ጌታን ቆመው አገልግለው ነበር።

ዛሬ ግን ወንድሞቹ እሱን ለሊት በተኛበት ሊያርዱት ሲሞክሩ እሱ አልሳካ ሲላቸው እንዲገለው ጠንቋይ ቤት እስኪሄዱ የገዛ ሰጋዎቹ ጨክነውበት ነበር።

በመላው አለም የምትገኙ ወደ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ከዚህ ተወዳጅ ዘማሪ ህይወት ጥቂቱን ብቻ አካፈልናችሁ።

ሙሉነህ ጩፋሙ "ዘጸዓት ለኢትዮጵያ" የተሰኘ ስለ ሃገራችን የተዘመረ ተወዳጅ ዝማሬ ጨምሮ 3 ሙሉ አልበሞች አሉት። በዚህ ሰዓት ልክ ዮሴፍን የማያውቅ ትውልድ እንደተነሳ ዛሬም በኛ ትውልድ የቀደሙትን የማያውቅ እና እንዲሁም የዘነጋ ትውልድ የተነሳ ይመስላል። ለማንኛውም ሙሉነህን ለማግኘት እና ለመደገፍ የምትፈልጉ አካላት የተቀመጡትን አድራሻዎች መጠቀም ትችላላችሁ።

በቀጣይ በተመሳሳይ የተወሰነ የሱን አገልግሎት እና ህይወት በተመለከተ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ይዘንላችሁ እንመጣለን።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#ፍትህ_ለፈረንሳይ_መካነየሱስ..
ሁላችንም ይይንን ምስል በፌስቡክና በኢንስታግራም ገፆቻችን ፖስት በማድረግ ያላግባብ በግለሰቦች ፍትህ ተዛብቶ እንድትዘጋ ለተወሰነባት የፈረንሳይ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን ድምፅ እንሁን…

#news

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ለሚኖሩ 12 አቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ስራ ጀመረች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁህ አቡነ መልከፀዴቅ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፍ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ የስራ ሃላፍዎች ሌሎች የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት የቤት እድሳቱን አስጀምረዋል።

በጎ ማድረግ ከፈጣሪ የተማርነው ተግባር ነው ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁህ አቡነ መልከፀዴቅ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ያለውን በማካፈል ሊተጋገዝ እና ሊረዳዳ ይገባል ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመንፈሳዊ ግልጋሎት ባለፈ በማህበራዊ አገልግሎቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የምታደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክራ እንደምትቀጥል ሊቀ ጳጳስ ብፁህ አቡነ መልከፀዴቅ ገልጸዋል ።

የቤት ዕድሳት ከሚደረግላቸው ነዋሪዎች መካከል ምንም ደጋፊ ለሌላቸው አንዲት እናት ብፁው አቡነ መልከፀዴቅ በግላቸው ለአንድ ዓመት ወጪ የሚሆን የ24 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባለፈው ሳምንት በከተማ አስተዳደር በይፋ በተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 12 የአቅመ ደካማ ነዋሪ ቤቶችን እድሳት ለማድረግ ቃል መግባቷ ይታወሳል።

በማስጀመሪያ መረሃ ግብር የተገኙት የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፍ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በማከል በአዲስ አበባ ከተማ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ መጀመሩን አስታውሰው ይህንን የከተማ አስተዳደር ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነውብለዋል።

በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባለፈው ቃል የተገባውን አርዓያ በመሆን 12 የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶችን ለማደስ እና ለቀለብ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ዛሬ ማድረጋቸውን አመስግነው ይህ በጎ ጅማሬ ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት በዚህ የክረምት ወራት በእንዲህ አይነት በጎ ተግባራት በመሠማራት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#አሳዛኝ_ዜና
#በቤተክርስቲያን_ላይ_ጥቃት_ደረሰ

በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፓብሊክ ቤኒ በተባለ አካባቢ በሚገኝ ካቶሊካዊ ቁምስና እሑድ ሰኔ 20/2013 ዓ. ም የጦር መሣሪያ ጥቃት መድረሱ ታውቋል።

በጥቃቱ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን ከሥፍራው የወጣ ዘገባ አመልክቷል። የአገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጥቃቱን አውግዘው “በዚያ አካባቢ አንድም ቀን የሰው ሕይወት ሳይጠፋ የሚያልፍበት ቀን የለም” ብለዋል።

ከአካባቢው የተሰራጨው ዘገባ እንዳመለከተው እሑድ ሰኔ 20/2013 ዓ. ም በቡቴምቦ-ቤኒ ወረዳ በሚገኝ ካቶሊካዊ ቁምስና ላይ የተፈጸመው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት ከደረሰው በላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር ተገልጿል። እሑድ ማለዳ ላይ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በመንበረ ታቦት አካባቢ የተጠመደው ቦምብ ፈንድቶ በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋን ማድረሱ ታውቋል።

ፍንዳታው እሁድ በቀረበው የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለሚሰጥ የቅዱስ ሜሮን ምስጢር ሥፍራን በማዘጋጀት ላይ በነበሩ ሁለት ሴቶች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋን ያደረሰ መሆኑ ታውቋል። አደጋው የደረሰባቸው ሴቶች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።

በሰሜን ምሥራቅ ዴሞክራሲዊት ኮንጎ ሪፓብሊክ የምትገኝ ቡቴምቦ-ቤኒ ቁምስና
ከረጅም ዓመታት ወዲህ ጥቃት ሲደርስባት በነበረው በሰሜን ኪቩ ክፍለ ሀገር የምትገኝ ወረዳ መሆኗ ታውቋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/

#አዲስ_ነገር

#ዘማሪ_ሙሉነህ_ጩፋሞ_የት_ጠፋ?

