የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለባህል ህክምና አዋቂዎች የተግባር ተኮር የላቦራቶሪ ስልጠና ሰጠ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር፣ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋርማሲ ት/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚገኙ የባህል ሃኪሞችን የቤተ ሙከራ ተግባር ተኮር ስልጠና ህዳር 5 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቴክኖሎጅ ሽግግር እና ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው እንዳሉት ሃኪሞች በሚሰሩት ስራ ላይ እሴት መጨመር እንዲችሉ ማስቻል ሲሆን፣ ቀለል ባለ መልኩ በባህል ሃኪሞች ሊተገበር በሚችል መልኩ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡ ስልጠናው በተለይም በመሰረታዊ የቅመማ ቁሳቁሶች አጠቃቀም፡ የተለያዩ የቆዳ ቅባቶች አዘገጃጀቶች እንዲሁም መድሃኒት በማዘጋጀት ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ቅድመ እና ድህረ ጥንቃቄዎች የዳሰሰ ነው ፡ ከዚህ በተጨማሪም ስልጠናው ስለመድሃኒት ማሸጊያ አመራረጥ እና አጠቃቀም እና ስለተለጣፊ ወረቀት (ሌብሊንግ) ዝግጅት መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳቦችን ያካተተ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ አክለው ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የባህል ህክምና ዴስክ ኃላፊ እና የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጳውሎስ ዳዊት የባህል ህክምና አዋቂዎች አእምሯዊ መብታቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ለሰልጣኞች አብራርተዋል፡፡
የባህል ሃኪሞች በዋናነት እንደ መጀመሪያ የንግድ ምልክቶች ማስመዝገብ ላይ ትኩረት ቢያደርጉ ተጠቃሚነታቻውን እንደሚያሰፋው የስልጠናው ዋና አስተባባሪ እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፋርማሲ ት/ቤት አስተማሪ እንዲሁም የቴክኖሎጅ ሽግግር እና ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ግንኙነት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋርማሲ ት/ቤት ዲን ዶ/ር አንተነህ በለጠ እንዲሁም የፋርማሲዩቲክስ እና ሶሻል ፋርማሲ ት/ክፍል ሃላፊ ዶ/ር መስፍን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህንን በጎ አላማ የያዘ የትብብር ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በከፍተኛ ደስታ በመቀበል ለስልጠናው የሚያስፈልገውን ግብአት አዘጋጅተው መጠበቃቸውን ገልፀዋል። ዶ/ር አንተነህ አያይዘውም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባህል ህክምናውን ለማዘመን እያደረገ ያለውን ብርቱ ጥረት አድንቀው፣ በቀጣይም በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን ለመካፈል ከኦሮሚያና ከአዲስ አበባ የመጡ የባህል ሃኪሞች የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ የባህል ሃኪሞችን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ብርቱ ጥረት አንድንቀዋል፡፡
በተያያዘም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር፣ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና የቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይርክቶሬት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታደሰ አወቀ የጎንደር ዩኒቨሪሲቲ በቅርቡ የክሊኒካል ሙከራ ማእከል ማቋቋሙን በመግለጽ የባህል ህክምናን እድገት ለማረጋገጥ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁልጊዜም ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለልህቀት እንተጋለን!
ህ/ዓ/አ/ግ/ዳይሬክቶሬት
ህዳር 7/2015ዓ/ም