1, ፊቅህ ማለት: -
☞በቋንቋ ደረጃ ማወቅ (መገንዘብ)
አላህ (ሱ,ወ) እንድህ ይላል: -አላህ ኸይር ያሻለት ሰው ድኑን (ሀይማኖቱን) ያሳውቀዋል እንድረዳ ፣ እንድገነዘብ ያደርገዋል
☞ ፊቅሁል ኢባዳ:- ኢባዳ ላይ ያተኮረ ሶላት ፣ ፆም ፣ዘካ ፣ ሀጂ ላይ ያተኮረ
የፊቁሁል ኢባዳ አይነቶች (ትምህርቶች) 7 አይነት ናቸው ሌላኛው ስለ ቤተሰብ የሚያጠና አለ ቤተሰባዊ ነክ የሆኑ ጉዳዬችን የሚያጠና አለ እንደዚሁም ፊቅሁል ሙአመላት ይህም ህዝቦች በመካከላቸው ያላቸውን ግንኙነት በስፋት የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው።ሌላው
አስተዳደር ነክ የሆኑ ጉዳዬችን የሚያጠና የፊቅህ ዘርፍ ነው ይህም ህጎችን (የህዝቦችና የመንግስታት (ከሚያስተዳድራቸው አካል ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው።ሌላው
ፊቅሁል እቁባት የሚል ቅጣትን በተመለከተ ያጠፋን ሰው ምን አይነት ቅጣት ይጣልበታል ምን ይጠብቀዋል
አለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን የሚያጠና የአኘፊቅህ ዘርፍ አለ
ስለ አህላቅ የሚያጠና የፊቅህ ዘርፍ አለ።
በዚህ መልኩ ኡለማዎች በመከፋፈል የፊቅህን ትምህርት ዘርዝረው ያስተምራሉ።
☞አንድ ሰው እውቀትን የሚጨብጥበት ነብዩ (ሰ,ዐ,ወ) በተከተለ መልኩ ኢባዳን ለመፈፀም ነው
ማንኛውም ኢባዳ ተቀባይነት የሚያገኘው በኢኽላስና በሙታብዓ ስለሆነ ነው
✏አንድ ሰው የድን እውቀት ካለው በማንኛውም ዘርፍ እውቀቱን ከተጠቀመበት ኢህላስን በልቡ ውስጥ እንድያመጣ ይረዳዋል
✏አንድ ሰው የድን እውቀት ካለው ☞አቂዳው የተስተካከለ ይሆናል። ☞ኢባዳውም ትክክል ይሆናል።
☞ከሰዎች ጋር ያለውም ግንኙነት የተስተካከለ ይሆናል።
☞ሁሉንም በመስመሩ ለማስኬድ ይረዳዋል።
☞በተቀመጠለት ለመፈፀምም ያግዘዋል።
☞አላህን ብቻ እንድገዛ ይረዳዋል።
☞በቀጥተኛ ጎዳና እንድጓዝም ይረዳዋል።........
☞ከጥመትና ከመሀይምነት እንድወጣ ዋስትና ይሆንለታል።
✏የድን እውቀትን ማወቅ ወደ ጀነት የሚወስድ መንገድ ነው።ይህም በሀድስ ሰፍሯል:-
አላህ ኸይር ያሻለት ሰው የድን እውቀትን ያስገነዝበዋል፣ ያሳውቀዋል።
ከባሮቹ አላህን የሚፈሩት ማናቸው አዋቂዎች ፣ኡለማዎች ናቸው።
☞የድን እውቀትን ለመማር የተጓዘ ወይንም ደግሞ የዚህን መንገድ የተከተለ አላህ (ሱ,ወ) የጀነት መንገድን ያገራለታል።
✏ ፈርድ (ግደታ) ማለት:
አንድን ነገር ከሰራነው የምንሸለምበትና ምንዳ የምናገኝበት ካልሰራነው የምንቀጣበት (የምንጠየቅበት) ስራን የሚያመለክት ማለት ነው። ግደታ የሆነ ነገር እንድንፈፅመው ወይም እንዳንፈፅመው ግደታ የተደረገብን ነገር ማለት ነው።
ፈርድ መከወኑ (መተግበሩ) ግደታ ነው። በመተግበራችን አላህ (ሱ,ወ) ምንዳን ይሰጠናል። ካለተገበርነው ደግሞ እንቀጣበታለን ማለት ነው።
✏ፈርደል አይን ማለት:-
በእያንዳንዱ (በሁሉም) ሰው ላይ ግደታ የሚሆን ማለት ነው
☞ፈርድ ግደታ ማለት ነው
☞አይን በእያንዳንዱ ሰው ላይ ማለት ነው
ምሳሌ:- መታወቅ ያለበት እውቀት ከሆነ ፈርደል አይን ነው ከተባለ ምሳሌ ፋቲሀን አያንዳንዱ ሰው በሰለት ወቅት መቅራት ግደታ ነው
✏ፈርደል ኪፋያ ማለት:-
በሁሉም ሰው ላይ ግደታ የማይሆን ወይም የተወሰኑ የማህበረሰብ ግለሰቦች ካወቁት (ከተገበሩት) ሚወርድ ሌሎቹ የማይጠየቁበት
የተወሰኑ ሰዎች ከፈፀሙት ሀላፊነቱ የሚበቃ ነገር ማለት ነው
ለምሳሌ:- ሶላቱል ጀናዛ መስገድ በሁሉም ሰው ላይ ግደታ አይሆንም
✏ሱና ማለት:-