ወንድማችን ኢንጂነር እና ዘማሪ ሙሉነህ ጩፋሞ የተቀባ እግዚአብሔር ለምድርቷ ካስነሳቸው ሃያላን መካከል አንዱ ነዉ በዝማሬ አገልግሎቱም ብዙ ተጽናንተናል።

"እንደገና ፊትህን መልሰው" የተሰኘው ዝማሬ እስከዛሬ ድረስ ድንቅ ትንቢታዊ መልእክት ያለበት መዝሙር፣ በተለይም በአሁኑ ዘመን የሚሆነውን በደጉ ጊዜ በመገለጥ የዘመረው መዝሙር ነው።

ዛሬ ላይ ግን እንደሰማነው ይህ ተወዳጅ አገልጋይ በሚያሳዝን ልብን በሚጎዳ ማንም በማያውቀው ችግር ውስጥ እንደሆነ ተስምቷል።

#ደማቅ_ሕይወት_አገልግሎት የተሰኘ አገልግሎት ዘማሪውን አነጋግሮ ነበር። ወደ ምሽት አከባቢ ይህ ተወዳጅ አንጋፋ አገልጋይ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#መልካም_ወጣት_2013
የ2013ዓ.ም መልካም ወጣት ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል።

ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በይፋ የሚጀምረው የመልካም ወጣት ስልጠና 7ኛ ምዝገባ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

መልካም ወጣት ስልጠና በኮቮድ-19 (ኮሮና ወረርሽ) ምክንያት በ2012ዓ.ም ሳይከናወን መቅረቱ ይታወሳል። የዘንድሮውም መልካም ወጣት ምንም እንኳን ቁጥራቸው ባይገለጽም በኮሮና ምክንያት አንሰተኛ ወጣቶች ብቻ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

2011ዓ.ም በነበረው ሰልጠና 35,000 ወጣቶች መሳተፋቸው ይታወሳል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#አዲስ_መረጃ

#ነብይ_ዳግም_ታደለ_በኮሮና_ተይዟል።

የበረከት ጉባኤ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን መስራች እና ባለ ራዕይ ነብይ ዳግም ከሰሞኑ በኮቪድ - 19 (በኮሮና) መያዙ ታውቋል።

በዛሬው እለት ከ Abel Demelash ቻናል ጋር ባደረገው ቆይታ እንደገለጸው ከሆነ ከሰሞኑ ባልታወቀ ምክንያት በኮሮና መያዙን እና ህክምና እየተከታተለ እና በማገገም ላይ እንዳለ ተናግሯል።

ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የአምልኮ ስነ ስረዓታቸውን ላይ የኮሮና መከላከያ መንገዶችን ጥንቃቄ ጉድለት እንዳለ የተናገረ ሲሆን ምዕመናን እና መሪዎች ትኩረት መስጠት እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል።

እሱም ከሰሞኑ ህክምናውን እየተከታተለ እንደሆነ እና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገልኝ ገልጾ በመጪ 3 ሳምንታት ውስጥ እንደ አምላክ ፍቃድ ወደ አገልግሎት እንደሚመለስ ገለጿል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ነብይ ዳግም ተሽሎት በመልካም ጤንነት እንዲመለስ ምኞታችን ነው።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#ተሰረዘ

#ካውንስሉ_ሊሰጠው_የነበረው_አስቸኳይ_መግለጫ_ተሰረዘ

#2_ልጆቼ_ማጥናት_አልቻሉም_በሚል_ክስ_የመካነ_ኢየሱስ_ቤተክርስቲያን_መዘጋቷን_መዘገባችን_ይታወሳል።

በመሆኑም ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስሉ ነገ ሰኔ 25/2013ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00ሰዓት ላይ በጽ/ቤቱ አስቸኳይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጾ ነበር።

አሁን በደረሰን መረጃ መረሃ ግብሩ እንደተሰረዘ ታውቋል። እንደሰማነው መረጃ ከሆነ የካውንስሉን አመራሮች መግለጫ ሊሰጡ መሆኑን ተከትሎ የፌደራል አቃቢ ህግ ስለጉዳዩ ለውይይት እንደጋበዟቸው ተሰምቷል።

የካውንስሉ አመራሮች ጉዳዩን ከአቃቢ ህግ ውይይት በኋላ የተደረሰበትን ውጡአት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉም ታውቋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና መረጃዎችን እየተከታተልን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#ሰበር_መረጃ

#ካውንስሉ_አስቸኳይ_መግለጫ_ሊሰጥ_ነው።

#2_ልጆቼ_ማጥናት_አልቻሉም_በሚል_ክስ_የመካነ_ኢየሱስ_ቤተክርስቲያን_መዘጋቷን_መዘገባችን_ይታወሳል።

አሁን በደረሰን መረጃ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስሉ ጉዳዩን በተመለከተ ነገ ሰኔ 25/2013ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00ሰዓት ላይ በጽ/ቤቱ አስቸኳይ መግለጫ እንደሚሰጥ ሰምተናል።

እንደሰማነው መረጃ ከሆነመግለጫውን በስፍራው ማንኛውም መንፈሳዊ ሚዲያዎች (ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምትሰሩትንም ያካትታል) መገኘት እና መዘገብ ይቻላል።

በመሆኑም #the_christian_news በስፍራው ተገኝቶ የመግለጫውን ሙሉ ሃሳብ በጽሁፍ እና በቪዲዮ ወደ እናንተ ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

489

obunachilar
Kanal statistikasi