መሰራት ያለበት ነገር ሆኖ ( እንድሰራ የሚበረታታ) ተግባር ኢባዳ ማለት ነው። ይህም ሽልማት የሚያስገኝ ከተውት ደግሞ የማያስቀጣ
ሱና ሁሉም ሰው እንድሰራ የሚበረታታ ጉዳይ ሆኖ ከተሰራ አጂር (ምንዳ) የሚያስገኝ ካልተሰራ ደግሞ የማያስቀጣ
✏ሱነቱል ሙዓከዳ ማለት:-
ነብዩ (ሰ,ዐ,ወ) ሁል ጊዜ የሚያከናውኑት፣ የማይተውት ፣ ሁሌ የሚተገብሩት ተግባር ነገር ማለት ነው። ጠንካራ ሱና ይባላል።
✏ሱነቱል ሙስተሃብ (የተወደደ ሱና) ማለት:-
የተወደደ ሱና ጠንካራ ያልሆነ ማለት ነው። ይህም ነብዩ (ሰ,ዐ,ወ) ሁል ጊዜ የማያከናውነው ፣ የማይተገብረው አንዳንድ ጊዜ የሚሰሩት ነገር ማለት ነው መስራቱ ግን የተወደደ ይሆናል ።
✏ሙባህ ማለት:-
የተፈቀደ ማለት ነው። ሽልማት የማያስገኝ ቅጣትንም የማያስቀጣ
ብትጠቀመውም ከአላህ ዘንድ ምንዳ የማያስገኝ ከተውት ደግሞ ያያስቀጣ ማለት ነው።
✏ መክሩህ ማለት:-
የተጠላ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሸሪዓው እንዳይተገበር የሚያበረታታ (የሚገፋፋ) ነገር ማለት ነው ። ሸሪአው እንዳንሰራው የሚከለክለን ነገር ነው መክሩህ ይባላል።
☞መክሩህ የሆነን ነገር መተው ያሸልማል (ምንዳ) ያስገኛል ።የተጠላን ነገር ደግሞ የተጠቀመ አይቀጣበትም።
✏ሀራም ማለት:-
የተከለከለ (የተጠላ) ማለት ነው። አንድ ሰው ሀራም የተባለውን ነገር ከተላለፈ የሚያስቀጣ ሀራም የተባለውን ነገር የሚተወውም ከሆነ ይሸለምበታል ምንዳ ያገኝበታል
አንድ ሀራም ነው የተባለን ነገር የተገበረ ፣ የተጠቀመ ፣ የፈፀመ ሰው ይቀጣበታል ። ካልተገበረው ደግሞ ምንዳ ያገኝበታል።
✏ኢጂማዕ ማለት:-
የሙስሊሙ ኡማ ተመራማሪዎች ፣ ታላላቅ አሊሞች ፣ ኡለማዎች የተስማሙበት ጉዳዮች በነርሱ ስምምነት መከተል ግደታ የሆነ ነገር ማለት ነው።
✏ቅያስ ማለት:-
አንድ ነገር ቀጥታ ማስረጃ ያልተገኘለት አንድን ጉዳይ ምሳሌ አስመልክቶ ቀጥተኛ የሆነ የፁሁፍ ማስረጃ ካልተገኘለት ከሀዲስ ፣ በቁርዓን ማለት ነው ለሱ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል መፍትሄ ከሌላኛው መውሰድ
አንድ መልእክትን የሚያስተላልፍ ሌላ አያ አለ እንበልና ያ ጉዳይ ከዛ ላይ የነብዮችን ምላሽ እንድሰጥ ሆኖ ይገኛል ይህ አይነቱ ቂያስ ይባላል።
☞ አንድን ነገር ለሌሎች ሀሳቡን ከተረዱ በኃላ ከዙያ ላይ ለሌሎቹ ጉዳዮች የመፍትሄ ሀሳብ ማመንጨት (አቅጣጫ መጠቆም) ቂያስ ይባላል።
✏ጠሃራ ማለት: -
በቋንቋ ደረጃ (ነዛፋ) ንፅህና ማለት ነው ።
አወንታዊ ፍቹ: ሁለት ትርጉሞች አሉት
☞ አል ጠሃራቱል ማዕነውያ:- የማይታየው የማይዳሰሰውን አካል ልብን የሚመለከት ጠሃራ ማለት ነው
☞ አል ጠሃራቱል ኪስያ: - አካላችንን ማፅዳት ፣ ልብሳችንን ውጫዊ የሆነን ነገር የሚታየውን ፣ የሚዳሰሰውን ነገር የሱን ጠሃራ መጠበቅ
✏ኡለማዎች በቀላሉ እንድንገነዘብ አስቀምጠውልናል
ለምሳሌ:- አል ጠሃታቱል ማዕነውያ ይህን በሁለት ከፍለውታል
☞ትልቁ :-ቀልባችንን ከሽርክ ፣ ከቢድዓ ማፅዳት ከዛ በተውሂድ መሙላት ፣ በተውሂድ አመለካከት መተካት ይህ አል ጠሃራቱል ኩብራ ይባላል።
ቀልብን ከኩራት ፣ ከኒፋቅ ፣ ከፊህድ ከተንኮል ባጠቃላይ ከክፉ አመለካከቶች ማፅዳት አለብን ። ከዚያም በጥሩ አስተሳሰብ በተውሂድ ፣ በአላህ ውደታ ፣ በነብዩ (ሰ,ዐ,ወ) ውደታ ልንሞላት ይገባል።
☞ትንሹ: - ከተለያዩ ወንጀሎች ቀልብን ማፅዳት ነው። ከዚያ በኃላ በመልካም ነገሮች መሙላትና መጠበቅ (አል ጠሃራቱል ሹብራ)
•════•••🌺🍃•••════•
ሼር 👇JoiN👇 & Share👇
https://t.me/AAASELEFYAhttps://t.me/AAASELEFYA